Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.57K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2024-03-18 20:58:48
ባለፉት ስምንት ወራት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ከ10 ትሪሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ዝውውር ተካሄደ፡፡
********************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሪዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለፁት ባለፉት ስምንት ወራት በባንኩ ዲጂታል አገልግሎቶች በተከናወኑ ከ800 ሚሊዮን በላይ ግብይቶች ከ10 ትሪሊዮን በላይ የገንዘብ ዝውውር ተፈፅሟል፡፡ ይህም ከአጠቃላዩ የገንዘብ ዝውውር 73 በመቶ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


ባንኩ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ባንክ ለመሆን በሚያደርገው እንቅስቃሴ በአሁኑ ጊዜ የለውጥ ሥራ ላይ መሆኑን የገለፁት አቶ አቤ፣ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን ወደላቀ ደረጃ ማድረስ ደግሞ የለውጡ ሥራ አንዱ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


አቶ አቤ 32 ሚሊዮን የዲጂታል ባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ ደንበኞች በባንኩ እንዳሉ እና በየቀኑ 4 ሚሊዮን ደንበኞች በዲጂታል አገልግሎት እንደሚስተናገዱ ገልፀዋል፡፡


የባንኩን ዲጂታል አገልግሎቶች ደህንነት አስተማማኝ ለማድረግ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ስርዓት መዘርጋቱን የገለፁት አቶ አቤ፣ በአሁኑ ጊዜ የባንኩ የመረጃ ደህንነት ሥራ አመራር እጅግ ዘመናዊ፣ በስርዓት የሚመራ እና በቴክኖሎጂ እና በብቁ ባለሙያዎች የተደገፈ በመሆኑ በሀገራችን ላሉ ለሁሉም የፋይናንስ እና ሌሎች ተቋማት እንደማሳያ የሚሆን ቁመና ያለው መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በዚህም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች የደህነነት ማረጋገጫ እውቅና እንዳገኘ አስረድተዋል፡፡
23.1K viewsBiniam zewdie, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 19:35:53
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ ገለፀ፡፡
• የደንበኞች የግል ሂሳብ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አልደረሰም
*****

መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከሲስተም ማሻሻያ ትግበራ ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ችግር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ደንበኞች ስጋት ላይ የሚጥል ክስተት እንዳልተፈጠረ ተገልጿል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አቶ አቤ ሳኖ እንደገለፁት በወቅቱ በተከሰተው ችግር የባንኩ ደንበኞች ሂሳብ ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም፡፡


አቶ አቤ ባንኩ እድርጎት በነበረ የሲስተም ማሻሻያ ክፍተት ምክንያት መጋቢት 7 ከሌሊቱ ጀምሮ ለተወሰኑ ሰዓታት የቆየ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውር የነበረ ቢሆንም ከሌሎች የባንኩ ደንበኞች ሂሳብ ጋር እንደማይገናኝ ገልፀዋል፡፡


ችግሩ በተከሰተበት ሰዓት ውስጥ ከ490 ሺ በላይ የገንዘብ ዝውውር እንደነበረ የገለፁት አቶ አቤ፣ በወቅቱ በዝውውር ውስጥ የተሳተፉ ሂሳቦችን በማገድ በባንኩ ላይ ሊደርስ የነበረውን ጉዳት መቀነስ እንደተቻለ አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡


ባንኩ በአሁኑ ጊዜ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን ለይቶ የጨረሰ ሲሆን፣ ከሌሎች ባንኮች እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ቀጣይ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ አቶ አቤ ገልፀዋል፡፡


ከኤቲኤም በህገወጥ መንገድ ገንዘብ ያወጡ ግለሰቦች በፈቃደኝነት ገንዘቡን እየመለሱ መሆኑን አቶ አቤ ገልፀው፣ ፈቃደኛ በማይሆኑት ላይ ከሚመለከተው የህግ አካል ጋር በመተባበር ገንዘቡ ተመላሽ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡

ከባንኩ በህገወጥ መንገድ የወጣው ጥሬ ገንዘብ መጠን የማጣራት ሥራ እየተሠራ..
ለተጨማሪ
https://www.facebook.com/photo/?fbid=805559308269984&set=pcb.805559418269973
21.7K viewsBiniam zewdie, edited  16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 17:57:32
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት ተገለፀ፡፡
• ባንኩ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ስርዓት አለው ተብሏል፡፡
**********************

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በቅርንጫፍ እና በዲጂታል የባንክ አገልግልቶቹ ላይ ለተወሰኑ ሰዓታት የአገልግሎት መቋረጥ ማጋጠሙ ይታወቃል፡፡


ይህን በማስመልከት በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ባንኩ ምንም አይነት የሳይበር ጥቃት እንዳልደረሰበት ገልፀዋል፡፡


ባንኩ ላይ የተለያዩ የሳይበር ጥቃት ሙከራዎች በየጊዜው እንደሚደረጉ እና ባንኩ ባለው እጅግ ጠንካራ የሳይበር ደህንነት ስርዓት እንደሚመከቱ የገልፁት አቶ አቤ አሁን የተፈጠረው ችግር በሲቢኢ ብር እና በሞባይል ባንኪንግ አገልግሎቶች ላይ ተደርጎ በነበረ አዲስ የሲስተም ማሻሻያ ትግበራ ክፍተት መሆኑን ገልፀዋል፡፡


ባንኩ የዲጂታል አገልግሎቶቹን ይበልጥ በማዘመን እና ለደንበኞች ይበልጥ ምቹ ለማድረግ በየጊዜው ማሻሻያዎችን ይተገብራል ያሉት አቶ አቤ፣ አሁን የተፈጠረውን ችግር በማጣራት ላይ መሆኑን ገልፀዋል፡፡


አቶ አቤ በቅርንጫፎች እና በዲጂታል የባንኩ አገልግሎቶች ላይ መቋረጥ የገጠመው ሲስተሙ አልሠራ ባለማለቱ ሳይሆን፣ አዲስ ተግባራዊ ተደርጎ በነበረው የሲስተም ማሻሻያ ሳቢያ በተፈጠረ ክፍተት የተደረጉ ህገወጥ የገንዘብ ዝውውሮችን በመለየት ለማገድ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሳይበር ደህንነት በተለያዩ ዓለም አቀፍ መመዘኛዎች የደህነነት ማረጋገጫ እንዳገኘ አቶ አቤ ገልፀው፣ በዚህ ረገድ ደንበኞች ስጋት ሊገባቸው እንደማይገባ አረጋግጠዋል፡፡
25.2K viewsBiniam zewdie, 14:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-18 15:46:09
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰሞኑን በውስጥ ሲስተም ችግር ምክንያት የአገልግሎት መስተጓጎል አጋጥሞት እንደነበር ይታወቃል። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ጋዜጣዊ መግለጫ በዋናው መ/ቤት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ ይሰጣል።
22.5K viewsBiniam zewdie, edited  12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-17 22:49:00
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት በጊዜያዊነት መቋረጥን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ መግለጫ
*****

መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጅታል የባንክ ሥርዓት ላይ ባጋጠመ ችግር ምክንያት የባንኩ መደበኛ አገልግሎቶች ለተወሰኑ ሰዓታት መቋረጣቸዉ ይታወቃል፡፡

እንደሚታወቀው ቀልጣፋና ደህንነቱ የተጠበቀ አገልግሎት ለመስጠት ባንኮች በሥርዓቶቻቸዉ ላይ በየጊዜዉ የደህንነት ፍተሻ እንዲሁም የማሻሻያ ሥራዎችን ያከናዉናሉ፡፡ በሥርዓቶቹ ላይ በሚከናወን ለዉጦችና ፍተሻዎችም የባንኮች አገልግሎት አልፎ አልፎ ሊቋረጥ ይችላል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትናንትናው ዕለት የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ከዚሁ ጋር የተያያዘ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

ችግሩ ከተከሰተበት ሰዓት አንስቶ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የባንኩን እና የደንበኞቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። በመሆኑም የባንኩ መደበኛ አገልግሎቶች በአጭር ጊዜ ዉስጥ እንዲጀምሩና ባንኩ ወደተለመደው እንቅስቃሴው እንዲመለስ ማድረግ ተችሏል፡፡

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ላይ የተከሰተዉ የአገልግሎት መቋረጥ ባንኩ በመደበኛነት በሥርዓቶቹ ላይ በሚያደርገዉ ማሻሻያና ፍተሻ ምክንያት የተከሰተ እንጂ የባንኩን፣ የደንበኞቹን እንዲሁም አጠቃላይ የፋይናንስ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ክስተት አለመሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

ሙሉውን መግለጫ ይህን ማስፈንጠረያ ይጫኑ https://www.facebook.com/share/p/NfFKPWGURamDzATU/?mibextid=Nif5oz
28.4K viewsBiniam zewdie, 19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 20:14:37
ለውድ የባንካችን ደንበኞች የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን እንገልፃለን።
===============================
በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር መግለፃችን ይታወቃል።
በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ያሳወቅን ሲሆን አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን እናሳውቃለን።
ውድ ደንበኞቻችን በትእግስት ስለጠበቃችሁን እያመሰገንን ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።
15.8K viewsBiniam zewdie, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 15:19:11
የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ጀምሯል!
• ሀሰተኛ መረጃን ስለማሳወቅ
*************************
ለክቡራን ደንበኞቻችን በቅርንጫፎች አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ቀደም ብለን ያሳወቅን ሲሆን አሁን ደግሞ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እንገልጻለን። በቀጣይም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ የምናስጀምር ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል በሲስተም ችግር ምክንያት በባንካችን በጊዜያዊነት የተከሰተውን የአገልግሎት መስተጓጎልን ምክንያት በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ትስሥር ገፆች በመዘዋወር ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል፡፡

በባንካችን የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንካችን የውስጥ የሲስተም ችግር እንጂ ፣ በሀሰት እንደሚሰራጨው ከባንኩ ውጭ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አለመሆኑን እየገለፅን፣ ባንካችን አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ያለው መሆኑን በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞች ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው እያሳሰብን፣ ችግሩን በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል አየሠራን መሆኑን እንገልፃለን፡፡
21.0K viewsH, edited  12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 13:13:17
ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል!
ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል!
************
ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ፡

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት የጀመረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እየገለፅን፣ የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡ እናሳውቃለን፡፡

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፥ ሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም ሲቢኢ ብር) ለማስጀመር እየሠራን መሆኑን እየገለፅን፣ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።
23.2K viewsH, 10:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-16 10:08:54
ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ
================================
በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሟል።

አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ በመሆኑ ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን እየጠየቅን፣ ለተፈጠረው መጉላላት ይቅርታ እንጠይቃለን።
25.9K viewsH, 07:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-15 21:16:48
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል ጨዋታ በመቻል ሁለት ጎሎች አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
===============================
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመጀመሪያዎቹ ደቂቃዎች በመቻል በተቆጠረበት ሁለት ተከታታይ ግቦች የ18ኘውን የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በ ነበረው 36 ነጥብ አጠናቀቀ። በመቻል በኩል ምንይሉ ወንድሙ በ3 ኛው እና አቤል ነጋሽ በ 6ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች ነው በማሸነፍ በእኩል 36 ነጥብ በጎል ክፍያ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበልጦ ሁለተኛ ሆኗል።
22.1K viewsBiniam zewdie, 18:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ