Get Mystery Box with random crypto!

ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ! ************ አጭበርባሪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የስርቆት | Commercial Bank of Ethiopia - Official

ከአጭበርባሪዎች ይጠንቀቁ!
************
አጭበርባሪዎች የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም የስርቆት ተግባር ይፈፅማሉ፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ የማህበራዊ ትስስር ገፆችን በመጠቀም እና አሳሳች ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት የማጭበርበር ሙከራዎች በስፋት እየታዩ ነው፡፡ ‘የኦንላይን ሥራ በመሥራት ገንዘብ ታገኛላችሁ’ በማለት የሚያጭበረብሩት ከነዚህ ውስጥ ይገኙበታል፡፡

ከሥር ባያያዝናቸው ምስሎች እንደሚታየው ‘Chelezo Heights’ በሚል ስያሜ በተከፈተ የፌስቡክ ገፅ እንዲሁም ‘ETHIOPIAN ONLINE WORKS’ በሚል ስያሜ በተከፈተ የቴሌግራም ገፅ አጭበርባሪዎች በኦንላይን ሥራ ገንዘብ አግኙ የሚል አሳሳች መልእክት እያስተላለፉ ናቸው፡፡

እነዚህ ገፆች ETHIOPIA ONLINE JOBS በሚል በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተከፈተ ሂሳብ ለተጠቃሚዎች ገንዘብ የተላለፈ በማስመሰል የተሠሩ ሀሰተኛ የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫዎችን በማጋራት ላይ ናቸው፡፡ ነገር ግን ETHIOPIA ONLINE JOBS በሚል በባንካችን የተከፈተ ሂሳብም የለም የሂሳብ እንቅስቃሴ መግለጫዎቹም ሀሰተኞች ናቸው፡፡
በመሆኑም ውድ ደንበኞቻችን በመሰል አሳሳች መልእክቶች እንዳትጭበረበሩ እያሳሰብን ማንኛውም የባንካችን ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ሳያረጋግጥ ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ ስለሁኔታው ማጣራት እንዳለበት እንጠቁማለን። ለበለጠ መረጃ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል።