Get Mystery Box with random crypto!

Ethio 19

የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19 E
የቴሌግራም ቻናል አርማ coronaethiopiaa — Ethio 19
የሰርጥ አድራሻ: @coronaethiopiaa
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 1
የሰርጥ መግለጫ

Y

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2021-02-19 15:40:32
#Share#Attention

በ5 ክልሎችና በ2 የከተማ አስተዳድሮች ኤችአይቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የፌዴራል የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽ/ቤት አስታወቀ።

በሀገር ደረጃ የኤች አይ ቪ/ኤድስ በወረርሽኝ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት መጠን ያለባቸው ፦

- ጋምቤላ 4.6 በመቶ
- አዲስ አበባ 3.4 በመቶ
- ድሬዳዋ 2.5 በመቶ
- ሀረሪ 2.4 በመቶ
- አፋር 1.4 በመቶ
- ትግራይ 1.2 በመቶ
- አማራ 1.2 በመቶ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በWHO መረጃ ከሆነ አንድ በሽታ ወረርሽኝ ነው የሚባለው የስርጭት ምጣኔው 1 በመቶ እና ከዚያ በላይ ሲሆን፣ እንደ ሀገር የኤች አይ ቪ/ኤድስ የስርጭት መጠን 0.93 በመቶ ስለሆነ በወረርሽኝ ደረጃ አይደለንም ተብሏል።በማህበረሰብ ደረጃ ከፍተኛ የስርጭት ምጣኔ የሚታይባቸው ሴተኛ አዳሪዎች ሲሆን ቁጥሩ 23 በመቶ ነው ተብሏል።በመቀጠልም፣ ባሎቻቸውን በሞት ያጡ ሴቶች ላይ 19 በመቶ ሆኖ ይታያል።

የረጅም ርቀት አሽከርካሪዎች፣ ኮንስትራክሽን ሳይት ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች፣ አፍላ ወጣቶች ላይ ከ2 በመቶ በላይ የስርጭት ምጣኔ ያሳያል።በከተማ ያለው የስርጭት ምጣኔ 3 በመቶ ሲሆን በገጠር ያለው ደግሞ 0.4 ደርሷል ተብሏል።

በተጨማሪ በወንዶች ያለው የስርጭት ምጣኔ ከሴቶች ይልቅ ዝቅ ብሎ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
የHIV የስርጭት ምጣኔ 61 በመቶ የሚሸፍኑት ሴቶች ሲሆኑ ፣ 39 በመቶ የሚሆነውን የሚሸፍኑት ወንዶች እንደሆኑ ተገልጿል። (ኢብኮ)

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
7.5K views12:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-19 15:15:31
ሀገር መከላከያ ሰራዊት "ዋዜማ ሬድዮን" በህግ እጠይቃለሁ አለ።

ዋዜማ ሬዲዮ ‘‘የተወሰኑ የመከላከያ ተቋማት የባንክ ሂሳባቸውን ወደ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ አዙረዋል፡፡ የመከላከያ ኮንስትራክሽን ድርጅት የባንክ አካውንቱን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወደ ኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ካዛወሩት መካከል ነው'' የሚል ዘገባ አውጥቷል።

የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ ፣ ይህ ዘገባ ፍጹም የተሳሳተ እና እውነት የሌለው መሆኑን አረጋግጠናል ብለዋል።

ዘገባው የህግ ጥሰት ያለበትና በህዝቡ እና በሠራዊቱ መካከል ጥርጣሬን የሚፈጥር በመሆኑ ተቋሙ በህግ ይጠየቃል ሲሉ ተናግረዋል።

ሜ/ጄ መሀመድ ፥ "መከላከያም ሆነ በስሩ ያሉት የልማት ድርጅቶች የቀየሩት ባንክ የለም። የተዛወረ ገንዘብም የለም፡፡ ስለዚህ ተቋሙ ይህን የተሳሳተ ዘገባ ያሰራጨውን በሀገራችን ህግ እንዲጠየቅ ያደርጋል" ሲሉ ተናግረዋል።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
7.5K views12:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-19 07:48:19
#እንጠንቅ SHARE ይደረግ

ማስጠንቀቂያ፡ ይህ ፅሑፍ ሊረብሹ የሚችሉ ይዘቶች አሉበት።

ቢቢሲ የሠራው የምርመራ ዘገባ አንድ ኦሚግል የተሰኘ የቪድዮ መደዋወያ ድረ-ገፅ ሕፃናትን ለወሲባዊ ጥቃት እንደሚያጋልጥ ተደረሰበት።
ኦሚግል የተሰኘው የቀጥታ ቪድዮ መደዋወያ መተግበሪያ [አፕሊኬሽን] የማይተዋወቁ ሰዎች እየተያዩ እንዲደዋወሉ የሚያስችል ነው።

ድረ-ገፁ ይዘቶቼን እቆጣጠራለሁ ቢልም ተጠቃሚዎች ያልተጠበቀ ድርጊት ሲፈፅሙበት ታይቷል።ዓለም አቀፍ የሕፃናት መብት ተቋርቋሪዎች ወሲባዊ ጥቃት አድራሾች ገፁን ተጠቅመው ሕፃናትን እየበዘበዙ ነው ሲል ይከስሳሉ።

የቢቢሲ ምርመራ ቡድን በመጀመሪያዎቹ ሁለት ሰዓታት ብቻ ግለ-ሩካቤ [ማስተበርቤት] ከሚያደርጉ 12 ወንዶች ጋር ተገናኝቷል።ከዚህ በተጨማሪ ስምንት ራቁታቸውን ያሉ ወንዶችና ሰባት የወሲብ ድረ-ገፅ ማስታወቂያዎች ተመልክቷል።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.5K viewsedited  04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-19 06:08:01
#SHARE

ክፍት አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ (SHARE) ይደረግ!!

ለእናንተ ባይጠቅም ለወዳጅ ለዘመድ (SHARE ) ይደረግ!!

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን የቅርንጫፍ 9 ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ጽ/ቤት ከላይ በተጠቀሰው የስራ መደብ ላይ ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል!

ለበለጠ መረጃ ስልክ ፡ 011 82 809 91

ቶሎ ቶሎ የሚወጡ የስራ ማስታወቂያዎች በፍጥነት ወደእናነተ እንዲደርሶት Notification on በማድረግ እና ለወዳጅ ለዘመድ SHARE SHARE እያረጋችሁ ተባበሩ።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
7.9K views03:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 22:01:59
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግራይን መልሶ ለመገንባቱ የአንድነት ንቅናቄ የሚችሉትን አስተዋጽኦ ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረቡ!!!
******************

ዛሬ ከሰዓት በበይነ መረብ በታገዘ ስብሰባ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ የክልል ፕሬዚደንቶች እና የከተማ ርዕሰ መስተዳድሮች ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ መስተዳድር እንዲሁም ለክልሉ ሕዝብ የሚሆን የአንድነት ንቅናቄን አስጀምረዋል።

የአንድነት ንቅናቄው ክልሎች፣ የፌደራል ተቋማት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመከናወን ላይ ያለውን ሰብዓዊ ርዳታ እንዲደግፉ የማስቻል ዓላማን ይዟል ተብሏል።

እያንዳንዱ ክልል ቃል የገባቸው ተሽከርካሪዎች፣ ልዩ ልዩ ቁሳቁስ እና መገልገያዎች፣ ለአርሶ አደሮች የሚቀርቡ ዘሮች፣ አምቡላንሶች፣ መድሃኒት እንዲሁም የገንዘብ ድጋፍ በሚቀጥሉት ቀናት ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የሚደርሱ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.6K views19:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 20:44:50
#ከፍተኛ_ጥንቃቄ_አዲስ_አበባ

በየዕለቱ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ሞት ሪፖርት እየተደረገ የሚገኘው ከአዲስ አበባ ከተማ ነው።

ለአብነትም ፦

- ዛሬ የካቲት 11 በሀገር አቀፍ ደረጃ ሪፖርት ከተደረገው የ12 ሰዎች ሞት ፤ 11ዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

- የትላንት ሪፖርት የከተማው አስተዳደር ጤና ቢሮው አላሰራጨም።

- የካቲት 9 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 14 ሞት 12ቱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

- የካቲት 8 በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው 15 ሞት 11ዱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ናቸው።

በየዕለቱ የሟቾች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል። እጅግ በርካታ ሰዎችም በፅኑ ታመዋል ፤ በርካቶችም የመተንፈሻ መሳሪያ ማግኘት ባለመቻላቸው ከፍተኛ ስቃይ እያጋጠማቸው/ህይወታቸውንም እያጡ ነው።

ውድ አባላት በየትኛውም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ሳትዘናጉ እራሳችሁን እና ቤተሰቦቻችሁን ከዚህ አስከፊ ወረርሽኝ እንድትጠብቁልን አደራ እንላለን።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
9.4K views17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 17:27:43
“ሕወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ እብደት ነው” ፕሬዝደንት ኢሳያስ

የኤርትራው ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፍወርቂ ትናንት ምሽት ከሀገራቸው ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ በርካታ ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ከሁለት ዓመታት በፊት የኢትዮያና የኤርትራ የኦምሀጀር ድንበር በተከፈተበት ወቅት ከቀድሞው የትግራይ ክልል ር/መስተዳደር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል (ዶ/ር) ጋር ተገናኝተው ለምን ለጦርነት ዝግጅት እንደሚያደርጉ ጠይቀዋቸው እንደነበር አንስተዋል፡፡

ሕወሓት በፍጹም የሰሜን ዕዝን በማጥቃት ጦርነት ይጀምራል ብሎ የጠበቀ እንደሌለ የገለጹት ፕሬዝደንት ኢሳያስ "ይህ ጦርነት በተሳሳተ ስሌት የተጀመረ ነው” ያሉ ሲሆን “ሕወሓት በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙ እብደት ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
9.2K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 07:25:38
ሰላም ዉድ ተመልካቾቻችን። በዚህ ቪድዬ ላይ 5 ከቤት ሆነው ኢንተርኔትን ብቻ በመጠቀም ማንኛውም ሰው ሊሰራቸዉ የሚችሉትን ስራዎች ይዘን ቀርበናል።

ADDIS IDEA
የተሰኘዉን YouTube ቻናላችንን SUBSCRIBE በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ።

ሙሉ ቪድዩ
Link



የ ቻናላችን አላማ

•ወደ USA እና ሌሎች ሀገሮች ስኮላርሽፕ (SCHOLARSHIP ) እንዴት መሙላት እንደሚችሉ አና መምጣት እንደሚችሉ ማስተማር።

•በተለያዩ ሃገራት ላይ ሆነዌ INTERNET በመጠቀም በቀን $$100 ዶላር እና ከዛ በላይ ገንዘብ እንዴት መስራት እንደሚቻል ይማሩ!!

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
9.7K views04:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-02-18 04:13:09
ክፍት አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ (SHARE) ይደረግ!!

ለእናንተ ባይጠቅም ለወዳጅ ለዘመድ (SHARE ) ይደረግ!!


ፌና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ያወጣዉ ከላይ የተጠቀሰዉን ስራ በቋሚነት ሰራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል !!

ስልክ 0115 51 67 77


ቶሎ ቶሎ የሚወጡ የስራ ማስታወቂያዎች በፍጥነት ወደእናነተ እንዲደርሶት Notification on በማድረግ እና ለወዳጅ ለዘመድ SHARE SHARE እያረጋችሁ ተባበሩ።

Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
8.7K viewsedited  01:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ