Get Mystery Box with random crypto!

Ethio 19

የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19
የሰርጥ አድራሻ: @coronaethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1
የሰርጥ መግለጫ

Y

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2021-01-30 15:58:39
የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 95ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
11.0K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 15:58:23
10.5K views12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 14:13:20
በአዳማ ከተማ ለእንግድነት ከወላጅ እናቱ ጋር የሄደ የ18 ወር ህፃን በጅብ ተበላ

በአዳማ ከተማ መስተዳድር ዳቤ ክፍለ ከተማ ዳቤ ሹሉቄ ቀበሌ ልዩ ቦታው ቀጠና 9 ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ለእንግድነት ከወላጅ እናቱ ጋር የሄደ የ 18ወር ህፃን በጅብ ስለመበላቱ ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።

በተጠቀሰው እለት ከምሽቱ 3ሰዓት ላይ አንዲት እናት የአንድ ዓመት ከስድስት ወር ህፃን ልጇን በመታቀፍ አቶ ሚኒሊክ ታዬ ከተባሉ ግለሰብ ቤት ታቀናለች።

ጫካ አፋፍ ላይ ከሚገኘው መኖሪያ ቤት ደርሳም ቡና ተፈልቶላት ከቤተሰቡ ጋር በመጫወት ላይ ሳለች ፤ ከጫካው የወጣ ጅብ ህፃኗን ከእናት እቅፍ ፈልቅቆ በመውሰድ ይሰወራል።

የከተማዋ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ገልሜቻ በተለይ ለብስራት ራዲዮ ሪፓርተር ሚኪያስ ፀጋዬ እንደተናገሩት ፤ በሁኔታው የተደናገጠው ቤተሰብ ጅቡን ተከታትለው ወደ ጫካ ቢገቡም ሊያገኙት የቻሉት ብቸኛ ነገር የህፃን ጨርቅ ብቻ ሁኗል።

ጉዳዩ ለአዳማ ከተማ ፖሊስ ሪፖርት የተደረገ ሲሆን የምርመራ ስራዎች በመከናወን ላይ ይገኛል ያሉት ኢንስፔክተር ወርቅነሽ ፤ በቅርብ ግዜያት መሰል አደጋ በከተማዋ ሲፈጠር ይህ ለሶስተኛ ግዜ መሆኑንም አስታውሰዋል።
11.5K views11:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-30 10:47:22
መቱ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

መቱ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት በተለያየ የትምህርት መስክ ትምህርታቸውን የተከታተሉ 2,896 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።
11.6K views07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 22:51:15
#የትግራይን_ህዝብ_እንርዳ

ከ4.5 ሚልዮን በላይ ቁጥር ያለው የትግራይ ህዝብ በጦርነቱ ክፉኛ በመጎዳቱ ኣስቸኳይ እርዳታ ያስፈልገዋል።

ኢትዮጵያውያን እንደ ክልል መስተዳድሮች፣ እንደ ከተማ ኑዋሪዎች፣ እንደ ህዝብና ዜጋ እንደ ዲያስፖራ፣ እንደ ሰው በጦርነቱ ክፉኛ ለተጎዳው የትግራይ ህዝብ እርዳታ ማድረስ ይጠበቅበታል።

በመላ ኢትዮጵያና ዓለም የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቻቹ፣ ጎረቤቶቻቹና ህዝባቹ በመርዳት ግዴታቹ ተወጡ።

* ምግብ፣ መድሓኒት፣ ሸቀጣሸቀጥ በኣስቸኳይ ያስፈልገዋል።

https://www.washingtonpost.com/world/africa/extreme-urgent-need-starvation-haunts-ethiopias-tigray/2021/01/17/3d219faa-589e-11eb-acc5-92d2819a1ccb_story.html?fbclid=IwAR0QGG8CPl61m8G-2loGAdIaVtlKVI7FgvsvYC4fL-xv69bJF7BjSP0FtKM

#የትግራይን_ህዝብ_እንርዳ #SHARE
12.5K views19:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 22:02:55
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስል የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው

ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ

የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ፣ የኢፌዴሪ የመከላከያ ሠራዊት ኢትዮጵያን እንዲመስልና በቴክኖሎጂ የዳበረ እንዲሆን የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ተናገሩ።

ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ የኢፌዴሪ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከአባሉ እስከ ከፍተኛ አመራሩ ድረስ የኢትዮጵያ ብሄር ብሔረሰቦችን እንዲመስል እና ከወቅቱ ጋር እንዲዘምን ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ከለውጡ በኋላ ወደ ሠራዊቱ የሚቀላቀሉ ወጣቶች ፍላጎት መጨመሩን የገለፁት ጄኔራል ብርሀኑ፣ ከመላ ሀገሪቱ በተመለመሉ ከፖለቲካ ወገንተኝነት የፀዱ እና ለሙያው ፍቅርና ክብር ያላቸው ተተኪ ወታደሮችን ለማፍራት ከፍተኛ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፤ በዚህም አበረታች ለውጦች እየተገኙ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።

በተለይም ከዚህ በፊት፣ በውሳኔ ሰጪ ቦታዎችና የተመረጡ ሙያዎች፣ በከፍተኛ ወታደራዊ አመራሩ በአንድ ብሔር ተወላጆች ብቻ ተይዞ መቆየቱን አውስተው ከለውጡ በኋላ የማመጣጠን ስራዎች በመሰራታቸው ትልቅ ውጤት ተገኝቶበታል፤ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሠራዊቱ ዘመኑ ከደረሰበት ቴክኖሎጂ ጋር አብሮ እንዲዘምን ሁለንተናዊ ተግባራት በመከናወን ላይ እንደሚገኙ ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ መግለፃቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
12.4K views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 14:07:06
በአዲስአበባ በህገወጥ የቤትና የመሬት ወረራ የተሳተፉ አመራሮችን ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ!

የከተማ አስተዳደሩ ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ የጥናቱን ግኝቶች እና መረጃዎች አባሪ አድርጎ ደብዳቤ መላኩንም አስታውቋል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማእረግ የአገልግሎት ሲጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ የከተማ አስተዳደሩ ሰሞኑን ይፋ ባደረገው የህገወጥ የመሬትና የቤት ወረራን አስመልክቶ ማብራርያ ሰጥተዋል።

በማብራርያቸው ጥናቱ በከተማ አስተዳደሩ ሁሉም ክፍለ ከተሞች መካሄዱን አብራርተዋል። ጥናቱን ለማካሄድ በተቋቋመው ኮሚቴም በየ15 ቀኑ ግምገማ ያደርግ እንደነበር አንስተዋል።

በዚህ ህገወጥ ስራ ላይ በተሰማሩት ላይ አስተዳደራዊና ፖለቲካዊ እርምጃ ወስደናል ያሉት አቶ ጃንጥራር ህጋዊ በሆነ መልኩ በዚህ ስራ ላይ የተሳተፉትን ተጠያቂ ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ ለፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ያገኛቸውን መረጃዎች አባሪ አድርጎ ደብዳቤ ልኳል ተጠያቂነቱ ቀጣይ ስራ ይሆናል ብለዋል አቶ ጃንጥራር አባይ። (ምንጭ:-ኢቢሲ)
13.7K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-01-29 11:44:45
ኑሮውን በጅማ ከተማ ያደረገውና የወርልድ ቴኳንዶ ስፖርትን ከተወዳዳሪነት ተነስቶ ወደ አሰልጣኝነት ደረጃ ደርሶ የነበረው ይታገሱ ኃ/ሚካኤል በድንገተኛ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
13.0K views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ