Get Mystery Box with random crypto!

ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ ====== | Debre Markos University /ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

ለአዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

============

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ |የካቲት 25/2015 ዓ.ም| ህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኔኬሽን ዳይሬክቶሬት

ደብረ ማርቆሰ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶች እና ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ዳይሬክቶሬት በ2015 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች በትናንትናው ዕለት የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

በህይወት ክህሎት ስልጠናው ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማድረግ የስልጠናውን አስፈላጊነትና ዓላማ ገለፃ ያደረጉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች ፣ወጣቶችና ኤች.አይ.ቪ/ ኤድስ ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላም መክብብ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲያችን የተመደቡ አዲስ ገቢ ሴት ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ለቀጣይ ህይወታቸው ስንቅ የሚሆናቸውን ቁም ነገር ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነ ጠቁመዋል።

የዚህ ስልጠና ዋና ዓለማም ተማሪዎች በራስ የመተማመን ስሜት እንዲያዳብሩ ፣ የሌሎችን ሀሳብ እንዲያከብሩ ፣ ሀሳብን በነጻነት በመግለጽ ክህሎት እንዲያጎለብቱ፣ መብትና ግዴታቸውን እንዲያውቁ ፣የአቻ ግፊትን እንዲቋቋሙ እና በአጠቃላይ ተማሪዎች ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና እንደሆነም አክለው ገልፀዋል።

ይህ የህይወት ክህሎት ስልጠና ለሁሉም አዲስ ገቢ ሴትና ወንድ ተማሪዎች በተጠናከረ መልኩ ለመስጠት በዝግጅት ላይ እንገኛለን ሲሉ ሀሳባቸውን አጠቃለዋል ፡፡

በስልጠና መረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው ለተማሪዎች የህይወት ተሞክሯቸውን ያካፈሉት በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ስነ ሰብ ኮሌጅ የአማረኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል መምህርት ወይዘሮ ሀይማኖት እጅጉ እንደገለጹት እንደ ሃገር አሁን እታየ ያለውን ውዥንብር በጥልቀት በመረዳት ተማሪዎች ለመጡበት ዓላማ ብቻ ትኩረት በመስጠት ራሳቸውን ከአልባሌ ቦታ መቆጠብ ፣ጊዜያቸውን በአግባቡ መጠቀም፣ ጓደኛን መምረጥና የአቻ ግፊትን በመቋቋም ራሳቸውን በዕውቀትና በአመለካከት ብቁ ማድረግ ይኖርባቸዋል ብለዋል። ሀገር ተረካቢ ትውልድ ለማፍራት ተማሪዎችን በዕውቀት ማነጽና ማስታጠቅ ተገቢ በመሆኑ እንዲህ ዓይነት ስልጠናዎችና ውይይቶች ተጠናከረው መቀጠል አለባቸው ሲሉም አክለዋል ፡፡

በህይወት ክህሎት ስልጠናው ተሳታፊ የነበሩት ተማሪ ማስተዋል ፈቃዱና ቃል ኪዳን ይታየው የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከአቀባበል ጀምሮ ያደረገላቸው መስተንግዶ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የዛሬው የህይወት ክህሎት ስልጠና ደግሞ ለቀጣይ ህይወታችን መሰረት የሚሆነን ብዙ ቁምነገርና ስንቅ ያገኝንበት ስልጠና ነበር ሲሉ ሀሳባቸውን ሰንዝረዋል። በቀጣይም ይህን የወሰድነውን ስልጠና ተግበር ላይ በማዋል ለመጣንበት ዓላማ ብቻ ትኩረት በማድረግ በትምህርታችን የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ተዘጋጅተናል ብለዋል። ሀገራችንና ቤተሰቦቻችን ከእኛ ብዙ ይጠብቃሉ ፤ የተሰጠን የህይወት ክህሎት ስልጠናም ጥሩ ስንቅ ይሆነናል በማለት ሀሳባቸውን አጋርተውናል ፡፡

ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

የዕውቀት አውድማ ከጮቄ ማማ

=============

ለተጨማሪ አዳዲስ መረጃዎች


#ዌብሳይት www.dmu.edu.et

#ፌስቡክ https://www.facebook.com/dmu.edu

#ቴሌግራም https://t.me/Debre_Markos_University

#ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCqQDHEyYDen3aybySpYsF_Q