Get Mystery Box with random crypto!

Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ D
የቴሌግራም ቻናል አርማ debre_markos_university — Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
የሰርጥ አድራሻ: @debre_markos_university
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.90K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴሌግራም ገጽ ነው። የዩኒቨርሲቲያችን ወቅታዊ መረጃዎች፣ ልዩ ልዩ ሁነቶች እና የስራ እና የትምህርት ማስታወቂያዎች ይተላለፉበታል። አሁንኑ ቤተሰብ ለመሆን ይቀላቀሉ!!
This is Our Official Telegram Channel. We Provide up-to-date Information about our University.
Join Us Now!🙏

Ratings & Reviews

4.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-03-30 15:06:30 የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ለአዲስ መደበኛ እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ

==============

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 22/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶች እና ኤች .አይ.ቪ /ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ስለ ጊዜ አጠቃቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ፡፡

በስልጠና መረሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች ንግግር ያደረጉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶችና ኤች .አይ.ቪ / ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት የስረዓተ ጾታ ባለሙያ ወ.ሮ አጸደ ወንድሙ እንደተናገሩት አዲስ መደበኛ እና ሪሚዲያል ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው አዲስ እንደመሆናቸው መጠን ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ፡፡

ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ጊዜያቸውን ባግባቡ መጠቀም ፣ ከጭንቀትና ከፍረሃት ነፃ ሆነው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፡፡


ሀሳባቸውን የሰጡት ተማሪ ውባየሁ አስራትና ናርዶስ ፀጋዬ እስካሁን እንዲህ አይነት ስልጠና ከዚህ በፊት አለማግኘታቸውን ገልፀው በስልጠናው ላይ በመጋበዛቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

የተሰጣቸውን ስልጠናም በአግባቡ ተግባር ላይ ለማዋልና ጊዜያቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ቁርጠኛ እንደሆኑም ጠቁመዋል። ጊዜያቸውንም አልባሌ ቦታ ከማሳለፍ ይልቅ ቤተ መጸሐፍት በመግባት ፣ ከጓደኞቻቸው ጋር በትምህርታቸው ዙሪያ በመጠያየቅ ፤ መምህራኖቻቸውን በመጠየቅ ፤ መደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜያትን ባለመሸራረፍ እና በአግባቡ በመከታተል አላማቸውን ዕውን ማድረግ እንዳለባቸውና ቤተሰቦቻቸውና ሀገር የጣለችባቸውን አደራ ማሳካት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ልምዷን ለተማሪዎች ያካፈለችው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት የሲቨል ምህንድስና ተማሪ ተስፋነሽ አምሳሉ እንደገለጸችው በዩኒቨርሲቲው በቆየችባቸው ዓመታት እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎችን ስትከታተል መቆየቷንና በህይወቷም በርካታ ጥቅሞችን ማግኘቷን ገልጻ ተማሪዎች እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎችንና ውይይቶችን በአግባቡ በመከታተል ተግባር ላይ እንዲያውሉት አሳስባለች ፡፡

ተማሪዎች ማድረግ ያለባቸውን ነገር አሁን ማድረግ እንዳለባቸው ነገር ግን ጊዜው ካለፈ በኋላ መፀፀት ተገቢ አይደለም ያለችው ተስፋነሽ መሆን የሚፈልጉትን ፣ ህልማቸውንና እቅዳቸውን ለማሳካት ከአሁኑ ጊዜያቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ስትልም ምክራን ለግሳለች ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
2.4K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:06:09
2.3K views12:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 14:51:54 የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ‹‹ የአባይ ዘመን ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የመጡ እንግዶች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ መምህራንናሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች በተገኙበት የስነ-ጽሁፍ ምሽት አካሄደ

===========

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 20/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
በመርሃ- ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር ) እንዳሉት ትልቁን የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ትልቁ የደም ስር የጮቄ ተፋሰስ በእኛ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ፀጋችን መሆኑን ጠቅሰው በታሪክ አጋጣሚ በአጼ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት አርቆ አሳቢነት የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዲገደብ ማስተር ፕላን ያሰሩና ማስተር ፕላኑም በታሪክ አጋጣሚ እኛ እጅ ላይ የደረሰ በመሆኑ ድርሻችንን የመወጣት ግዴታ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

ፕሬዚደንቱ አክለውም እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአዲሱ ትውልድ ብሄራዊ አርማና ተስፋ እንደሆነና ኢትዮጵያ ዛሬ ካለችበት የድህነት አረንቋ ትላቀቃ ከሌሎች አገሮች እኩል ትራመዳለች ተብሎ የሚታሰበው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚፈጥረው የልማት ተስፋ ስለሆነና የአዲሱ ትውልድ የብሩህ ተስፋ ነጸብራቅ በመሆኑ ልንጠብቀው፣ ልንከባከበውና ዳር ልናደርሰው ሃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ተካ በበኩላቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብዙ መሰናክሎችን አልፎ ከፍተኛ እምርታ የታየበትና 88 % በመቶ የደረሰበት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ሲሉ ንግግራቸውን ጀምረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የይቻላልን መንፈስ በማንገብ መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲሰለፉ ያደረገ በመሆኑ የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብቱን ፍትሃዊና በእኩልነት የመጠቀም መርህን በተግባር በማሳየት ጭምር አዲስ የትብብር ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል፡፡

ከግድቡ ግዙፍነት ባሻገር በራስ አቅም የመልማትና የማደግ እሳቤን ለእኛ ኢትዮጵያውን ፣ ለአፍሪካዊያን እና እንዲሁም ለዓለም ያስተዋወቀ ግድብ መሆኑንም አክለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ 12ኛ ዓመት ክብረ በዓል "ታላቁ ህዳሴ ግድብና ሴቶች" በሚል የፓናል ውይይት እየተከበረ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

የአባይ ዘመን የስነ-ጽሁፍ ምሽት የታላቁ ህዳሴ ግድብ 12ኛ ዓመት አከባበር አንዱ አካል ሲሆን አላማው ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለኪጥበብ ያለው ተምሳሌታዊ ተግባርን ለማሳየት፣ የግድቡ ቱርፋት የሆነውን "የይቻላል" መንፈስ ለተማሪዎች ፣ ለወጣቶች እንዲሁም በጠቅላላው ለትውልዱ ለማስረጽ እና የግድቡንም ስራ ለማጠናቀቅ የሚደረግ ጥረት ነው ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ክብረ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ ደራሲያን ግጥሞችንና የኪነ ጥበብ ስራዎቻቸውንም አቅርበዋል፡፡

ዲፕሎማት ዘሪሁን አበበ -ኪናዊ ዲፕሎማሲ
በ (ዶ/ር) አንዱአለም አባተ "ልጅ ለሚወርሰው" በሚል ርዕስ በ(ዶ/ር) ገዛኽኝ ፀጋው "የአባይ አብ ህዝብና የአባይ ምት እንደ ግጥም ቤት ስም" በሚል ርዕስ
አገኘሁ አዳነ (የስነ-ስዕልና ስነ-ጽሁፍ መምህር "ብሄራዊ ምስል ኪናዊ አንድምታ" በሚል ርዕስ
ማርታ ቶሎሳ "ሰላም ለኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ " ፍለጋ " ባለ አንድ ገቢር ቴአትር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ቀርበዋል፡፡

በመጨረሻም ከዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) አቶ ሰለሞን ተካ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ በተገኙበት የስነ-ግጥም ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

1ኛ- ተማሪ ያብስራ ፀጋየ "ቁርጥ እኔ ቁርጥ እኛ"

2ኛ- ተማሪ አብርሃም እባቤ "አንተ ጥቁር ካህን"

3ኛ- በህይወት ዮሴፍ "ያው ደሞ አባይ" በሚሉ አርዕስት በፃፏቸው የስነ ፅሑፍ ስራዎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ተሸልመዋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

==================
ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
1.6K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-29 14:51:07
1.6K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-27 10:59:46
ለተጨማሪ መረጃዎች

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
460 views07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 10:39:58 ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ የ2015ዓ.ም 4ኛው ዙር የተማሪዎች አምባሳደር ሊስት ማዕረግ የእውቅናና የሽልማት ስነ ስረዓት የዩኒቨርሲቲያችን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚደንትን ጨምሮ የካምፓሱ ከፍተኛ አመራሮች እና ሌሎችም ሀላፊዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የአካባቢው ማህበረሰብ በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
2.2K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-26 10:39:51
2.2K viewsedited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:38:50 የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ 4ኛው ዙር የ2015ዓ.ም የተማሪ አምባሳደር ሊስት የእዕውቅና ሽልማት መረሐ ግብር በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ይገኛል።

በዚህ የሽልማትና የእውቅና ፕሮግራም ላይ ከፌደራል መንግስት የመጡ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው እና የአካባቢው ማህበረሰብ ተገኝተዋል።

በዚህ መርሐ ግብር 3.75 እና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ በአጠቃላይ 247 ተማሪዎች ከዋናው ግቢና ከጤና ካምፓስ ሽልማትና እውቅና ይሠጣቸዋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

==========
ለተጨማሪ መረጃዎች

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et
2.9K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:38:21
2.8K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 10:38:18
2.8K views07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ