Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ = | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ከአጋርና ባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ ተካሄደ

===============

ደብረ ማርቆስ ዩንቨርሲቲ | መጋቢት 22/2015 ዓ.ም | ህዝብ ግንኙነትና ኮምኒኬሽን ዳይሬክቶሬት |የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በቡሬ ካምፓስ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች፣ እንዲሁም ባለድርሻና አጋር አካላት በተገኙበት የውይይት ተካሄደ፡፡

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ብርሃኑ አለሙ (ዶ/ር) የእንኳን ድህና መጣችሁ መልዕክት ከአስተላለፉ በኋላ እንዳሉት መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የግል ድርጅቶች፣ እንዲሁም ዩኒየኖች ጋር በመተባበር የቡሬ ካምፓስን አቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ቡሬ ከተማ ውስጥ የኢንዱስትሪ ፓርክ በመኖሩ እንዱስትሪዎች ወደ ከተማዋ እየመጡ በመሆኑ ይህን ጸጋ በአግባቡ ለመጠቀም መተባበር፣ መረዳዳትና የጋራ ግንዛቤ በመያዝ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል ሲሉ ገልፀዋል፡፡

በመርሃ - ግብሩ መግቢያ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አስካለማርያም አዳሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ለማድረግ እንደ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተቋም ራዕዩንና ተልዕኮውን እውን ሊያደርግ የሚችለው ከተቋማት ጋር በጋራ መስራት ሲችል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡


ይህንም ተግባር ዩኒቨርሲቲው በአስር አመቱ እስትራቴጅክ እቅድ አንድ ተተኳሪ ተግባር አድርጎ ወደ ስራ መግባቱንም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንቷ አክለው ገልፀዋል፡፡

ረዳት ፕሮፊሰር ደምሳቸው ሽታው የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር እንደገለጹት በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ወደ ስራ የገቡ ፕሮጀክቶችን ዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የቡሬ ግቢ- የዶሮ እርባታ፣ ንብ እርባታ፣ የወተት ልማት አትክልትና ፍራፍሬ፣ አቦካዶ በ1.8 ሄክታር መሬት 365 የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ መድሃኒታማ ዕጽዋት ፣ ግቢውን የማስዋብ ስራ፣ የሙዝ ተክል፣ ሻይ ቅጠል ተክል መሆናቸውን የደብረማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ቡሬ ካምፓስ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሬክተር ብርሃኑ አለሙ (ዶ/ር) በሪፖርቱ አቅርበዋል፡፡

በመጨረሻ የጀርመን ተራድኦ ድርጅት፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ሴቶችና ህፃናት ቢሮ፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ባህል ቱሪዝም፣ አዴት ግብርና ምርምር ማዕከል፣ ምዕራብ ጎጃም ዞን ጤና መምሪያ፣ከዩኒቨርሲቲው ጋር በጥምረት እንደሚሰሩ ቢሮ ሃላፊዎችና ሰራተኞች ገልፀዋል፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

===================

ለተጨማሪ እና አዳዲስ መረጃዎች

#ፌስቡክ
https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም
https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q

#ዌብሳይት www.dmu.edu.et