Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲከፍተኛ አመራሮች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ትምህርት | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲከፍተኛ አመራሮች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን የስራ እንቅስቃሴ ጎበኙ

=============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 24/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |

የደብረ ማረቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር)፣ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት ይኸይስ አረጉ (ዶ/ር) እና የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አስካለ ማርያም አዳሙ (ዶ/ር) እንዲሁም ከአማራ ክልልና ከደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የትምህርት መምሪያ ሃላፊዎች በተገኙበት የተክለሃይማኖት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤትና ኢትዮ ጃፓን ደብረ ማርቆስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ትምህርታዊ ጉብኝት አካሄዱ፡፡

በዚህ መርሃ ግብር በትምህርት ቤቶቹ ግቢ ውስጥ የሚገኙ አረንጓዴ ተክሎች ፣ ቤተ-ሙከራ ክፍሎች፣ የፈጠራ ስራዎች፣ የመረጃ አደረጃጀቶች፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርትና ስልጠና እና ድጋፍ አሰጣጥቶች እና እንዲሁም የምርምር ማዕከላት ተጎብኝተዋል።


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲና የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ልዩ ተግባራት በትብብር እየሰሩ እንደሆነ የዛሬው የጉብኝት መርሃ ግብር አመላካች ነው።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ


=============

ለተጨማሪ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q