Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሁለት የፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የም | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በሁለት የፈጠራ ስራዎች ዘርፍ ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የምስክር ወረቀት አገኘ
===================

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ :- ነሐሴ 15/2014 ዓ.ም (ደማዩ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከ"እንሰት" የሚሰራ ጠላና አዘገጃጀት እና እንዲሁም ከ"እንሰት" የሚሰራ አረቂና አዘገጃጀት ዘርፎች ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ባለስልጣን የአዕምሯዊ ባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀቶችን ማግኘቱን የዩኒቨርሲቲያችን የዩኒቨርሲቲ-እንዱስትሪ ትስስርናቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፈ ይበልጣል ታረቀኝ አሳውቀውናል።

ከዳይሬክተሩ ባገኘነው መረጃ መሰረት ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የእነዚህ ሁለት የፈጠራ ስራ ባለቤት ሊሆን የቻለው የፈጠራ ስራ ምርምር ካደረጉት መምህርና ተመራማሪ አቶ ባወቀ ጥሩነህ ጋር በትብብር በተሰራ የምርምር ፕሮጀክት መሆኑ ታውቋል ።

ይህ ፈጠራ ስራ ውጤት እውን እንዲሆን በዩኒቨርሲቲው የአዕምሯዊ ንብረት ፖሊሲ መሰረት በምርምር ሂደቱ ወቅት የሚያስፈልጉ የቤተ ሙከራ፣ የተመራማሪ እና ሌሎችም ለሂደቱ አስፈላጊ ወጭዎችን በሙሉ ዩኒቨርሲቲው የሸፈነ ሲሆን ተመራማሪው በበኩሉ ደግሞ የፈጠራ ሀሳቡንና ዝርዝር ሂደቱን በተመለከተ ሙያዊ ደረጃውን የጠበቀ የፕሮጀክት እቅድ በማቅረብ በትብብር እንደተሰራና ዩኒቨርሲቲያችንም የፈጠራ ስራው ባለቤትነትን ማግኘት እንደቻለ ረ/ፕ ይበልጣል ታረቀኝ ጨምረው ገልፀዋል።

በመጨረሻም እንደዩኒቨርሲቲ በዚህ የፈጠራ ስራ ዘርፍ በተገኘው ምስክር ወረቀት መደሳተቸውን ገልፀው ሁሉም የዩኒቨርሲቲያችን ተመራማሪ ማህበረሰብ ደረጃቸውን የጠበቁና ከዚህ በፊት በሌላ አካል ያልተሰሩ የፈጠራና ምርምር ስራዎቻቸውን ለዩኒቨርሲቲው እያቀረቡ በጋራ እንድንሰራ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ይህ የፈጠራ ስራ ሙሉ በሙሉ ወደተግባር ሲገባ በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለምንም አገልግሎት እንዲሁ የሚታወቀውን የእንሰት ተክል በሰፊው እንዲመረትና ጥቅም ላይ እንዲውል ለማድረግ የሚያስችል የምርምር ውጤት እንደሆነ መረዳት ይቻላል።

ከታች ያስቀመጥናቸው የዩኒቨርሲቲያችን ይፋዊ የማህበራዊ ትስስር አድራሻዎች ናቸው። ተራ በተራ ሊንኮቹን እየተጫናችሁ ትወዳጁን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን



ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"

ስለአብሮነታችሁ እናመሰግናለን