Get Mystery Box with random crypto!

Ethio 19

የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19
የሰርጥ አድራሻ: @coronaethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1
የሰርጥ መግለጫ

Y

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2021-02-26 21:29:54
Laink
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
6.9K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 19:07:06
የኤርትራ ምላሽ ፦

የኤርትራው የማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገ/መስቀል ዛሬ ከሰዓት በኋላ በትዊተር ባሰፈሩት ጽሁፍ የአገራቸው ወታደሮች አክሱም ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ስለመግደላቸው አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣውን ሪፖርት እንዳጣጣሉት ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

ሚኒስትሩ ኤርትራ በሪፖርቱ መቆጣቷንና የተሳሳተ ነው ያሉትን ሪፖርት ሙሉ ለሙሉ እንደማትቀበለው በመግለጽ ሪፖርቱ በአብዛኛው መሰረት ያደረገው ሱዳን ውስጥ ባለው ሐምዳይት የስደተኞች መጠለያ ውስጥ ያሉ 31 ግለሰቦችን ነው ብለዋል።

ሚኒስትሩ አቶ የማነ ጨምረውም ፥ "በዚህ መጠለያ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን በተገደሉበት የማይካድራው ጭፍጨፋ ተሳታፊ ሆነው የሸሹ የህወሓት ሚሊሻዎች መሆናቸው ይታወቃል" በማለት በትዊተር ገጻቸው ላይ ስፍረዋል።

የአምነስቲ ኢንተርናሽናል ሪፖርት ከእውነት የራቀ መሆኑን በመግለጽ አገራቸው እንዳማትቀበለው አሳውቀዋል።

Laink
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
7.4K views16:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 18:30:32
#SHARE ይደረግ

ክፍት አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ (SHARE) ይደረግ!!

ምንም የስራ ልምድ አያስፈልግም !!!

S.E.E.D PLC Invites competent applicant to hire as soon as possible !

Apply on Email : seedplc1@gmail.com

ቶሎ ቶሎ የሚወጡ የስራ ማስታወቂያዎች በፍጥነት ወደእናነተ እንዲደርሶት Notification on በማድረግ እና ለወዳጅ ለዘመድ SHARE SHARE እያረጋችሁ ተባበሩ።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
6.9K views15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 16:04:28
ያው ነው ከልኩ አያልፍም የታባቱ!

በአሁን ሰአት የኑሮ ዉድነት ኢትዮጵያ ውስጥ ከአቅም በላይ በመሆኑ መንግስት ለህዝባችን ፈጣን እርዳታ እና እርምጃዎች ካልወሰደ ብዙ ትእይንት የሆኑ ነገሮች ሊፈጠር እንደሚችል ሾካካዉ ሹክ ብሎናል!!

መፍትሔ ቶሎ ይሰጠን!

Laink
7.4K viewsedited  13:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-26 02:18:16 በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ነጭኖ ቀበሌ 10 አማራዎች በኦነግ ታጣቂዎችና በተባባሪዎቹ ዛሬ የካቲት 18 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት እስከ 4 ሰዓት በስለት ተወግተው መገደላቸውን ነው ነዋሪዎች የገለፁት።

በነጭኖ ቀበሌ ደደቢ በተባለ ወንዝ አካባቢ በቆሎ እየወቁ ሳሉ ነው አማራዎች ከ30 በላይ በሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተይዘው በስለት የታረዱት ይላሉ ነዋሪዎች።

አንድ ቦታ ላይ 6፣አጠገቡ 2፣ በመንገድ ላይ 2 በአጠቃላይ የ10 አማራዎችን አስከሬን ለማንሳት መቻሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

በግፍና በአሰቃቂ መልኩ በስለት ብቻ አንገታቸው ላይ ተወግተው የተገደሉትም ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች ሲሆኑ እነሱም ታደሰ ሙሉነህ፣ውብሸት፣እንዳላማው፣ቄስ አንተነህ፣ክንዴነህ፣ካሳሁን፣ተመስገን፣መልካሙ፣ሲሳይእና አንድ ስሙ ያልታወቀ የ7 ዓመት ህጻን መሆናቸው በነዋሪዎች ተረጋግጧል።

ከመካከላቸው ለወሬ ነጋሪ አንድ መልካሙ ተሾመ የተባለ የ24 ዓመት ወጣት ልጅ ሮጦ በማምለጥ የተረፈ ቢሆንም በሁኔታው በከፍተኛ መረበሽ ውስጥ በመግባቱ ለጊዜው በቂ መረጃ ሊሰጠን አልቻለም።

አሰቃቂ ግድያው ከተፈፀመ በኋላ ከ30 ያላነሱ የኦሮሚያ ልዩ ኃይልና የፖሊስ አባላት ቢመጡም አስከሬን ሳያነሱ "ደክሞናልና እርቦናል" በሚል ጥለውን ወደመጡበት ተመልሰዋል ብለዋል።

16 የመኖሪያ ቤቶች፣ የእህል ጎተራና ክምር ስለመቃጠላቸው ምንጮች ገልፀዋል።

Laink
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.8K views23:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 20:14:39
ላምሮት ከማል በነፃ እድትለቀቅ ፍርድ ቤት ወሰነ !

በድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ተጠርጥረው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከነበሩት መካከል አንዷ የሆነችው ላምሮት ከማል በነጻ እንድትለቀቅ ፍርድ ቤት ወሰነ።

በግድያው ተጠርጥረው መዝገብ ከተከፈተባቸው አራት ግለሰቦች ውስጥ ላምሮት ከማል ግድያውን በማመቻቸት ተጠረጥራ የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ ተሳትፎዋን የሚያረጋግጥ የሰውም ሆነ የሰነድ ማስረጃ ዐቃቤ ሕግ አለመቅረቡን በመግለጽ ነው እንድትለቀቅ የወሰነው።

ዛሬ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ የፀረ ሽብርና ሕገ መንግሥታዊ ወንጀል ሁለተኛ ምድብ ችሎት የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰው ማስረጃና የሰነድ ማስረጃ ከመረመረ በኋላ ነው ብይን የሰጠው።

ፍርድ ቤቱ አንደኛ ተከሳሽ ጥላሁን ያሚ የድምጻዊ ሃጫሉን ግድያ መፈፀሙን ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መርምሮ ማረጋገጡን ገልጿል።

የዛሬው የችሎት ውሎ : telegra.ph/BBC-02-25

Via BBC

@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
9.0K viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 16:17:09
ታላቅ ደስታ!

ትላንት ምሽት በስፔን ማድሪድ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች በድል ተንበሻብሸዋል
**************************
ትላንት ምሽት በስፔን ማድሪድ ከተማ በተካሄደ የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በሴቶች 3ሺህ ሜትር አትሌት ጉዳፍ ጸጋዬ በ8:22:65 አንደኛ በመውጣት የምንጊዜም ሁለተኛ ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ በበላይነት ስታጠናቅቅ፣ ለምለም ኃይሉ በሁለተኛነት ውድድሯን አጠናቃለች።

በወንዶች 1500 ሜትር ደግሞ ሰለሞን ባረጋ 3:35:42 በመግባት በአንደኛነት አጠናቋል።
በተመሳሳይ በሴቶች 1500 ሜትር ሂሩት መሸሻ 4:09:42 በመግባት በሁለተኛነት አጠናቃለች።

በተጨማሪም፣ በሴቶች 800 ሜትር ሀብታም አለሙ የቦታውን ሰዓት ጭምር በማሻሻል 1:58:94 በመግባት በአንደኛነት ማጠናቀቋ የአፍሪካ አትሌቲክስ ዩናይትድ መረጃ ያመለክታል።

Laink
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.8K views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 15:58:48
#SHARE ይደረግ

ክፍት አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ (SHARE) ይደረግ!!

=======
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከ6 በላይ ክፍት የስራ ቦታዎች አሉት።
ቶሎ ይመዝገቡ!!!
Apply Email : nebevacanev@abhpartners.com

Office located : Bole Road , behind DH geda Tower Addis Ababa

Application Dead line March 5 ,2021

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.2K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 08:10:50
#SHARE ይደረግ

ሲጠበቅ የነበረዉ ቪድየ ተለቀቀ

በ 2021 አራት 4 , ቤት ውስጥ ሆነን ብዙ ገንዘብ የምንሰራቸው ቢዝነሶች ! 4 Online Business ,To Work from home.

ሙሉ ቪድዩ




Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
9.4K viewsedited  05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-25 08:03:08
በwአንድ ወር ውስጥ ብቻ ወደ 7 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተሰደው ወደ ሱዳን መግባታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንዳለው ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከምዕራባዊው የኢትዮጵያ ከፍል የመተከል ዞን ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሱዳን መሸሻቸውን ገልጿል።

የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ብባር ባሌክ ትናንት በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለፁት፤ ከኢትዮጵያ ወጥተው ወደ ሱዳኗ የብሉ ናይል ግዛት የገቡት ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል።

እስካሁን 3 ሺህ የሚሆኑትን መመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው፤ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቅለው የመጡ ሰዎችን መመዝገብ ሲቻል ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የኤጀንሲው ቃል አባይ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹን ጥገኝነት ጠያቂዎች የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሱዳናዊያን ተቀብለው እያስተናገዷቸው እንደሚገኙ ተገልጿል።


Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.5K views05:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ