Get Mystery Box with random crypto!

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ለአዲስ መደ | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ለአዲስ መደበኛ እና ለሪሚዲያል ተማሪዎች ስልጠና ሰጠ

==============

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 22/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶች እና ኤች .አይ.ቪ /ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ስለ ጊዜ አጠቃቀም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ ፡፡

በስልጠና መረሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች ንግግር ያደረጉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ወጣቶችና ኤች .አይ.ቪ / ኤድስ መከላከል ዳይሬክቶሬት የስረዓተ ጾታ ባለሙያ ወ.ሮ አጸደ ወንድሙ እንደተናገሩት አዲስ መደበኛ እና ሪሚዲያል ተማሪዎች ለዩኒቨርሲቲው አዲስ እንደመሆናቸው መጠን ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና ነው ብለዋል ፡፡

ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ለማድረግ ጊዜያቸውን ባግባቡ መጠቀም ፣ ከጭንቀትና ከፍረሃት ነፃ ሆነው ትምህርታቸው ላይ ብቻ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል ፡፡


ሀሳባቸውን የሰጡት ተማሪ ውባየሁ አስራትና ናርዶስ ፀጋዬ እስካሁን እንዲህ አይነት ስልጠና ከዚህ በፊት አለማግኘታቸውን ገልፀው በስልጠናው ላይ በመጋበዛቸው ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል ፡፡

የተሰጣቸውን ስልጠናም በአግባቡ ተግባር ላይ ለማዋልና ጊዜያቸውን በአግባቡ ለመጠቀም ቁርጠኛ እንደሆኑም ጠቁመዋል። ጊዜያቸውንም አልባሌ ቦታ ከማሳለፍ ይልቅ ቤተ መጸሐፍት በመግባት ፣ ከጓደኞቻቸው ጋር በትምህርታቸው ዙሪያ በመጠያየቅ ፤ መምህራኖቻቸውን በመጠየቅ ፤ መደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜያትን ባለመሸራረፍ እና በአግባቡ በመከታተል አላማቸውን ዕውን ማድረግ እንዳለባቸውና ቤተሰቦቻቸውና ሀገር የጣለችባቸውን አደራ ማሳካት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ልምዷን ለተማሪዎች ያካፈለችው በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የ5ኛ ዓመት የሲቨል ምህንድስና ተማሪ ተስፋነሽ አምሳሉ እንደገለጸችው በዩኒቨርሲቲው በቆየችባቸው ዓመታት እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎችን ስትከታተል መቆየቷንና በህይወቷም በርካታ ጥቅሞችን ማግኘቷን ገልጻ ተማሪዎች እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎችንና ውይይቶችን በአግባቡ በመከታተል ተግባር ላይ እንዲያውሉት አሳስባለች ፡፡

ተማሪዎች ማድረግ ያለባቸውን ነገር አሁን ማድረግ እንዳለባቸው ነገር ግን ጊዜው ካለፈ በኋላ መፀፀት ተገቢ አይደለም ያለችው ተስፋነሽ መሆን የሚፈልጉትን ፣ ህልማቸውንና እቅዳቸውን ለማሳካት ከአሁኑ ጊዜያቸውን ትምህርታቸው ላይ ብቻ ማዋል ይጠበቅባቸዋል ስትልም ምክራን ለግሳለች ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et