Get Mystery Box with random crypto!

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ምሁራዊ የፖለቲካ ገለልተኝነት እንዳለ ተጠቆመ ======== | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

አሁን ባለው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ምሁራዊ የፖለቲካ ገለልተኝነት እንዳለ ተጠቆመ

================

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 27/2015 ዓ.ም| ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኔኬሽን ዳይሬክቶሬት |

በደብረ ማርቆስ ዪኒቨርስቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትም/ክፍል "#በአሁኗ_ኢትዮጵያ_ፖለቲካዊ_ተሳትፏችን_ምን _መምሰል_አለበት?" በሚል መሪ ሃሳብ ትምህረተ ጉባኤ አካሂደ፡፡

በትምህርተ ጉባኤው ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይኸይስ ሐረጉ አሁን የገጠመንን ችግር ለመጋፈጥ ልዩነቶቻችንን ወደ ጎን በመተው አንድነታችንን ማጠናከር ፤ የፖለቲካ አመራሮችን ቀርበን ማስተማርና ክፍተቶቻቸውን መሙላት እና ምሁራን እና አመራሮች ጠላቶቻችንን በጋራ መታገል እና ለመጪው ትዉልድ ሲባል መስዕዋትነት መክፈል እንደሚገባ ገልፀዋል። አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ምሁራዊ የፖለቲካ ገለልተኝነት እንዳለና ምሁራን ያገባኛል በሚል ስሜት ፖለቲከኞችን ቀርቦ ማገዝ እንዳለባቸውም ጨምረው ጠቁመዋል።

"#በአሁኗ_ኢትዮጵያ_ፖለቲካዊ_ተሳትፏችን_ምን _መምሰል_አለበት?" በሚል መሪ ሃሳብ ፅሁፋቸውን ያቀረቡት የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትም/ክፍል መምህር ዶ/ር መኮንን አለኸኝ፦
* የምሁራን ፓለቲካዊ ተሳትፎ አናሳ መሆኑን፤
* የአንድነትና የመለያየት ሃይሎች ትልቅ ትግል እያደረጉባት ያለች ሀገር መሆኗን
* ከ1960ዎቹ ጀምሮ ያለው የፖለቲካ ችግር የመደብ ወይስ የብሔር የሚለው ጥያቄ ያልተለየበት መሆኑን
* በኢትዮጵያ ፖለቲካ የምዕራባውያን ጫና ጎልቶ የሚታይበት መሆኑን፤
* የውጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ግልጽ አለመሆኑን፤ እና
* የፖለቲካ ተሳትፎን ጠንቅቆ ያለመረዳትና የመለየት ችግሮች በጉልህ መልኩ እንደሚስተዋሉ
* አለማቀፋዊ የሆኑ የፖለቲካ ጫናዎች እንደሚስተዋሉ በሰፊው በመግለፅ የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦችም ጠቁመዋል።

* የፖለቲካ ፖርቲዎች ተሳትፎቸውን ማሳደግ እንደሚገባ
* የመንግሥት ባለሥልጣናት እና ምሁራን ተቀራርቦ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ፤
* ስለ አገራችን ወቅታዊ ሁኔታ በቂ መረጃና ግንዘቤ መያዝ እንደሚገባ ፤
* ማንኛውም ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች መደገፍ እንደሚገባን እና በግል ወይም በቡድን ፖለቲካዊ ተሳትፎአችንን ማጠናከር እንደሚገባ በመግለፅ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል ።

በመጨረሻም በቀረበው መነሻ ፅሁፍ ላይ ሰፊና ጥልቅ ወይይት ተደርጎበት ትምህረተ ጉባዔው ተጠናቋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች



#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q