Get Mystery Box with random crypto!

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ****** እንኳን ለማርች 8 የሴቶች ቀን አደረሳችሁ! በአሜሪካን ሀገር | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን
******
እንኳን ለማርች 8 የሴቶች ቀን አደረሳችሁ!
በአሜሪካን ሀገር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1908 ብዛታቸው 15 ሺ የሚሆኑ ሴቶች የተሻለ ደመወዝ፣ የሥራ ቦታ ፣ ጥሩ የሥራ አካባቢና የሥራ ሰዓት ማስተካከያ እንዲሁም የሴቶች የመምረጥ መብት እንዲከበር ለመጠየቅ ወደ አደባባይ ወጡ፡፡
ሴቶች በአደባባይ ወጥተው ነፃነታቸውን የጠየቁበትን ቀን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት "የሴቶች ቀን ብሎ " በማወጅ ዓለም አቀፍ ይዘት ኖሮት በየዓመቱ እንዲከበር በ1975 እ.ኤ.አ ውሳኔ አስተላለፈ።
ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን (March 8) ላለፉት ዓመታት በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የመጣ ሲሆን ዘንድሮም “ሴቶች ላይ ኢንቨስት ማድረግ፡ እድገትን ማፋጠን” በሚል መሪ ቃል በዓለማቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ በተለያዩ መርሐ ግብሮች እየተከበረ ይገኛል።
በዓለማችን እንዲሁም በሀገራችን የሴቶቹ ትግል ፍሬ አፍርቶ በአሁኑ ጊዜ የ ሴቶች መብት እየተከበረ ወደ አመራርነት እየመጡ እና ተፅዕኖ እየፈጠሩ ይገኛሉ።
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክም ከቅጥር ጀምሮ በተለያዪ ደረጃዎች ሴቶች ወደ አመራርነት እንዲመጡ ትኩረት ተሰጥቶበት እየተሰራ ይገኛል። በዚህም ከሥራ አስኪያጅነት እስከ ምክትል ሥራ አስፈፃሚነት ደረጃ መድረስ ችለዋል ። በተጨማሪም ባንኩ በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጡ ቅርንጫፎችን ከፍቶ ለደንበኞቹ ተደራሽ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክም በመላው ዓለም ለምትገኙ ሴቶች በሙሉ እንኳን ለዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን አደረሳችሁ ለማለት ይወዳል።
መልካም በዓል!