Get Mystery Box with random crypto!

ለክቡራን የባንካችን ደንበኞች =============================== በአዲስ አበባ አራ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ለክቡራን የባንካችን ደንበኞች
===============================
በአዲስ አበባ አራት ኪሎ አካባቢ በሚሰራው የመንገድ ግንባታ ምክንያት በመንገዱ አቅራቢያ በሚገኙ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ማለትም ራስ መኮንን ፣ብርሃንና ሰላም እንዲሁም መንበረ ፀሐይ ፓትርያርክ ቅርንጫፎች በኔትወርክ ብልሽት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አልቻሉም፡፡ ስለሆነም ክቡራን ደንበኞቻችን በሌሎች ዙርያውን በሚገኙ የባንካችን ቅርንጫፎች እና በሁሉም የዲጂታል አማራጮች የባንክ አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ልናሳውቃችሁ እንወዳለን።
የኔትወርክ መስመሩ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ ወዲያውኑ የምናሳውቅ መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!