Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ተቀብሎ ለማስተና | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን እየገለፅን ውድ ተፈታኞቻችን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በሰላም እንድትገቡ ከወዲሁ ምኞታችንን እንገልፃለን!

በእኛ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ ለምትፈተኑ ተማሪዎች በሙሉ ከታች የተዘረዘሩት የመፈተኛ መለያ ቁጥራችሁ፣የህንፃ ቁጥር ፣ የፎቅ(ወለል) ቁጥር እና የመፈተኛ ክፍል ቁጥር በትክክል የተጠቀሰ ስለሆነ ወደ ግቢ ስትገቡ እነዚህን ከታች የዘረዘርናቸውን አቅጣጫ ጠቋሚዎች ያስቀመጥንላችሁ በመሆኑ የመፈተኛ ክፍላችሁን ለማግኘት የማትቸገሩ መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

ተፈታኞች መልካም ዕድል!

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!