Get Mystery Box with random crypto!

Ethio 19

የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19
የሰርጥ አድራሻ: @coronaethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1
የሰርጥ መግለጫ

Y

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2021-02-01 14:38:39
ምርጫ ቦርድ የፓርቲዎችን የምርጫ ምልክት ዛሬ ይፋ ያደርጋል !

የኢትዮጽያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የፓለቲካ ፓርቲዎችን የምርጫ መወዳደሪያ ምልክት ይፋ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የቦርዱ ኮሙኒኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ እንደገለጹት፤ እስካሁን መስፈርቱን አሟልተው ጠቅላላ የተመዘግቡት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል እስእካሁን የደረሷቸውን 48 የምርጫ ምልክቶች ናቸው።

እነዚህን ምልክቶችም አስቀድሞ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ቦርዱ ዛሬ ይፋ ያደርጋል ማለታቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስነብቧል።
8.4K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-01 06:34:26
#CoupAlert

በማይናማሯ መሪ አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ መፈንቅለ መንግሥት ተፈፀመ!

በቀድሞዋ በርማ በአሁኑ መጠሪያዋ ማይናማር የምትባለው ሀገር መሪ ዳው አንግ ሳን ሱ ኪ ላይ በመከላከያ ሰራዊቱ መፈንቅለ መንግስት እንደተፈፀመባቸው እየወጡ የሚገኙ ዘገባዎች ያሳያሉ። የሀገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን የተቋረጠ ሲሆን የኢንተርኔት እና የስልክ ግኑኝነት በተመሳሳይ ተቋርጠዋል። መከላከያ ሰራዊቱ በራሱ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳስታወቀው ከሆነ በሀገሪቱ ለአንድ አመት የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል። ይህንንም ተከትሎ ሁሉም ስልጣኖች በመከላከያ ሰራዊቱ እጅ እንደሚሆኑም ተገልጿል። በዚህ መግለጫ መሪዋና የሷ ሰዎች ከሁለት ወር በፊት የተደረገውን የምርጫ ውጤት በማጭበርበራቸው ከስልጣን እንዲነሱና እንዲታሰሩ ተደርገዋል በሚል ተገልጿል።
9.7K views03:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 18:11:06
በጉለሌ እፀዋት ፓርክ የተነሳው እሳት ፦

ዛሬ ከቀኑ ሰባት ሰዓት አካባቢ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በጉለሌ እጽዋት ፓርክ ውስጥ እሳት ተነስቶ በተደረገው ርብርብ እሳቱ የከፋ ጉዳት ሳያስከትልና ወደ ሌላ ቦታ ሳይስፋፋ በቁጥጥር ስር እንዲውል መደረጉን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አሳውቀዋል።

እሳቱን ለማጥፋት በርካታ የአዲስ አበባ እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች ፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት ፣ የአዲስ አበባ የእሳት እና የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባልደረቦች ፣ የመንገዶች ባለስልጣን፣ የአከባቢው አስተዳደር እና ህብረተሰብ ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸው ተገልጿል።

እሳቱን ለማጥፋት ርብርብ ላደረጉ አካላት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማ አሰተዳደሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

ለእሳቱ መነሳት ምክንያት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው የተገለፀ ሲሆን ቀሪ ስራዎች በልዩ ትኩረት እንደሚከናወኑና በየወቅቱ ለህበረተሰቡ መረጃ እንደሚሰጥ ምክትል ከንቲባዋ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው አሳውቀዋል።
10.9K views15:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 18:10:10
የኮሮና ክትባት በመጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ተገለጸ!

ክትባቱ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ይዳረሳል ተብሏል፡፡ የክትባት ስራውን የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙንም የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
9.8K viewsedited  15:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 14:19:24 የህወሃት ሊቀመንበር የሆኑት ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ከሁለት ወራት ዝምታ በኋላ በትናትናው ዕለት፣ ጥር 22፣ 2013 ዓ.ም በድምፂ ወያነ ትግራይ ፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለትግራይ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ደብረ ፅዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) በትግራይ ላይ የተከሰተውን ወታደራዊ ግጭት ተከትሎ በተቋረጠው ድምፂ ወያነ ትግራይ የፌስቡክ ገፅ በቀጥታ ለ13 ደቂቃዎች በድምፅ ባስተላለፉት መልዕከት ክልሉ ላይ ደርሷል ስለተባሉ ውድመቶች፣ ቀጥሏል ስላሉት ትግል ሁኔታ እንዲሁም ለትግራይ ህዝብና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ አቅርበዋል።"የትግራይ ሴቶች በተናጠልና በደቦ ይደፈራሉ። የትግራይ ሰዎች ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችና ነጻነቶች በከፋ መገለጫና አኳሃን ይጣሳሉ፣ ይገፈፋሉ። የትግራይ መንደሮችና ዓብያተ እምነቶች፣ የትግራይ ሰራዊት ይኑርበት አይኑርበት ሳይገዳቸው የቦምቦችና የመድፎ ዒላማ ይደረጋሉ። ውድና መተኪያ የሌላቸው ቅርሶችም ይወድማሉ፣ ይዘረፋሉ። በሚልዮን የሚቆጠር ህዝብ እንዳለ ከቀየው ወጥቶና ተፈናቅሎ የመከራ ኑሮ ይኖራል።" ብለዋል።

በትግራይ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግና የፌደራል ፖሊስ በበርካታ የህወሓት ወታደራዊና ፖለቲካዊ አመራሮች ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው። ከነዚህም አመራሮች አንዱ የህወሃት ሊቀ መንበር ደብረ ፅዮን ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት ያሉበት አይታወቅም።ለእስር ማዘዣው ዋነኛ ምክንያቶቹ በትግራይ ክልል በሚገኘው በአገር መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት በመፈፀም፣ የአገር ክህደት ወንጀል በመፈፀም፣ የመከላከያ ሠራዊትና የፖሊስ አባላት እንዲታገቱ አድርገዋል በሚል ተጠርጥረው ነው።

(BBC)
11.0K views11:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-31 12:47:04
የህዳሴው ግድብ ግንባታ በታቀደለት ጊዜና በሚፈለገው መንገድ እየተከናወነ መሆኑ ተገለፀ!

የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚንስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ እና የኢትዮጰያ ኤሌክትሪክ ቦርድ አባላት በትናንትናው ዕለት በስፍራው በመገኘት ግምገማ አድርገዋል። ከጉብኝቱ በኋላ ፣ የግድቡ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ እየተከናወነ እንደሆነና የግንባታ ሂደቱም በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡ሚንስትሩና የቦርድ አባላቱ የግንባታ ስራውን ከሚያከናውኑ ኮንትራክተሮች ፣ ከባለሙያዎችና አማካሪዎች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል፡፡ ለግድቡ መጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሃገር ውስጥና ውጪ እያደረጉት ያለው ድጋፍ ከምን ግዜውም በላይ ተጠናክሮ ቀጥሏልም ነው ያሉት።
11.1K views09:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 22:41:01
ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት ፈጋግ ድንበር ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ሥራ ጀመረ

የኢሚግሬሽን ፣ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ኢትዮጵያ ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስናት የጋምቤላ ክልል ፈጋግ ድንበር የመጀመሪያው ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላ ዛሬ በማስመረቅ ሥራ ጀመረ።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክታር አቶ ሙጂብ ጀማል በምረቃ ስነ- ስርዓቱ ወቅት እንዳሉት የመቆጣጠሪያ ኬላው የሁለቱ ሀገራትን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል።

በተለይም በአካባቢው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና አሁን ላይ የሀገራት ስጋት የሆነውን የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ጭምር ጠቀሜታው የላቀ መሆኑን ተናግረዋል።

አሁን ላይ በኢትዮጵያ ብሎም በአፍሪካ የህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ከፍተኛ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ቀውስ እያስከተለ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

ኤጀንሲው ከ2012ዓ.ም. ጀምሮ በሀገሪቱ ጠረፋማ አካባቢዎች ዘመናዊ የመቆጣጠሪያ ኬላዎችን በማቋቋም ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርንና ፍልሰትን ለመቆጣጠር በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
11.9K views19:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 19:52:17
የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ ባካሄደው ስብሰባ ህገ ወጥ የመሬት ወረራ፤ ባለቤት አልባ ህንፃዎች፤ የኮንደሚኒየም ቤቶች፤ የቀበሌ መኖርያና ንግድ ቤቶችን አስመልክቶ በጥናት የተገኘው ግኝትቶች ላይ የውሳኔ ሃሳብ አስተላለፈ፡፡

የከተማው ካቢኔ ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የከተማው አመራር በሪፎርሙ በገባው ቃል መሰረት ምንም እንኳ ቢዘገይም የነዋሪው ቅሬታ መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት እና በተጨባጭ ጥናት በመመርኮዝ ለማጣራት እና ለመለየት የተደረገውን ጥረት ያመሰገኑ ሲሆን ወደፊት መወሰድ አለበት ባሉት እርምጃ ላይ አፅንኦት ሰተው ተወያይተዋል፡፡በመሆኑም በጥናቱ የተገኙ 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ፤ በጥናቱ የተገኘው ህገ-ወጥ መንገድ የተያዙ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል፤ በዋናነት በ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤ የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንሰጥ ሲሉ ወስነዋል፡፡ካቢኔው በቀረቡት አጀንዳዎች ላይ በሰፊው የተወያየ ሲሆን ይህ ችግርና ስርዓት አልበኝነት 1997 ጀምሮ እየተንከባለለ የመጣ መሆኑን እና ወደፊት እንዳይደገም እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡

[Capital]
11.9K views16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 19:19:02
አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች አፍሪካን የሁለተኛ ዙር ወረርሺኝ ሰለባ እያደረጉ ነው ተባለ

አዲስ የተገኙ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች አፍሪካን ለሁለተኛ ጊዜ በወረርሺኝ ክፉኛ እንድትጠቃ እያደረጉ እንደሆነ የአለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ፡፡

በአሁን ወቅት በቀላሉ የሚተላለፉት አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያዎች በመላው አፍሪካ እየተስፋፉ ተጨማሪ ታማሚዎችና ሞት እያስከተሉ እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል፡፡

መጀመሪያ በደቡብ አፍሪካ የተገኘው አዲስ የኮሮናቫይረስ ዝርያ በሌሎች የአፍሪካ አገራት በፍጥነት እየተስፋፋ እንደሆነ በአፍሪካ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞኤቲ በበይነ መረብ አማካኝነት በተካሄደ ጉባዔ ተናግረዋል፡፡

አሁን ላይ አዲሱ ዝርያ በቦትሰዋና፣ ጋና፣ ኬንያ፣ ማዮቴ እና በዛምቢያ እንዲሁም ከአፍሪካ ውጪ ባሉ 24 የአለም አገራት መገኘቱ ተረጋግጧል፡፡

እስካሁን ባለው መረጃ በአፍሪካ ኮቪድ 19 ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲጠቁ 89 ሺህ ገደማ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸውን ማጣታቸውን ከሲኤንቢሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
11.1K views16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 17:14:37
በአዲስአበባ ህገወጥ ሆነው የተገኙት 322 ባለቤት አልባ ህንጻዎች በግልፅ ጨረታ ተሸጠው ወደ መንግስት ካዝና ገቢ እንዲሆኑ፤ ባዶ ሆነው የተገኙ 21,695 የኮንዶሚኒየም ቤቶችን በማስለቀቅ ለተጠቃሚዎች እንዲታደል ተወሰነ!

የኮንዶሚኒየም ቤቶቹ በዋናነት በ1997 ተመዝጋቢ የሆኑና በቋሚነት እየቆጠቡ ላሉ ነዋሪዎች በእጣ እንዲተላለፍ፤ የቀበሌ ቤቶችን አስመልክቶ በህገ-ወጦች የተያዙ የመኖርያ ቤቶች ግልፅ የሆነ መስፈርት ወቶላቸው ለደሆች፤ ለአቅመ ደካሞችና ለተለያየ ችግር ለተጋለጡ ነዋሪዎች እንዲሰጥ፤ የቀበሌ የንግድ ቤቶች በህገ-ወጥነት ከያዙት ሰዎች ተነጥቆ ለስራ አጥ ወጣቶች በእጣ እንሰጥ ሲሉ ወስኗል፡፡
11.1K views14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ