Get Mystery Box with random crypto!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሰርጥ አድራሻ: @debre_markos_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 26

2022-10-08 08:19:17
ለፈተና የመጣችው ተማሪ ሴት ልጅ በሰላም ተገላገለች

=========

በ26/ዐ1/2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመፈተን ከቢቡኝ ወረዳ ወደ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የገባችው ተማሪ ሴት ልጅ በሰላም ተገላገለች።

ከሌሊቱ 9:00 ላይ ከዩኒቨርሲቲ ወደ ደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል በዩኒቨርሲቲው አምቡላንስ የገባችው ተማሪ መታደል እንዳላማው በዛሬው ዕለት ማለትም በ28/01/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 1:00 አካባቢ ሴት ልጅ በሰላም ተገላግላለች ።

በዚህ አጋጣሚ ለተማሪዋ ቤተሰቦች በአሁኑ ስዓት እናት ከእነ ልጇ በሙሉ ጤንነት ላይ መሆናቸውን እየገለፅን ዩኒቨርሲቲያችን አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ እያደረገ መሆኑንም እናሳስባለን።

Website www.dmu.edu.et

Telegram https://t.me/Debre_Markos_University

Facebook https://www.facebook.com/dmu.edu

Youtube https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

Twitter
https://twitter.com/dmu_ethiopia

Instagram https://www.instagram.com/dmu_ethiopia/

Linkedin https://www.linkedin.com/in/dmu-ethiopia/

"Grow Wiser as the Water Tower!"

Thank you for being with us
893 views05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 15:30:03 ተፈታኞቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ !

==============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 26/2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የተመደቡለት ቢሆንም እንደነዚህ አይነት ወሳኝ ሀገራዊ ግዴታዎችን በጥንቃቄ እና በታላቅ የኃላፊነት ስሜት የማከናወን ብቃት ያለው ዩኒቨርሲቲያችን ከላይ እስከ ታች ያሉ የዩኒቨርሲሲቲው አመራሮችና ሁሉም የግቢው መምህራንና ሰራተኞች በመናበብ ባደረግነው ሰፊና ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ርብርብ እነሆ በዛሬው ዕለት ተፈታኝ ተማሪዎቻችንን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበልን እንገኛለን።

በአሁኑ ስዓት #ከቢቡኝ፣ #ከእነማይ፣ #ከደባይ_ጥላት_ግን እና #ከሸበል_በረንታ ወረዳዎች ተማሪዎች በሰላም እየገቡ መሆኑን እንገልፃለን።

ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግቢያ በር በምትደርሱበት ስዓት የጥበቃ ፍተሻውን እንዳለፋችሁ ፊት ለፊት የመረጃ መስጫ ማዕከል ( information desk) የተዘጋጀ ስለሆነ ግልፅ ያልሆነላችሁን ማንኛውንም ነገር መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን!

በደጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ !

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!
2.5K views12:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 15:29:53
2.3K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-06 15:29:44
2.4K views12:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-05 14:11:33
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ #ዋናው_ግቢ የተመደባችሁ ተማሪዎች #የምኝታ አገልግሎት የምታገኙበት ህንፃ ቁጥር የሚያሳይ ሰንጠረዠ!
678 views11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:17:32
1.1K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:17:28
1.1K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:17:23
1.1K views19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:11:38 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን እየገለፅን ውድ ተፈታኞቻችን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በሰላም እንድትገቡ ከወዲሁ ምኞታችንን እንገልፃለን!

በእኛ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለምትፈተኑ ተማሪዎች በሙሉ ከታች የተዘረዘሩት የመፈተኛ መለያ ቁጥራችሁ፣የህንፃ ቁጥር ፣ የፎቅ(ወለል) ቁጥር እና የመፈተኛ ክፍል ቁጥር በትክክል የተጠቀሰ ስለሆነ ወደ ግቢ ስትገቡ እነዚህን ከታች የዘረዘርናቸውን አቅጣጫ ጠቋሚዎች ያስቀመጥንላችሁ በመሆኑ የመፈተኛ ክፍላችሁን ለማግኘት የማትቸገሩ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ተፈታኞች መልካም ዕድል!

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!
1.2K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 22:11:28
1.1K views19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ