Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 120.27K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2024-03-10 18:04:25
17.3K viewsBiniam zewdie, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 18:04:13
16.6K viewsBiniam zewdie, 15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-07 16:50:49
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን
******
እንኳን ለማርች 8 የሴቶች ቀን አደረሳችሁ!
በአሜሪካን ሀገር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1908 ብዛታቸው 15 ሺ የሚሆኑ ሴቶች የተሻለ ደመወዝ፣ የሥራ ቦታ ፣ ጥሩ የሥራ አካባቢና የሥራ ሰዓት ማስተካከያ እንዲሁም የሴቶች የመምረጥ መብት እንዲከበር ለመጠየቅ ወደ አደባባይ ወጡ፡፡
ሴቶች በአደባባይ ወጥተው ነፃነታቸውን የጠየቁበትን ቀን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት "የሴቶች ቀን ብሎ " በማወጅ ዓለም አቀፍ ይዘት ኖሮት በየዓመቱ እንዲከበር በ1975 እ.ኤ.አ ውሳኔ አስተላለፈ።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የመጣ ሲሆን ዘንድሮም “ሴቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ፡ እድገትን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በዓለማቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በዓለማችን እንዲሁም በሀገራችን የሴቶቹ ትግል ፍሬ አፍርቶ በአሁኑ ጊዜ የ ሴቶች መብት እየተከበረ ወደ አመራርነት እየመጡ እና ተፅዕኖ እየፈጠሩ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከቅጥር ጀምሮ በተለያዪ ደረጃዎች ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ከሥራ አስኪያጅነት እስከ ምክትል ሥራ አስፈፃሚነት ደረጃ መድረስ ችለዋል ። በተጨማሪም ባንኩ በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለደንበኞቹ ተደራሽ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በመላው ዓለም ለምትገኙ ሴቶች በሙሉ እንኳን ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።
መልካም በዓል!
13.2K viewsB, edited  13:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-06 18:58:48
ከሲቢኢ ብር ወደ ባንክ ሒሳብዎ ገንዘብ ሲያስተላልፉ ክፍያው ነጻ ነው።
ሲቢኢ ብርን ከ play store እና app store ማግኘት ይችላሉ።
መተግበሪያን ለማውረድ፡
• ለአንድሮይድ ስልኮች፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbe.birr
• ለአፕል ስልኮች፡ https://apps.apple.com/us/app/cbebirr/id1600841787
15.0K viewsBiniam zewdie, 15:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-05 15:38:20
ለክቡራን የባንካችን ደንበኞች
===============================
በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ በሚሰራው የመንገድ ግንባታ ምክንያት በመንገዱ አቅራቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማለትም ራስ መኮንን ፣ብርሃንና ሰላም እንዲሁም መንበረ ፀሐይ ፓትርያርክ ቅርንጫፎች በኔትወርክ ብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን በሌሎች ዙርያውን በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች እና በሁሉም የዲጂታል አማራጮች የባንክ አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
የኔትወርክ መስመሩ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ወዲያውኑ የምናሳውቅ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
13.3K viewsBiniam zewdie, 12:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-04 15:34:35 #ዜና
በሲቢኢ ኑር አገልግሎት ላይ የተደረጉ የአሠራር ማሻሻያዎች ለአገልግሎቱ ተደራሽነት እገዛ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ፡፡
********
የሲቢኢ ኑር 10ኛ ዓመት ክብረ በዓል ማጠቃለያ ፕሮግራም በባንኩ ዋና መሥሪያቤት በልዩ ልዩ መርሐግብሮች ተከናውኗል፡፡
በመርሐግቡሩ ላይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ እንደተናገሩት መንግስት ሥራላይ ያዋላቸውን የአሠራር ማሻሻያዎችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ይሰጥ በነበረው ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት ላይ የመዋቅር የዐሠራር እና የአገልግሎት አሠጣጥ ለውጦች አድርጎል፡፡ እነዚህ የአሠራር ማሻሻያና ለውጦች ደንበኞችን በከፍተኛ ደረጃ ተጠቃሚ አድርገዋል ነው ያሉት፡፡



#ሲቢኢ ኑር #ከወለድነፃ #ባንክ #አገልግሎት #መዋቅር #ዐሠራር
13.4K viewsB, 12:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-04 10:34:32 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ አገልግሎት መተግበሪያ በሚያዘምኑበት ጊዜ ይህን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
*************** *******
ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖረው በማድረግ ብቻ ካለምንም ተጨማሪ ሰው እገዛ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት መተግበሪያቸውን ለማዘመን ይችላሉ፡፡
የባንኩን የሞባይል ባንክ አገልግሎት እና የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎችን ለማዘመን እና ለማውረድ Play Store ወይም App Store ብቻ መጠቀም አለባቸው።
ደንበኞች የሞባይል ባንክ አገልግሎን ለማዘመን በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ አገልግሎት እንደሌለ በማወቅ ተመሳሳይ መልእክቶች ሲደርሳቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም ወደ 951 በመደወል ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !



#ሞባይልባንኪንግ #ደንበኞች #ማዘመን #መተግበሪያ
13.3K viewsB, 07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-03 21:02:51
በ16ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪነቱን ተረከበ።
============================
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና አዳማ ከነማ በድሬዳዋ ስታዲየም ባደረጉት የእግር ኳስ ጨዋታ ንግድ ባንክ 4ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን በ35 ነጥብ ሊጉን መምራት ጀምሯል።
13.9K viewsBiniam zewdie, 18:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-03 20:57:56
ጎል!!!!!!የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራተኛውን ጎል በሳይመን ፒተር በደቂቃ ጎል 94 ኛው ደቂቃ አስቆጠረ።
============================
12.7K viewsBiniam zewdie, 17:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-03 19:19:02
ጎል!!!!!!የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመጀመሪያውን ጎል በ ኪቲካ ጅማ አስቆጠረ።
==========================
12.8K viewsBiniam zewdie, 16:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ