Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ‹‹ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ‹‹ የአባይ ዘመን ትውልድ›› በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ የመጡ እንግዶች፣ የኪነጥበብ ባለሙያዎች፣ መምህራንናሰራተኞች እንዲሁም ተማሪዎች በተገኙበት የስነ-ጽሁፍ ምሽት አካሄደ

===========

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 20/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |
በመርሃ- ግብሩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር ) እንዳሉት ትልቁን የምስራቅ አፍሪካ የውሃ ማማ እና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ትልቁ የደም ስር የጮቄ ተፋሰስ በእኛ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ፀጋችን መሆኑን ጠቅሰው በታሪክ አጋጣሚ በአጼ ሀይለ ስላሴ ዘመነ መንግስት አርቆ አሳቢነት የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንዲገደብ ማስተር ፕላን ያሰሩና ማስተር ፕላኑም በታሪክ አጋጣሚ እኛ እጅ ላይ የደረሰ በመሆኑ ድርሻችንን የመወጣት ግዴታ አለብን ሲሉ አሳስበዋል።

ፕሬዚደንቱ አክለውም እንደገለጹት የታላቁ ህዳሴ ግድብ የአዲሱ ትውልድ ብሄራዊ አርማና ተስፋ እንደሆነና ኢትዮጵያ ዛሬ ካለችበት የድህነት አረንቋ ትላቀቃ ከሌሎች አገሮች እኩል ትራመዳለች ተብሎ የሚታሰበው ከታላቁ የህዳሴ ግድብ በሚፈጥረው የልማት ተስፋ ስለሆነና የአዲሱ ትውልድ የብሩህ ተስፋ ነጸብራቅ በመሆኑ ልንጠብቀው፣ ልንከባከበውና ዳር ልናደርሰው ሃላፊነት አለብን ብለዋል፡፡

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ተካ በበኩላቸው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ብዙ መሰናክሎችን አልፎ ከፍተኛ እምርታ የታየበትና 88 % በመቶ የደረሰበት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን ሲሉ ንግግራቸውን ጀምረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ የይቻላልን መንፈስ በማንገብ መላው ኢትዮጵያውያን በአንድነትና በኢትዮጵያዊነት መንፈስ እንዲሰለፉ ያደረገ በመሆኑ የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብቱን ፍትሃዊና በእኩልነት የመጠቀም መርህን በተግባር በማሳየት ጭምር አዲስ የትብብር ምዕራፍ የከፈተ ነው ብለዋል፡፡

ከግድቡ ግዙፍነት ባሻገር በራስ አቅም የመልማትና የማደግ እሳቤን ለእኛ ኢትዮጵያውን ፣ ለአፍሪካዊያን እና እንዲሁም ለዓለም ያስተዋወቀ ግድብ መሆኑንም አክለዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ 12ኛ ዓመት ክብረ በዓል "ታላቁ ህዳሴ ግድብና ሴቶች" በሚል የፓናል ውይይት እየተከበረ እንደሚገኝም ገልፀዋል።

የአባይ ዘመን የስነ-ጽሁፍ ምሽት የታላቁ ህዳሴ ግድብ 12ኛ ዓመት አከባበር አንዱ አካል ሲሆን አላማው ታላቁ ህዳሴ ግድብ ለኪጥበብ ያለው ተምሳሌታዊ ተግባርን ለማሳየት፣ የግድቡ ቱርፋት የሆነውን "የይቻላል" መንፈስ ለተማሪዎች ፣ ለወጣቶች እንዲሁም በጠቅላላው ለትውልዱ ለማስረጽ እና የግድቡንም ስራ ለማጠናቀቅ የሚደረግ ጥረት ነው ሲሉም አክለዋል።

በዚህ ክብረ መርሐ ግብር ላይ የተለያዩ ደራሲያን ግጥሞችንና የኪነ ጥበብ ስራዎቻቸውንም አቅርበዋል፡፡

ዲፕሎማት ዘሪሁን አበበ -ኪናዊ ዲፕሎማሲ
በ (ዶ/ር) አንዱአለም አባተ "ልጅ ለሚወርሰው" በሚል ርዕስ በ(ዶ/ር) ገዛኽኝ ፀጋው "የአባይ አብ ህዝብና የአባይ ምት እንደ ግጥም ቤት ስም" በሚል ርዕስ
አገኘሁ አዳነ (የስነ-ስዕልና ስነ-ጽሁፍ መምህር "ብሄራዊ ምስል ኪናዊ አንድምታ" በሚል ርዕስ
ማርታ ቶሎሳ "ሰላም ለኢትዮጵያ" በሚል ርዕስ " ፍለጋ " ባለ አንድ ገቢር ቴአትር በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቴአትር ጥበባት ትምህርት ክፍል ቀርበዋል፡፡

በመጨረሻም ከዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዚዳንት ታፈረ መላኩ (ዶ/ር) አቶ ሰለሞን ተካ፣ ደራሲ ዘነበ ወላ በተገኙበት የስነ-ግጥም ውድድር አሸናፊ ተማሪዎች ሽልማት ተቀብለዋል፡፡

1ኛ- ተማሪ ያብስራ ፀጋየ "ቁርጥ እኔ ቁርጥ እኛ"

2ኛ- ተማሪ አብርሃም እባቤ "አንተ ጥቁር ካህን"

3ኛ- በህይወት ዮሴፍ "ያው ደሞ አባይ" በሚሉ አርዕስት በፃፏቸው የስነ ፅሑፍ ስራዎች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ተሸልመዋል።

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

==================
ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et