Get Mystery Box with random crypto!

የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ጀምሯል! • ሀሰተኛ መረጃን ስለማሳወቅ ****************** | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ጀምሯል!
• ሀሰተኛ መረጃን ስለማሳወቅ
*************************
ለክቡራን ደንበኞቻችን በቅርንጫፎች አገልግሎት መሰጠት መጀመሩን ቀደም ብለን ያሳወቅን ሲሆን አሁን ደግሞ ተቋርጦ የነበረው የኤቲኤም(ATM) አገልግሎት ሙሉ በሙሉ ስራ የጀመረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እንገልጻለን። በቀጣይም ሁሉንም ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶች ሥራ የምናስጀምር ይሆናል፡፡

በሌላ በኩል በሲስተም ችግር ምክንያት በባንካችን በጊዜያዊነት የተከሰተውን የአገልግሎት መስተጓጎልን ምክንያት በማድረግ ሀሰተኛ መረጃዎች በማህበራዊ ትስሥር ገፆች በመዘዋወር ላይ እንደሚገኙ ለመረዳት ችለናል፡፡

በባንካችን የተከሰተው የአገልግሎት መቋረጥ በባንካችን የውስጥ የሲስተም ችግር እንጂ ፣ በሀሰት እንደሚሰራጨው ከባንኩ ውጭ በደረሰ የሳይበር ወይም ሌላ ተመሳሳይ ጥቃት አለመሆኑን እየገለፅን፣ ባንካችን አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ያለው መሆኑን በድጋሚ እናረጋግጣለን፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘ ደንበኞች ምንም አይነት ስጋት እንዳይገባቸው እያሳሰብን፣ ችግሩን በሰዓታት ልዩነት ሙሉ በሙሉ ለማስተካከል አየሠራን መሆኑን እንገልፃለን፡፡