Get Mystery Box with random crypto!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሰርጥ አድራሻ: @debre_markos_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-04-28 14:11:54 የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ እና በጎዛምን ወረዳ የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር በመተባበር የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ ስልጠና ሰጠ

======

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | ሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት|የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ከደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለፈንደቃ፣ ሊባኖስ፣ ጎዛምን፣ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል፣ ውሰታ፣ ደብረ ማርቆስ ከተማ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራናህክምና መስጠት ሙያ ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ት/ቤት የማህጸንና ጽንስ ትምህርት ክፍል የማህጸንናጽንስ እስፔሻሊስትና መምህር ምናልባት አበበ (ዶ/ር) እንደገለጹት የማህጸን በር ካንሰር ከእናቶች ካንሰር ከፍተኛውን ቁጥር የያዘውና መከላከልና ህክምና ያለው የካንሰር አይነት መሆኑን ጠቁመው ቅድመ ካንሰር ልየታ በማድረግና በማከም በሽታው የመከሰት እድሉን መቀነስ እንደሚቻል ገልፀዋል።

ስልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ጤና ጣቢያዎች ተመርጠው ለመጡ የአዋላጅ ነርስ ባለሙያዎች ሲሆን ከሰልጣኞች የሚጠበቀው የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ እንዲያደርጉና የተለዩትንም ህክምና መስጠት እንዲችሉና ከአቅማቸው በላይ የሆኑትን ወደ ሌላ ጤና ተቋም በሪፈር እንዲልኩ ለማስቻል መሆኑንም ጨምረው አብራርተዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ መንግስቱ ዘላለም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ፣ ቅድመ መከላከል እና ህክምና መስጠት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኑርልኝ አበበ (ዶ/ር) ከዩኒቨርሲቲው ተልኮዎች ውስጥ አንዱ በማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆኑን ጠቅሰው የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ መከላከልናእንክብካቤ ላይ እንደሆነም ገልፀዋል።

ስልጠናውን የወሰዱ የጤና ባለሙያዎች ወደመጡበት ሲመለሱ ከዚህ በፊት ከሚሰሩት በበለጠ እንዲሰሩና ለውጥ እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው ከ16- 19 /2015 ዓ.ምለተከታታይ አራት ቀናት የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

#ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቱዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
4.5K viewsedited  11:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 18:41:26
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1444ኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
3.2K views15:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 08:11:37
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ


===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
3.2K viewsedited  05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 19:50:54
የሐዘን መግለጫ
========
በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ በእፅዋት ትምህርት ክፍል መምህር የነበሩት አቶ አግሟስ አስራት ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 29/2015 ዓ.ም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። አቶ አግሟስ አስራት ባለትዳርና የሶስት ልጆች አባትም ነበሩ ።

በባልደረባችን ሞት የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እየገለፅን ለመላው ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ሁሉ ልባዊ መፅናናትን እንመኛለን።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
4.3K views16:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:36:21 ከአዲስ መደበኛ እና ሪሚዲል ሴት ተማሪዎች ጋር በኤች.አይ.ቪ ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ

==================

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 29/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት| በዩንቨርሲቲው የስርዓተ ፆታ፣ኤች.አይ.ቪ ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክቶሬት ለአካል ጉዳተኞችና ሴት ተማሪዎች ስልጠናና ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዛሬው ዕለትም ሴት ተማሪዎች ግቢ ህይወት ሳያታልላቸው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ለማስቻል የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የስርዓተ ፆታ፣ኤችአይቪ ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም መክብብ ከሴት ተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረግ ያስፈለገው ተማሪዎች ከቤተሰብ እርቀው ሲኖሩ በአላስፈላጊ ነገሮች እንዳይታለሉና ከተለያዩ በሽታዎች ራሳቸውን ጠብቀውና የአቻ ግፊቶችን ተቋቁመው ጤናማ፣ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው ለስኬት እንዲበቁ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪ ብርቱካን ላቃቸው ከእኛ የሚጠበቀው ጠንክረን አንብበን ውጤታችንን ማሻሻል ሲሆን ነገርግን ዩንቨርሲቲ ሲባል እንደ ነፃነት ቦታ በመቁጠር ትምህርትን ችላ የማለት ዝንባሌ ይታያል፡፡ ይህ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱም መልካምና መጥፎ ጉዳዮች ላይ ተወያይተን የሚያስፈልገንን ብቻ ለይተን በማወቅ ስኬታማ እንድንሆን ያስችለናል ስትል ገልፃለች፡፡

ተማሪ ያለምወርቅ ሰውነት ውይይቱ እንዳንዘናጋና ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ትምህርታችን ላይ የበለጠ ትኩረት እንድናደርግ የሚያስችል በመሆኑ ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብላለች፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
2.5K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:35:28
2.4K views07:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:21:48
#NEW_Vacant-Positions
2.6K views07:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:44:44 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ

===============

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 22/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በቡሬ ካምፓስ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ባለድርሻና አጋር አካላት በተገኙበት የውይይት ተካሄደ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ብርሃኑ አለሙ (ዶ/ር) የእንኳን ድህና መጣችሁ መልዕክት ከአስተላለፉ በኋላ እንዳሉት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ እንዲሁም ዩኒየኖች ጋር በመተባበር የቡሬ ካምፓስን አቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ቡሬ ከተማ ውስጥ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመኖሩ እንዱስትሪዎች ወደ ከተማዋ እየመጡ በመሆኑ ይህን ጸጋ በአግባቡ ለመጠቀም መተባበር፣ መረዳዳትና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመርሃ - ግብሩ መግቢያ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አስካለማርያም አዳሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ እንደ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተቋም ራዕዩንና ተልዕኮውን እውን ሊያደርግ የሚችለው ከተቋማት ጋር በጋራ መስራት ሲችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


ይህንም ተግባር ዩኒቨርሲቲው በአስር አመቱ እስትራቴጅክ እቅድ አንድ ተተኳሪ ተግባር አድርጎ ወደ ስራ መግባቱንም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንቷ አክለው ገልፀዋል፡፡

ረዳት ፕሮፊሰር ደምሳቸው ሽታው የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር እንደገለጹት በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ወደ ስራ የገቡ ፕሮጀክቶችን ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቡሬ ግቢ- የዶሮ እርባታ፣ ንብ እርባታ፣ የወተት ልማት አትክልትና ፍራፍሬ፣ አቦካዶ በ1.8 ሄክታር መሬት 365 የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ መድሃኒታማ ዕጽዋት ፣ ግቢውን የማስዋብ ስራ፣ የሙዝ ተክል፣ ሻይ ቅጠል ተክል መሆናቸውን የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ብርሃኑ አለሙ (ዶ/ር) በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ሴቶችና ህፃናት ቢሮ፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ባህል ቱሪዝም፣ አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ፣ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጥምረት እንደሚሰሩ ቢሮ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ገልፀዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
3.0K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:44:22
2.5K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 11:44:24
2.8K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ