Get Mystery Box with random crypto!

በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለአምስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

በደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለአምስተኛ ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሄደ

===============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም (የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት)

በኢፌዴሪ መንግስት የሰላም ሚኒስቴርና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ትብብር ለአምስተኛ ዙር የሚደረገውን የብሔራዊ በጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም ሰልጣኝ ወጣቶች የእንኳን ደህና መጣችሁና የስልጠና ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ የሰላም ሚኒስቴር ወጣቶች ላይ እየሰራ ያለው ሥራ ወቅቱን የጠበቀና ጊዜውን የሚመጥን መሆኑን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው ሰልጣኝ ወጣቶች በቆይታቸው የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት ገልጸዋል።

በዚህ መርሃ ግብር ላይ የምስራቅ ጎጃም ዞን የሰላምና ፀጥታ መምሪያ ምክትል መምሪያ ኃላፊ አቶ ላቃቸው አብጠው የተገኙ ሲሆን የሰላም ሚኒስቴር እየሰራ ያለው መልካም ተግባር እንደሆነ ተናግረው ሰልጣኞች በደብረ ማርቆስ ከተማና በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ያለምንም ችግር ስልጠናቸውን አጠናቅቀው እንዲመለሱ አብረን በተባባሪነት እንሰራን ሲሉ ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ በሰላም ሚኒስቴር በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሚኒስትር ዋና አማካሪ አቶ ካይዳኪ ገዛኸኝ እንደተናገሩት በጎ ፈቃደኝነት ያለ ማንም ግፊት በራስ ተነሳሽነት የሚፈፀም የህሊና እርካታ የሚሰጥ ተግባር መሆኑን ገልፀው "በጎነት ለአብሮነት" በሚል የተዘጋጀው መርሃግብር አንዱ የሌላውን እሴት እንዲያውቅና እርስ በእርስ በመጋመድ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት የሚያግዝ ፕሮግራም እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

አቶ ካይዳኪ አክለውም በዚህ ፕሮግራም ተሳታፊ የሆናችሁ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ያለውን መከፋፈልና ጥርጣሬ በማስወገድ ሃገራዊ አንድነትን ለማጠናከር የጎላ ሚና ያላችሁ በመሆኑ የሚሰጠውን ስልጠና በብቃትና ስነምግባር በተሞላበት መልኩ በመከታተል ሀገራዊ ሃላፊታችሁን ልትወጡ ይገባል ብለዋል ፡፡

በአምስተኛው ዙር የብሔራዊ የበጎ ፈቃድ የማህበረሰብ ልማት አገልግሎት ፕሮግራም በአምስት ዩኒቨርስቲዎች ከ10ሺህ በላይ ወጣቶች ስልጠናቸውን የሚከታተሉ ሲሆን በዛሬው ዕለት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ 1ሺህ ሰልጣኞች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ከዚህ በፊት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ለበጎ ፈቃደኞች ስልጠናው የተሰጠ መሆኑ ይታወሳል።