Get Mystery Box with random crypto!

በwአንድ ወር ውስጥ ብቻ ወደ 7 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተሰደው | Ethio 19

በwአንድ ወር ውስጥ ብቻ ወደ 7 ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተሰደው ወደ ሱዳን መግባታቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን እንዳለው ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከምዕራባዊው የኢትዮጵያ ከፍል የመተከል ዞን ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሱዳን መሸሻቸውን ገልጿል።

የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ብባር ባሌክ ትናንት በጄኔቫ በሰጡት መግለጫ ላይ እንደገለፁት፤ ከኢትዮጵያ ወጥተው ወደ ሱዳኗ የብሉ ናይል ግዛት የገቡት ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል።

እስካሁን 3 ሺህ የሚሆኑትን መመዝገብ መቻሉን ጠቅሰው፤ በሁሉም አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቅለው የመጡ ሰዎችን መመዝገብ ሲቻል ቁጥሩ ሊጨምር እንደሚችል የኤጀንሲው ቃል አባይ ተናግረዋል።

ቀሪዎቹን ጥገኝነት ጠያቂዎች የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ሱዳናዊያን ተቀብለው እያስተናገዷቸው እንደሚገኙ ተገልጿል።


Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa