Get Mystery Box with random crypto!

ለውድ የባንካችን ደንበኞች የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን እንገልፃለን። ===== | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ለውድ የባንካችን ደንበኞች የዲጂታል ባንክ አግልግሎት ሙሉ በሙሉ መጀመሩን እንገልፃለን።
===============================
በሲስተም ችግር ምክንያት በባንኩ አገልግሎቶች ላይ ማለትም በቅርንጫፎች፥ በኢንተርኔት ባንኪንግ፥ በሞባይል ባንኪንግ፥ እንዲሁም በሲቢኢ ብር የአገልግሎት መቋረጥ አጋጥሞ እንደነበር መግለፃችን ይታወቃል።
በቅርንጫፍ እና በኤቲኤም የሚሰጡ አገልግሎቶች ቀደም ብለው መጀመራቸውን ያሳወቅን ሲሆን አሁን ደግሞ በዲጂታል የሚሰጡ የባንክ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ መጀመራቸውን እናሳውቃለን።
ውድ ደንበኞቻችን በትእግስት ስለጠበቃችሁን እያመሰገንን ለተፈጠረው የአገልግሎት መስተጓጎል በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን።