Get Mystery Box with random crypto!

127ኛው የአደዋ ድል በዓል መታሰቢያ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ በ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

127ኛው የአደዋ ድል በዓል መታሰቢያ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሐዲስ ዓለማየሁ የጉባዔ አዳራሽ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ተከበረ

==============
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 23/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |

"አንድነት፣ ጀግንነትና ጽናት" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዚህ በዓል የምስራቅ ጎጃም ዞን የስራ ኋላፊዎቸ ፣ የደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር እና የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና ተማሪዎች እና እንዲሁም የዩኒቨርስቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተሳትፈውበታል።

የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ በንግግራቸውም ከአድዋ ጀግኖች የተማርነው ርህራሄ ፣ የአመራር ጥበብ፣ የአንድነት መንፈስ ፣ ነፃነትና እኩልነትን መሆኑን ጠቁመው የአሁኑ ትውልድ የጀግኖች አባቶቹን ፈለክ መከተል እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ረ/ፕሮፈሰር ግዛቸው አንዳርጌ የዓድዋ ድልን በተመለከተ ከመነሻ እስከ ፍፃሜው የነበረውን ታሪካዊ ሁነት የሚያስቃኝ የውይይት ሰነድ አቅርበዋል።
እንደ ተመራማሪው ገለፃ የካቲት ወር ለኢትዮጵያ በጣም በብዙ ነገር ታሪካዊ ወር እንደሆነ የታሪክ መዛግብቶችና ድርሳናት እንደሚያመላክቱ ጠቁመዋል። ይካቲት 12 ግራዚያኒ አዲስ አበባ ላይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ የፈጸመበት ወቅት በመሆኑ ፤ ይካቲት 23 ደማቁን ያአደዋ ድል ያስመዘግንበት መሆኑ ፤ የካቲት 26 ወራሪው የዚያድባሬ ጦር በካራ ማራ ላይ ድል ተደርጎ የተመለሰበት ወር መሆኑን ለአብነት ጠቅሰው ባጠቃላይ የካቲት ወር የኢትዮጵያ ትንሳዔ ወር ነው ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ይኸይስ አረጉ የበዓሉን የመዝጊያ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም የዓድዋ ዘመን ጀግኖች እነሱ ለማይኖሩበት ዓለም መስዋዕትነት ከፍለውልን እኛ በነፃነት እንድንኖር አስችለውናል። በመሆኑም የታሪክ ምሁራን ከታሪክ ተጠያቂነት ለመዳን ወጣቱን ትውልድ መቅረፅ ፣ እውነትን መመስከር ፣ ማስተማርና ማንቃት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። ከትውልዱ ደግሞ ደፍሮ መማር እና ማወቅ ፣ የአድዋን ዘመን ጀግኖች መንፈስ መላበስ እንደሚጠበቅ በአንክሮ ገልፀዋል።


ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ


=============

ለተጨማሪ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q