Get Mystery Box with random crypto!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሰርጥ አድራሻ: @debre_markos_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 23

2022-11-11 11:05:49 በሰላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት ከተለያዩ የሀገራችን ክልሎች የተውጣጡና በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ5ኛው ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ስልጠና በመውሰድ ላይ የሚገኙ ወጣቶች ዛሬ ጠዋት ወደ ስልጠና አዳራሽ ከመግባታቸው በፊት የኢትዮጵያ ህዝብ ብሔራዊ መዝሙር ሲዘምሩ ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ህዳር 02/2015 ዓ.ም ( የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት )

የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!


ዌብሳይት www.dmu.edu.et
ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University
ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia
እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/
ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

ከእኛ ጋር ሰለሆናችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!
3.4K viewsedited  08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-11 11:05:26
3.3K views08:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 21:40:23 የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ0215 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ ተካሄደ
================
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ህዳር 1/2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት )

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ2014 ዓ.ም የዕቅድ ክንውን ግምገማ እና የ2015 ዓ.ም በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ የውይይት መድረክ በሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ ተካሄደ

በውይይት መድረኩ የብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ.ር ታፈረ መላኩ የውይይት መድረኩን ዓላማና አስፈላጊነት በተመለከተ የመግቢያ ንግግር አድርገዋል።

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ፣ደራሲ እና እንዲሁም በአሁኑ ስዓት ደግሞ በማህበረሰባችን ውስጥ የገጠሙንን ማህበራዊ ሳንካዎች ለመቅረፍ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የማነቃቂያ ንግግር በማቅረብ ላይ የሚገኙት ዶ.ር ሻምበል አጉማስ በውይይት ጉባዔያችን ላይ ተገኝተው ለዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ቁልፍ ንግግር አቅርበዋል።

በውይይት መድረኩ የ2014 ዓ.ም በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015 ዓ.ም በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል።
ከሰብሰባው ተሳታፊዎችም በቀረቡት ሪፖርቶችና የስራ እቅዶች ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

ከስብሰባው ታሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና ሀሳቦችም የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ዶ.ር ታፈረ መላኩ ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕ ዶ.ር ይሄይስ አረጉ እና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንት ዶ.ር አስካለማሪያም አዳሙ በየዘርፋቸው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

"የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ"
4.3K viewsedited  18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-10 21:39:57
4.2K views18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 19:03:29
#New
3.0K views16:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 17:56:34 በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለአምስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

===============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም (የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)

በኢፌዴሪ መንግስት የሰላም ሚኒስቴርና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ለአምስተኛ ዙር የሚደረገውን የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ የሰላም ሚኒስቴር ወጣቶች ላይ እየሰራ ያለው ሥራ ወቅቱን የጠበቀና ጊዜውን የሚመጥን መሆኑን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው ሰልጣኝ ወጣቶች በቆይታቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ላቃቸው አብጠው የተገኙ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር እየሰራ ያለው መልካም ተግባር እንደሆነ ተናግረው ሰልጣኞች በደብረ ማርቆስ ከተማና በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ያለምንም ችግር ስልጠናቸውን አጠናቅቀው እንዲመለሱ አብረን በተባባሪነት እንሰራን ሲሉ ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትር ዋና አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ እንደተናገሩት በጎ ፈቃደኝነት ያለ ማንም ግፊት በራስ ተነሳሽነት የሚፈፀም የህሊና እርካታ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ገልፀው "በጎነት ለአብሮነት" በሚል የተዘጋጀው መርሃግብር አንዱ የሌላውን እሴት እንዲያውቅና እርስ በእርስ በመጋመድ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚያግዝ ፕሮግራም እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

አቶ ካይዳኪ አክለውም በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ የሆናችሁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ ሃገራዊ አንድነትን ለማጠናከር የጎላ ሚና ያላችሁ በመሆኑ የሚሰጠውን ስልጠና በብቃትና ስነምግባር በተሞላበት መልኩ በመከታተል ሀገራዊ ሃላፊታችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል ፡፡

በአምስተኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም በአምስት ዩኒቨርስቲዎች ከ10ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ 1ሺህ ሰልጣኞች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ከዚህ በፊት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ለበጎ ፈቃደኞች ስልጠናው የተሰጠ መሆኑ ይታወሳል።
2.3K viewsedited  14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-06 17:56:19
2.2K views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 21:22:57 #ማስታወቂያ
ለደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የአካባቢው ማህበረሰብ በሙሉ፦

በዩኒቨርሲቲያችን የስፖርት ሳይንስ ጅምናዚዬም ሲሰጥ የቆዬው የጅም ስፖርት አገልግሎት በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ምክንያት ለሳምንታት ተቋርጦ መቆዬቱ ይታወቃል።
ከ26/02/2014 ዓ.ም ጀምሮ በሙሉ አቅም ስራ የጀመርን መሆኑን እየገለፅን ነባር የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች በተለመደው ፕሮግራም መሰረት እንድትቀጥሉ እያሳሰብን በአዲስ ለመመዝገብና የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን የምትፈልጉ ደግሞ በስልክ ቁጥር 09-13-87-48-67 በመደወል ሙሉ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

የስፖርት ሳይንስ ጅምናዚዬም
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ዌብሳይት www.dmu.edu.et

ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

ቲዊተር https://twitter.com/dmu_ethiopia

እንስታግራም https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/
ሊንክድኢን https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

"የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!"

ከእኛ ጋር ሰለሆናችሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!
4.4K viewsedited  18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-05 21:22:21
3.9K views18:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ