Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.57K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2024-03-31 20:50:47
ገንዘብ ተመላሽ ለማድረግ የመጨረሻ የሶስት ቀናት ስለመስጠት፤
=============================== https://www.facebook.com/share/p/yJRtv4nbECrAgfiJ/?mibextid=Nif5oz
18.1K viewsBiniam zewdie, 17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 19:54:17
በድሬዳዋ ከተማ የተካኤደው 19ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከድሬዳዋ ከተማ ገጥሞ በአቻ ውጤት ተለያየ።
=======
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የሁለቱ ጨዋታ በሁለቱም በኩል በርካታ ደጋፊዎች በስታዲየሙ የተገኙ ሲሆን ድሬዳዋ ከተማ በ 14 ደቂቃ ላይ በቻርለስ ሙሴጌ አማካኝነት በማስቆጠር እስከ 80ኛ ደቂቃ የቆየ ሲሆን ሳይመን ፒተር ለንግድ ባንክ በማስቆጠር 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ጨዋታው ተጠናቋል።
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ 19ኛ ሳምንት ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመሪው መቻል በሁለት ነጥብ ዝቅ ብሎ በ37 ነጥብ እና በ13 ንጹህ ጎል ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
16.6K viewsBiniam zewdie, 16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 17:54:34
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
15.5K viewsBiniam zewdie, 14:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 17:46:40
16.5K viewsBiniam zewdie, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-31 17:46:37
13.7K viewsBiniam zewdie, 14:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-30 15:35:17
ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!
************
አጭበርባሪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የስርቆት ተግባር ይፈፅማሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም እና አሳሳች ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት የማጭበርበር ሙከራዎች በስፋት እየታዩ ነው፡፡ ‘የኦንላይን ሥራ በመሥራት ገንዘብ ታገኛላችሁ’ በማለት የሚያጭበረብሩት ከነዚህ ውስጥ ይገኙበታል፡፡

ከሥር ባያያዝናቸው ምስሎች እንደሚታየው ‘Chelezo Heights’ በሚል ስያሜ በተከፈተ የፌስቡክ ገፅ እንዲሁም ‘ETHIOPIAN ONLINE WORKS’ በሚል ስያሜ በተከፈተ የቴሌግራም ገፅ አጭበርባሪዎች በኦንላይን ሥራ ገንዘብ አግኙ የሚል አሳሳች መልእክት እያስተላለፉ ናቸው፡፡

እነዚህ ገፆች ETHIOPIA ONLINE JOBS በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተከፈተ ሂሳብ ለተጠቃሚዎች ገንዘብ የተላለፈ በማስመሰል የተሠሩ ሀሰተኛ የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫዎችን በማጋራት ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ETHIOPIA ONLINE JOBS በሚል በባንካችን የተከፈተ ሂሳብም የለም የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫዎቹም ሀሰተኞች ናቸው፡፡
በመሆኑም ውድ ደንበኞቻችን በመሰል አሳሳች መልእክቶች እንዳትጭበረበሩ እያሳሰብን ማንኛውም የባንካችን ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ሳያረጋግጥ ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ ስለሁኔታው ማጣራት እንዳለበት እንጠቁማለን። ለበለጠ መረጃ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል።
12.7K viewsBiniam zewdie, 12:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 17:14:11
15.3K viewsH, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-29 17:14:09
15.0K viewsH, 14:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-28 11:34:13
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገለፀ፡፡
******************
ይህ የተገለፀው መጋቢት 16፣ 2016 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መሥሪያ ለተገኘው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የባንኩ የ2023/24 በጀት ዓመት የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት በቀረበበት ወቅት ነው፡፡

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ፕሮፌሰር መሐመድ አብዱ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሀገር የልማት እንቅስቃሴ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ያለ ባንክ ነው፡፡

ባንኩ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ውስጥ የሚጠብቀበትን እየተወጣ እንዲቀጥል እና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስቀመጠውን ግብ ለማሳካት ይረዳው ዘንድ ደግሞ የባለድርሻ አካላት የፖሊሲን ጨምሮ ተገቢውን ድጋፍ ሊያደርጉለት እንደሚገባ ዋና ሰብሳቢው አሳስበው፣ ቋሚ ኮሚቴው አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

የተከበሩ ፕሮፌሰር መሐመድ ባንኩ በወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ዘርፍ የሠራው ሥራ የሚያስመሰግነው እንደሆነም ነው የገለፁት፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ባንኩ ማህበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣበትንም መንገድ ዋና ሰብሳቢው አድንቀዋል፡፡

የቋሚ ኮሚቴው አባላት የባንኩን የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት መነሻ በማድረግ ላነሷቸው ጥያቄዎች የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖን ጨምሮ የሚመለከታቸው የባንኩ ምክትል ፕሬዚዳንቶች ሰፊ ማብራሪያና ገለጻ መስጠታቸው እና የቋሚ ኮሚቴው አባላት ሳምንቱን ሙሉ ለ24 ሰዓት የሚሠራውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመረጃ ደህንነት ሥርዓት ተዘዋውረው መጎብኘታቸው ይታወሳል፡፡
12.6K viewsH, 08:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-25 18:27:40
15.6K viewsH, 15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ