Get Mystery Box with random crypto!

የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ0215 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የ2014 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ0215 ዓ.ም ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች የውይይት መድረክ ተካሄደ
================
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፣ ህዳር 1/2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት )

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የ2014 ዓ.ም የዕቅድ ክንውን ግምገማ እና የ2015 ዓ.ም በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ የውይይት መድረክ በሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ ተካሄደ

በውይይት መድረኩ የብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ.ር ታፈረ መላኩ የውይይት መድረኩን ዓላማና አስፈላጊነት በተመለከተ የመግቢያ ንግግር አድርገዋል።

በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ፣ደራሲ እና እንዲሁም በአሁኑ ስዓት ደግሞ በማህበረሰባችን ውስጥ የገጠሙንን ማህበራዊ ሳንካዎች ለመቅረፍ ለተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የማነቃቂያ ንግግር በማቅረብ ላይ የሚገኙት ዶ.ር ሻምበል አጉማስ በውይይት ጉባዔያችን ላይ ተገኝተው ለዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ ቁልፍ ንግግር አቅርበዋል።

በውይይት መድረኩ የ2014 ዓ.ም በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015 ዓ.ም በጀት አመት ዋና ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች ዝርዝር መረጃዎች ቀርበዋል።
ከሰብሰባው ተሳታፊዎችም በቀረቡት ሪፖርቶችና የስራ እቅዶች ዙሪያ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተሰጥተዋል።

ከስብሰባው ታሳታፊዎች ለቀረቡ ጥያቄዎችና ሀሳቦችም የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚደንት ዶ.ር ታፈረ መላኩ ፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕ ዶ.ር ይሄይስ አረጉ እና የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚደንት ዶ.ር አስካለማሪያም አዳሙ በየዘርፋቸው ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

"የእውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ"