Get Mystery Box with random crypto!

ተፈታኞቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ ! ============== ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ተፈታኞቻችን እንኳን ደህና መጣችሁ !

==============

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ መስከረም 26/2015 ዓ.ም ( ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የተመደቡለት ቢሆንም እንደነዚህ አይነት ወሳኝ ሀገራዊ ግዴታዎችን በጥንቃቄ እና በታላቅ የኃላፊነት ስሜት የማከናወን ብቃት ያለው ዩኒቨርሲቲያችን ከላይ እስከ ታች ያሉ የዩኒቨርሲሲቲው አመራሮችና ሁሉም የግቢው መምህራንና ሰራተኞች በመናበብ ባደረግነው ሰፊና ጠንካራ የቅድመ ዝግጅት ርብርብ እነሆ በዛሬው ዕለት ተፈታኝ ተማሪዎቻችንን በደማቅ ሁኔታ እየተቀበልን እንገኛለን።

በአሁኑ ስዓት #ከቢቡኝ፣ #ከእነማይ፣ #ከደባይ_ጥላት_ግን እና #ከሸበል_በረንታ ወረዳዎች ተማሪዎች በሰላም እየገቡ መሆኑን እንገልፃለን።

ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መግቢያ በር በምትደርሱበት ስዓት የጥበቃ ፍተሻውን እንዳለፋችሁ ፊት ለፊት የመረጃ መስጫ ማዕከል ( information desk) የተዘጋጀ ስለሆነ ግልፅ ያልሆነላችሁን ማንኛውንም ነገር መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ለማሳሰብ እንወዳለን!

በደጋሚ እንኳን ደህና መጣችሁ !

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!