Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.57K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-03-22 19:28:24
15.4K viewsBiniam zewdie, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 19:28:23
14.7K viewsBiniam zewdie, 16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 19:28:18 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲቢኢ ኑር የባንክ አገልግሎት የኢፍጣር መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ አከናወነ።
======================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1445ኛውን የረመዷን ፆምን በማስመልከት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለደንበኞቹ  መልካም ምኞት ለመግለጽ እና ያለውን አጋርነት  ለማሳየት ዛሬ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት የኢፍጣር ሥነ-ሥርዓት በሸራተን አዲስ ሆቴል አከናውኗል፡፡

በመርሐ-ግብሩ ላይ ለተገኙ እንግዶች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የባንኩ የሲቢኢ ኑር አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ኑሪ ሁሴን የዘንድሮውን የኢፍጣር መርሀ ግብር ለየት የሚያደርገው ባንኩ ከውለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት የጀመረበትን 10ኛ ዓመት በድምቀት ባከበረ ፣ የሲቢኢ ኑር ተቀማጭ ገንዘብ 100 ቢሊዮን በተሻገረበት እንዲሁም የዘጠነኛው ዓለም አቀፍ የኢስላሚክ ሪቴይል ባንኪንግ ሽልማት ባገኘበት ማግስት መሆኑን ገልፀዋል።

በኢፍጣር መርሐ ግብሩ ላይ በመገኘት መልእክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ሼህ ሙሀመድ ሀሚዲን ባንኩ የሸሪዓ መርሆዎችን የተከተለ አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ገልፀው፣ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከባንኩ ጋር በጋራ በመሆን  አገልግሎቱን ማሳደግ እንደሚጠበቅበት ተናግረዋል።
 
የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሀጂ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው የኢፍጣር መርሀ ግብሩን በዘጉበት ንግግር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሙስሊሙ ማህብረሰብ ትልቅ ባለውለታ መሆኑን በመግለፅ ምስጋና አቅርበዋል።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የመንግስት የሦራ ኃላፊዎች፣ የሃይማኖቱ አባቶች፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሲቢኢ ኑር የሸሪዓ መማክርት ኮሚቴ አባላት፣ ደንበኞች እና የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ156 ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ብቻ በሚሰጡ ቅርንጫፎች እንዲሁም ከ1,940 በላይ በሚሆኑ ቅርንጫፎች ለአገልግሎቱ ብቻ በተለየ መስኮት የሲቢኢ ኑር ከወለድ ነፃ የባንክ  አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ባንካችን ቀሪው የረመዷን ወር በሰላም እንዲፈፀም  መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
13.4K viewsBiniam zewdie, edited  16:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 17:32:26
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለእስልምና እምነት ተከታይ ደንበኞቹ የኢፍጣር መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል በዛሬው እለት ያከናውናል።
14.8K viewsH, 14:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-22 09:57:11
ለሐጅ መንገደኞች ልዩ መስተንግዶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
*******************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሐጅ መንገደኞች
የቅድመ ጉዞ የተቀላጠፈ የባንክ አገልግሎት
ልዩ መስተንግዶ በሁሉም ቅርንጫፎቻችን እየሰጠ ይገኛል፡፡

#ሐጅ #መንገደኞች #ልዩ #አገልግሎት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !
16.8K viewsH, 06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 22:17:04
የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም ያለአግባብ የተወሰደን ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ እንደሚቻል ስለማሳወቅ
===========================
ባንካችን አንዳንድ ግለሰቦች ያለአግባብ የወሰዱትን የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመገኘት እንዲመልሱ ጥሪ ባደረገው መሰረት በርካታ ግለሰቦች በቅርንጫፎች እየቀረቡ ገቢ እያደረጉ ቢሆንም ተጨማሪ የመመለሻ ኣማራጭ መስጠት ጠቃሚ እንደሆነ ታምኖበታል::

ስለዚህ ከቅርንጫፎች በተጨማሪ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችንም በመጠቀም በቀጥታ ቀድሞ ገንዘቡ አለአግባብ ወጪ ወደተደረገበት በባንካችን የሚገኝ የባንክ ሂሳባችሁ ማስተላለፍ (transfer) እና ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።
18.7K viewsBiniam zewdie, 19:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-21 10:17:51 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የራሳቸው ያልሆነን ገንዘብ የወሰዱ ወይም ወደተለያየ ሂሳቦች ያስተላለፉ ግለሰቦች እስከ መጪው ቅዳሜ ድረስ በፈቃዳቸው እንዲመልሱ ያሳስባል።
==≠=========================
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካጋጠመው የሲስተም ችግር ጋር ተያይዞ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ የወሰዱና ያልተገባ የገንዘብ እንቅስቃሴ ካከናወኑ ግለሰቦች መካከል ብዙዎች የተደረገላቸውን ጥሪ ኣክብረው የራሳቸው ያልሆነውን ገንዘብ ወደ ባንኩ ቅርንጫፎች እየቀረቡ እየመለሱ በመሆኑ ከስህተታቸው የመመለስ በጎ ምላሽነቱን እናደንቃለን። እስካሁን ቀርበው ገንዘቡን ተመላሽ ያላደረጉ ግለሰቦችም እስከመጪው ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመቅረብ ተመላሽ እንዲያደርጉ ባንካችን የመጨረሻ ጥሪ ያቀርባል፡፡
ይሁን እንጂ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ተጠቅመው አላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦች ላይ ደረጃ በደረጃና በተከታታይ የተለያዪ ጠንከር ያሉ እርምጃዎች ለመውሰድ እንደሚገደድ እንገልፃለን::
ከታቀዱት ዋና ዋና እርምጃዎች መካከል የሚከተሉት እንዳሉ እንዲታወቁ ይፈለጋል:-
1. ከሕግ አካላት ጋር በመተባበር የግለሰቦችን ሥም ዝርዝር በየቅርንጫፎች እና እንደሁኔታው ግለሰቦቹ ሊታወቁ በሚችሉበት ኣካባቢ ይፋ በማድረግ ቀጣይ ሕጋዊ እርምጃዎችን እንዲቀጥሉ እንደሚደረግ እንገልጻለን፡፡
2. ⁠ከዚህ በላይ በተጠቀሰው እርምጃ መሰረት ኣሁንም ቀርበው የማይመልሱ ከሆነ በሕጋዊ ሂደቱ ተገቢው ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ በድርጊቱ የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ፎቶግራፋቸውን እና ዝርዝር ማንነታቸውን የሚገልፁ መረጃዎች ባንኩ በመረጠው የብዙሀን መገናኛ መንገድ ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ያሳስባል፡፡
3. ⁠ከዚሁ በላይ ከተጠቀሱት እርምጃዎች ጎን ለጎንም ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ የወሰዱትን ገንዘብ እስከ ቅዳሜ ተመላሽ የማያደርጉ ግለሰቦችን ከፍትህ አካላትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመተባበር ተገቢውን የወንጀል፣የፍትሐ ብሔርና አስተዳደራዊ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እንደሚያደርግ ያሳስባል።
15.0K viewsBiniam zewdie, 07:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-20 10:28:56 ትላንት፣ ዛሬ፣ ነገ....
የትውልዶች ቀዳሚ ምርጫ!

ቀዳሚ መሆንን ምርጫቸው ያደረጉ
የሚተማመኑበትን ያውቃሉ!
****
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !



19.6K viewsH, 07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-19 12:29:15
የጥንቃቄ መልዕክት
**************

አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል፡፡

እነዚህ አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “የተዘጋ ሂሳብችሁን እንክፈትላችሁ” ፤ “ሂሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡

ነገር ግን ባንካችን ስልክ ደውሎ ስለ ሂሳብዎ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሂሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሰራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው ምንም አይነት ኮድ የለም፡፡

በመሆኑም ማንኛውም የባንካችን ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል ስለሁኔታው መረጃ መጠየቅ እንዳለበት እናሳስባለን፡፡
24.0K viewsH, 09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-19 10:24:49
መተግበሪያዎን ሲቢኢ ብር ላይ ያስቀምጡ
በቀላሉ በርካታ ደንበኞች ዘንድ ይድረሱ!

#CBE #cbebirr #apps #digitalbanking
*************
የሲቢኢ ብር መተግበሪያ ማስፈንጠሪያ፡

• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
258.5K viewsH, 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ