Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ እና በጎዛምን ወረዳ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ውስጥ እና በጎዛምን ወረዳ የጤና ተቋማት ውስጥ አገልግሎት በመስጠት ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች ከደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር በመተባበር የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራ ስልጠና ሰጠ

======

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | ሚያዚያ 20/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት|የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ጤና ካምፓስ ከደብረ ማርቆስ ሪፈራል ሆስፒታል ጋር በመተባበር ለፈንደቃ፣ ሊባኖስ፣ ጎዛምን፣ ደብረ ማርቆስ ሆስፒታል፣ ውሰታ፣ ደብረ ማርቆስ ከተማ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ምርመራናህክምና መስጠት ሙያ ላይ ስልጠና ሰጠ፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ት/ቤት የማህጸንና ጽንስ ትምህርት ክፍል የማህጸንናጽንስ እስፔሻሊስትና መምህር ምናልባት አበበ (ዶ/ር) እንደገለጹት የማህጸን በር ካንሰር ከእናቶች ካንሰር ከፍተኛውን ቁጥር የያዘውና መከላከልና ህክምና ያለው የካንሰር አይነት መሆኑን ጠቁመው ቅድመ ካንሰር ልየታ በማድረግና በማከም በሽታው የመከሰት እድሉን መቀነስ እንደሚቻል ገልፀዋል።

ስልጠናው የተሰጠው ከተለያዩ ጤና ጣቢያዎች ተመርጠው ለመጡ የአዋላጅ ነርስ ባለሙያዎች ሲሆን ከሰልጣኞች የሚጠበቀው የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ እንዲያደርጉና የተለዩትንም ህክምና መስጠት እንዲችሉና ከአቅማቸው በላይ የሆኑትን ወደ ሌላ ጤና ተቋም በሪፈር እንዲልኩ ለማስቻል መሆኑንም ጨምረው አብራርተዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ መንግስቱ ዘላለም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ከሚሰራቸው ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ ልየታ፣ ቅድመ መከላከል እና ህክምና መስጠት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ካምፓስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ኑርልኝ አበበ (ዶ/ር) ከዩኒቨርሲቲው ተልኮዎች ውስጥ አንዱ በማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆኑን ጠቅሰው የማህጸን በር ካንሰር ቅድመ መከላከልናእንክብካቤ ላይ እንደሆነም ገልፀዋል።

ስልጠናውን የወሰዱ የጤና ባለሙያዎች ወደመጡበት ሲመለሱ ከዚህ በፊት ከሚሰሩት በበለጠ እንዲሰሩና ለውጥ እንዲያስመዘግቡ አሳስበዋል፡፡

ስልጠናው ከ16- 19 /2015 ዓ.ምለተከታታይ አራት ቀናት የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ!

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች


#ቴሌግራም፡ https://bit.ly/3HbDPCB

#ፌስቡክ፡ https://bit.ly/3mYfnNW

#ዩቱዩብ፡ https://bit.ly/3L73hu3

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et