Get Mystery Box with random crypto!

“ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም” እና “የሕይወት ቃርሚያ” በሚል ርዕስ የተደረሱ ሁለት መጽሐ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

“ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም” እና “የሕይወት ቃርሚያ” በሚል ርዕስ የተደረሱ ሁለት መጽሐፍት ተመረቁ

====================

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ሰኔ 28/2014 ዓ.ም ( ደ.ማ.ዩ. ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ድሬክቶሬት ) በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በማሀበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ በአማርኛ ቋንቋና ስነ-ፅሁፍ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ በድሉ አዳም “ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም” እንዲሁም በዲያቆን አሻግሬ አምጤ “የሕይወት ቃርሚያ” በሚል ርዕስ የተደረሱ ሁለት መጽሐፍት የዩኒቨርሲቲያችን መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች፣የአካባቢዉ ማህበረሰብ አካላትና የደራሲዎቹ ቤተሰቦች በተገኙበት ተመርቀዋል፡፡


በዩኒቨርሲቲያችን የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ዲን ዶ.ር አማረ ሰውነት የመጻሕፍቱን መመረቅ በማስመልከት የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸዉም የግአዝ ቋንቋ በሀገራችን ትልቁን ታሪክ መዝግቦና ሰንዶ የያዘ ቋንቋ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ህልውናዋ ነዉ ብለዋል፡፡ ካለ ግእዝ ኢትዮጵያ ከየት ተነስታ የት እንደደረሰች ማወቅ አይቻልም፡፡ ምክንያቱም ግእዝ የኢትዮጵያን ሚስጢራት በትልቁ ጨምቆ የያዘ ቋንቋ በመሆኑ፡፡ የግዕዝ ቋንቋ መፈላሰፊያችንና ታሪካችንን የምናውቅበት ቋንቋ ነው፡፡ በመሆኑም ታሪካችንን ለማወቅ ሀገራችንን ለማሳደግ የግእዝን ቋንቋ መማር ማወቅ ማሳደግ ይገባል ፤ስለሆነም በዛሬው ዕለት ለመመረቅ የበቃው ይህ የግዕዝ አማረኛ ቃላት ለሁሉም ቋንቋውን ለማሳደግና ሚስጢራትን ለማወቅ የማይተካ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡


በሌላ መልኩ በደራሲ ዲያቆን አሻግሬ አምጤ የተደረሰው የሕይወት ቃርሚያ የተሰኘው መጽሐፍ ትውልዱ ሲወርድ ሲዋረድ የመጡ መልካም እሴቶችን ጠብቆ እንዲይዝና ወደ ማንነቱ እንዲመለስ በሚያግዝ መልኩ የቀረበ መጽሐፍ በመሆኑ ጠቀሜታዉ የጎላ እንደሚሆን እተማመናለሁ፡፡ ስለሆነም የሁለቱም መፅሐፍት ደራሲያን እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታቸውን ገልፀዋል፡፡


ግእዝ-አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም በተሰኘዉ መጽሐፍ ላይ መምህር ሰናይ ታረቀኝ፣ የሕይወት ቃርሚያ በተሰኘው መጽሐፉ ላይ ደግሞ ዶ.ር አራጋው አንተነህ ሙያዊ ዳሰሳ አድርገዉበታል፡፡


መምህር በድሉ አዳም የግእዝ አማርኛ መዝገበ ቃላት ለሁሉም መፃፍ ደራሲ እንደገለፁት ከዋናዉ የመማር ማስተማር ስራዬ በተጨማሪነት የግእዝ ቋንቋን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ሳስተምር ተማሪዎቼ ቋንቋዉን ለማጥናት ሲቸገሩ በማየቴ ችግሩን ለመቅረፍ በማሰብ ይህን መፅሀፍ ለማዘጋጀት እንደተነሳሱ ገልፀዋል፡፡ የግእዝ ቋንቋን መማር የኢትዮጵያን ጥበብ ፈልፍሎ ለማውጣት ትልቅ አቅም እንዳለዉና የዚህ መፅሐፍ መታተምም አንድም ለተማሪዎች እንደማጣቀሻ ያገለግላቸዋል በሌላ በኩልም የግእዝ ቋንቋን ለማሳደግ ብዙ ፍይዳ እንደሚኖረዉ አስረድተዋል፡፡


በሌላ በኩል የህይወት ቃርሚያ የተሰኘው መፅሐፍ ደራሲ ዲያቆን አሻግሬ አምጤ እንደገለፁት መጽሐፉ በዋናነት የቀደሙ አባቶቻችንን አኗኗር ዘይቤ፣ መልካም እሴቶችንና ትውፊቶችን መሠረት አድርጎ እንደተፃፈ ገልፀዋል፡፡ ታሪክን ፣ ስነ- ፅሑፍን ፣ ስነ- ምግባርን ፣ ስነ-ልቦናን ህግና ፍትህን ለሰዎች መልካም ማድረግን ርህራሄንና ሌሎችንም እየጠፉ ያሉ መልካም ነገሮችን መመለስ እንደሚያስፈልግና ሀገራችን የተጋረጠባትን የባህል ወረራ ፣ የማንነት ጥያቄና የዕውቀት ክፍተት ለመሙላት ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡ በምረቃ ፕሮግራሙ ስነ ፅሑፍ ና ልዩ ልዩ ቅኔዎችም ቀርበዋል።