Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ አገልግሎት መተግበሪያ በሚያዘምኑበት ጊዜ ይህን ጥንቃቄ እ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንክ አገልግሎት መተግበሪያ በሚያዘምኑበት ጊዜ ይህን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ይመከራል፡፡
*************** *******
ደንበኞች የእጅ ስልካቸውን የኢንተርኔት አገልግሎት እንዲኖረው በማድረግ ብቻ ካለምንም ተጨማሪ ሰው እገዛ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት መተግበሪያቸውን ለማዘመን ይችላሉ፡፡
የባንኩን የሞባይል ባንክ አገልግሎት እና የሲቢኢ ብር መተግበሪያዎችን ለማዘመን እና ለማውረድ Play Store ወይም App Store ብቻ መጠቀም አለባቸው።
ደንበኞች የሞባይል ባንክ አገልግሎን ለማዘመን በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ አገልግሎት እንደሌለ በማወቅ ተመሳሳይ መልእክቶች ሲደርሳቸው ወደ ባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም ወደ 951 በመደወል ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ !



#ሞባይልባንኪንግ #ደንበኞች #ማዘመን #መተግበሪያ