Get Mystery Box with random crypto!

የተወደዳችሁ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂዎች ፣ ይህ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የተወደዳችሁ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተመራቂዎች ፣ ይህ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የተከፈተ ይፋዊ የዩኒቨርሲቲያችን የቀድሞ ተመራቂ ተማሪዎች ማህበር ቡድን ( Debre Markos University Alumni Association Group ) መሆኑን ስንገልፅላችሁ በደስታ ነው። ይህ ግሩፕ ከቀድሞ ተራቂዎቻችን ጋር ግንኙነት ለመፍጠርና መረጃዎችን ለመለዋወጥ እንድንችል ታስቦ የተከፈተ ግሩፕ ነው።

በመሆኑም በየትኛውም አመተ ምህረት፣ በማንኛውም መርሃ ግብር በዩኒቨርሲቲያችን ተመርቃችሁ በስራ ዓለም ላይ ያላችሁም ሆነ ስራ ለመቀጠር በመፈለግ ላይ የምትገኙ ወይም የራሳችሁን ስራ ፈጥራችሁ እየሰራችሁ ያላችሁ ሁሉ የዚህ ቡድን አባላት መሆን የምትችሉ ስለሆነ ወደ ግሩፑ እንድትቀላቀሉ በአክብሮት እንጋብዛለን።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ( ነሐሴ ፦ 12/2014 ዓ.ም )

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ !

ግሩፑን ለመቀላቀል ከታች ያስቀመጥነውን ሊንክ ይጫኑ



https://www.facebook.com/groups/604704201179469/

https://t.me/dmu_pralmuni2014