2021-02-13 18:48:50
የኮሮናቫይረስ ክትባት ሴቶች እንዳይወልዱ ያደርጋል በሚል የሚሰራጨው አሉባልታ መሠረተ ቢስ እንደሆነ ባለሙያዎች ገለጹ።
የፋይዘር ክትባት የሴቶች የሥነ ተዋልዶ ጤና ቀውስ ያስከትላል መባሉ "ምክንያታዊ አይደለም" ሲሉ በለንደን ኪንግስ ኮሌጅ የሚሠሩት ፕ/ር ሉሲ ቻፔል ተናግረዋል።
ክትባቱ ሰውነት በሽታውን የመከላከል አቅም እንዲያዳብር የሚረዳ ነው። ሰዎች በቫይረሱ እንዲያዙ ወይም ዘረ መላቸው እንዲለወጥ አያደርግም።
በሌላ በኩል ነፍሰ ጡር ሴቶች በክትባት ሙከራው ወቅት አልተካተቱም። ባለሙያዎች በክትባቱና በነፍሰ ጡር ሴቶች መካከል ስላለው ትስስር ግልጽ መረጃ ባይሰጡም፤ በከፍተኛ ሁኔታ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ነፍሰ ጡር ሴቶች ብቻ ክትባቱን እንዲወስዱ ይመክራሉ።
ፕ/ር ኒኮላ ስቶንሀውስ የተባሉ የቫይረስ ተመራማሪ፤ ክትባቱ የተሠራበት መዋቅር የሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድርበት መንገድ የለም ይላሉ።
ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ያለው አሉባልታ የሚያጣቅሰው ከዚህ ቀደም በዩናይትድ ኪንግደም መንግሥት የወጣ መግለጫን ነው።
Link
@coronaethiopiaa @coronaethiopiaa
11.9K viewsedited 15:48