Get Mystery Box with random crypto!

ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል! ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል! *** | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል!
ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት ይሰጣል!
************
ለውድ የባንካችን ደንበኞች በሙሉ፡

በሲስተም ችግር ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የቅርንጫፎች አገልግሎት የጀመረ መሆኑን ለክቡራን ደንበኞቻችን እየገለፅን፣ የባንኩ ቅርንጫፎች ዛሬ እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት አገልግሎት እንደሚሰጡ እናሳውቃለን፡፡

በተመሳሳይ ዲጂታል የባንክ አገልግሎቶችን (ኢንተርኔት ባንኪንግ፥ ሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም ሲቢኢ ብር) ለማስጀመር እየሠራን መሆኑን እየገለፅን፣ ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።