Get Mystery Box with random crypto!

ከአዲስ መደበኛ እና ሪሚዲል ሴት ተማሪዎች ጋር በኤች.አይ.ቪ ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች ዙሪያ ውይይ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ከአዲስ መደበኛ እና ሪሚዲል ሴት ተማሪዎች ጋር በኤች.አይ.ቪ ኤድስና ተዛማጅ በሽታዎች ዙሪያ ውይይት ተደረገ

==================

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 29/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት| በዩንቨርሲቲው የስርዓተ ፆታ፣ኤች.አይ.ቪ ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክቶሬት ለአካል ጉዳተኞችና ሴት ተማሪዎች ስልጠናና ልዩ ልዩ ድጋፎችን እያደረገ ይገኛል፡፡ በዛሬው ዕለትም ሴት ተማሪዎች ግቢ ህይወት ሳያታልላቸው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ለማስቻል የምክክር መድረክ አካሂዷል፡፡

የስርዓተ ፆታ፣ኤችአይቪ ኤድስና አካል ጉዳተኞች ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላም መክብብ ከሴት ተማሪዎች ጋር ውይይት ማድረግ ያስፈለገው ተማሪዎች ከቤተሰብ እርቀው ሲኖሩ በአላስፈላጊ ነገሮች እንዳይታለሉና ከተለያዩ በሽታዎች ራሳቸውን ጠብቀውና የአቻ ግፊቶችን ተቋቁመው ጤናማ፣ብቁና ተወዳዳሪ ሆነው ለስኬት እንዲበቁ ለማስቻል ነው ብለዋል፡፡

የሪሚዲያል ተማሪ ብርቱካን ላቃቸው ከእኛ የሚጠበቀው ጠንክረን አንብበን ውጤታችንን ማሻሻል ሲሆን ነገርግን ዩንቨርሲቲ ሲባል እንደ ነፃነት ቦታ በመቁጠር ትምህርትን ችላ የማለት ዝንባሌ ይታያል፡፡ ይህ የውይይት መድረክ መዘጋጀቱም መልካምና መጥፎ ጉዳዮች ላይ ተወያይተን የሚያስፈልገንን ብቻ ለይተን በማወቅ ስኬታማ እንድንሆን ያስችለናል ስትል ገልፃለች፡፡

ተማሪ ያለምወርቅ ሰውነት ውይይቱ እንዳንዘናጋና ቅድመ ጥንቃቄ በማድረግ ትምህርታችን ላይ የበለጠ ትኩረት እንድናደርግ የሚያስችል በመሆኑ ይህን ፕሮግራም ላዘጋጁት አካላት ምስጋና ይገባቸዋል ብላለች፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et