Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.57K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2024-04-04 09:41:03
ኮንሰርት፣ ባዛር ሲያዘጋጁ
ፊልም/ቲያትር ሲያቀርቡ
የሚታይ የሚጎበኝ ሲኖርዎት
የመግቢያውን ትኬት
እኛ እንሽጥልዎት!
**********
በሲቢኢ ብር መተግበሪያ የትኬት ሽያጭ አገልግሎት
በቀላሉ ሚሊዮኖች ጋር ይደርሳሉ!

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
13.4K viewsH, 06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 19:34:39
ከ 95 ሺ እስከ 80 ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ስለማውጣት (3ኛ ዙር)
******************************
በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያላግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት ከ10 ሺ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መልሰዋል፡፡

በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ የማይመልሱ ግለሰቦችን ምስል ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ባንካችን በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሰረት በሶስተኛ ዙር ያልመለሱት የገንዘብ መጠን ከ 95 ሺ እስከ 80 ሺ ብር የሆነ ግለሰቦችን መረጃ ለማውጣት ተገደናል፡፡

የምስል እና ሌሎች መረጃዎችን ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መመልከት ይችላሉ ።

https://combanketh.et/customer-round-three
16.0K viewsBiniam zewdie, 16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-03 10:32:34
ባሉበት ዘና ብለው ይላኩ!

EthioDirect - #ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ የሞባይል መተግበሪያ፡፡
******************

በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ መላክ ይችላሉ፡፡
*********************

የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።

• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect

• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
17.2K viewsH, 07:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 19:22:22
ከ 121 ሺ እስከ 95 ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ስለማውጣት
**************
በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10 ሺ በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መልሰዋል፡፡
የገንዘብ መጠኑ ከ 121 ሺ እስከ 95 ሺ ብር ያለአግባብ ከባንካችን ወስደው ያልመለሱ የግለሰቦችን ማንነት የሚያሳዩ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ ማድረግ ስላስፈለገ ለሁለተኛ ጊዜ ያወጣናቸውን መረጃዎች ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መረጃዎችን መመልከት ይችላሉ ።
https://combanketh.et/customer-round-two
23.0K viewsBiniam zewdie, 16:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 16:34:42
የጥንቃቄ መልዕክት
**************
አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል፡፡
እነዚህ አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “የተዘጋ ሂሳብችሁን እንክፈትላችሁ” ፤ “ሂሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ነገር ግን ባንካችን ስልክ ደውሎ ስለ ሂሳብዎ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሂሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሰራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው ምንም አይነት ኮድ የለም፡፡
በመሆኑም ማንኛውም የባንካችን ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል ስለሁኔታው መረጃ መጠየቅ እንዳለበት እናሳስባለን፡፡
18.8K viewsBiniam zewdie, 13:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 15:08:36
ካርድዎን አልያዙም?
በሲቢኢ ብር ያለካርድ ከኤቲኤም ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ!
========
በሲቢኢ ብር አገልግሎት አማካኝነት በኤቲኤም ማሽን ብር ወጪ እንዲሆን በማዘዝ እና በኤቲኤም ማሽኑ የሚጠየቁትን ብር የተላከበትን የስልክ ቁጥር፥ የሚስጥር ቁጥር እንዲሁም የተላከውን የገንዘብ መጠን በማስገባት ያለካርድ ገንዘብ ማውጣት ይችላሉ፡፡

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
18.3K viewsH, edited  12:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-02 10:02:50
ለተሻለ ነገ...
የትምህርት ቁጠባ ሂሳብ
===============
የርስዎንም ሆነ የልጆችዎን የከፍተኛ ትምህርት ወጪ ለመሸፈን
የትምህርት ቁጠባ ሒሳብ ተጠቃሚ ይሁኑ!

#CBE #education #saving #ትምህርት #ቁጠባ #ሂሳብ #ወላጆች #ከፍተኛትምህርት #ገንዘብ
12.7K viewsH, 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 20:26:46
ከ 305 ሺ እስከ 108 ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ስለማውጣት
******************************
በባንኩ የሲስተም ማዘመኛ ሥራ ላይ የተፈጠረውን ክፍተት በመጠቀም መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. ያለአግባብ ከባንካችን የወሰዱትን ገንዘብ እንዲመልሱ እስከ መጋቢት 21 ቀን 2016 ዓ.ም በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ መሠረት 10,857 የሚሆኑ ግለሰቦች ያለባቸውን ገንዘብ አጠናቀው መልሰዋል፡፡

ነገር ግን የተሰጠውን ተደጋጋሚ እድል ተጠቅመው ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦች አሉ፡፡ በመሆኑም ባንካችን ገንዘቡን ለማስመለስ በተከታታይ ስለሚወስዳቸው እርምጃዎች በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሠረት እስካሁን ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን የመጀመሪያ ዙር ፎቶግራፍ በባንካችን ድረ-ገጽ እና የማህበራዊ ትስስር ገፆች ለማውጣት ተገደናል፡፡

በዚህ አጋጣሚ ባንካችን የተለያዩ ምክንያቶችን ግምት ውስጥ በማስገባት የገንዘብ መመለሻ ጊዜውን ለመጨረሻ ጊዜ እስከ መጋቢት 25 ቀን 2016 ዓ.ም ያራዘመ በመሆኑ፣ ይህን የመጭረሻ እድል ተጠቅማችሁ ገንዘቡን እድትመልሱ እያሳሰብን፣ በተሰጠው የጊዜ ገደብ የማይመልሱትን ወደ ህግ የምናቀርብ መሆኑን በድጋሚ እናሳስባለን፡፡
የግለሰቦችን ማንነት የሚያሳዩ መረጃዎችን ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መመልከት ይችላሉ ።
https://combanketh.et/list-of-customers
18.0K viewsBiniam zewdie, 17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 13:18:09
ከውጭ ሀገር ገንዘብ ለመላክ በርካታ አማራጮች!
****************
ከውጭ ሀገር በመረጡት ዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ገንዘብ ያስልኩ፤
ወዲያውኑ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ይቀበሉ!

#CBE #international #moneytransfer #service #ንግድ #ባንክ #ዓለምአቀፍ #የገንዘብ #አስተላላፊ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
17.3K viewsH, 10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-01 10:10:23
እጥፍ ወለድ....
********
ከባህር ማዶ ገንዘብ ሲላክልዎ፤
አዲሱን የውጭ ሐዋላ የቁጠባ ሂሳብ ይክፈቱ!

• ከመደበኛው ሂሳብ እጥፍ ወለድ ያስገኛል ፣
• ለውጭ ሀገር ጉዞዎ ቅድሚያ የውጪ ምንዛሬ አገልግሎት እና
• የሞባይል ካርድ ስጦታም ያገኛሉ ።

ይቆጥቡ፤ የበለጠ ያግኙ!
#CBE #saving
17.0K viewsH, 07:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ