Get Mystery Box with random crypto!

Commercial Bank of Ethiopia - Official

የሰርጥ አድራሻ: @combankethofficial
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 116.57K
የሰርጥ መግለጫ

Commercial Bank of Ethiopia is the leading bank in Ethiopia, established in 1942. Pioneer to introduce modern banking to the country with more than 1800 branches across the country.
@ www.facebook.com/combanketh
@ www.twitter.com/combankethiopia

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2024-04-11 18:02:53
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል አድርጓል፡፡
********
በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው 39ኛ ደቂቃ ሀዋሳ ከተማ በዓሊ ሱለይማን ባገኘው ጎል ጨዋታውን እየመራ ቡድኖቹ ወደ እረፍት ያመሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከረፍት መልስ ተጭኖ በመጫወት በ50ኛው ደቂቃ በሲሞን ፒተር እና በ65ኛው ደቂቃ በኪቲካ ጅማ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሊጉ ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 13 አሸንፎ በአራቱ አቻ በመለያየት በአራቱ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በ43 ነጥብ እና በ18 ንፁህ ጎል ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡
14.8K viewsH, 15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 16:51:33
እረፍት
****
የ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 1 ለ 0 መሪነት ወደ እረፍት አምርቷል፡፡

አሊ ሱሌማን በ39ኛው ደቂቃ የሀዋሳ ከተማን ጎል ያስቆጠረ ተጫዋች ነው፡፡
13.1K viewsH, 13:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-08 10:20:32
Vacancy
=======
Commercial Bank of Ethiopia would like to invite qualified and interested job seekers to apply for the following positions:
1. Senior Psychiatry Nurse
2. Senior Biomedical Engineer
3. Neurologist
4. Radiologist
5. Gynecologist
6. Specialist Physician (Internist)
7. General Practitioner
8. Junior Pharmacy Service Officer
9. Junior Psychiatry Nurse

Interested and qualified job seekers should apply through CBE career website
( https://vacancy.cbe.com.et ) from April 08 - 14, 2024.

For requirements and other detail information, please use the following link:
https://combanketh.et/cbeapi/uploads/External_Vacancy_97b7ef4f03.pdf
18.4K viewsH, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-06 16:36:52
ከ 64 ሺ እስከ 53 ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ስለማውጣት (6ኛ ዙር)
**********************************
በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ የማይመልሱ ግለሰቦችን ምስል ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ባንካችን በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሰረት ስድስተኛ ዙር ያልመለሱት የገንዘብ መጠን ከ 64 ሺ እስከ 53 ሺ ብር የሆነ ግለሰቦችን መረጃ ለማውጣት ተገደናል፡፡

የምስል እና ሌሎች መረጃዎችን ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መመልከት ይችላሉ ።

https://combanketh.et/customer-round-six
20.6K viewsBiniam zewdie, 13:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 22:11:04
በኢትዮጵያ የዲጂታል የክፍያ ስርአት እንዲያድግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ከፍተኛ እገዛ ማድረጉ የባንካችን ፐሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።
================
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዘጋጅነት ዛሬ በእስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፡ የፋይናንስ ተቋማት ፡ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት አሁን ለደረሰበት ደረጃ የተጫወተውን ሚና አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል፡፡
አቶ አቤ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታ ባንክ አገልግሎትን ለደንበኞቹ ከማስተዋወቅ እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ ለሌሎችም አርአያ በሚሆን መልኩ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳረገ ጠቁመዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ለዲጂታል የክፍያ ስርአት እድገት የላቀ ሚና እንዲወጣ አስችሎታል ብለዋል።
አቶ አቤ አክለውም ለዲጂታል የክፍያ ስርአት መጎልበት በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፡ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ፡ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና የዘርፉ ተሳታፊዎች በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ መልኩ የዘርፉን ተሳታፊዎች ያሳተፈ የውይይት መድረክ ማሰናዳቱ እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።
በመጨረሻም እንደነዚህ አይነት የውይይት መድረኮች በሀገር አቀፍ ደረጃ በዲጂታል የክፍያ ስርአት ላይ ለሚወጡ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች ከፍተኛ ግብአት የመሆን አቅም ኣላቸው ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ባንኮች ፣የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና የግሉ ዘርፍ ፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡
14.8K viewsBiniam zewdie, 19:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 14:52:35
ከ 71 ሺ እስከ 64 ሺ ያለአግባብ የወሰዱትን ገንዘብ ያልመለሱ ግለሰቦችን ምስል ስለማውጣት (5ኛ ዙር)
**********************************
በተሰጣቸው የጊዜ ገደብ ያላግባብ የወሰዱትን ገንዘብ የማይመልሱ ግለሰቦችን ምስል ከተጨማሪ መረጃዎች ጋር ለህዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ባንካችን በተደጋጋሚ ባሳወቀው መሰረት አምስተኛ ዙር ያልመለሱት የገንዘብ መጠን ከ 71 ሺ እስከ 64 ሺ ብር የሆነ ግለሰቦችን መረጃ ለማውጣት ተገደናል፡፡

የምስል እና ሌሎች መረጃዎችን ከዚህ በታች ባለው ማስፈንጠሪያ መመልከት ይችላሉ ።

https://combanketh.et/customer-round-five
15.4K viewsBiniam zewdie, 11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-05 11:16:13
መልካም የፊቼ - ጫምባላላ በዓል!

Hawalle Sidaamu Daga Diru Soorro Fichee Cambalaallate Ayyaanira Keerunni Iillishi’ne!
Ayyaanu Hagiirrunniha, Keerunniha, Mittimmannihanna Baxillunniha Ikko’ne.

Ayiidde Cambalaalla!
15.0K viewsH, 08:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 22:06:27
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5 ለ 1 በማሸንፍ ወደ መሪነቱ በድጋሚ ተመለስ
********************************
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከሀምበርቾ ጋር ባደረገው ደማቅ ጨዋታ በ24ኛው ደቂቃ ጎል ቢቆጠርበትም ከእረፍት መልስ ባስቆጠረቸው ተከታታይ ጎሎች በብቃት አሸንፎ ሊወጣ ችሏል።
ከተከታታይ ሶስት ጨዋታ በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ 53ኛ እና 72ኛ ደቂቃ አዲስ ግደይ በፍጹም ቅጣት ምት ጎል ሲያስቆጠር በ 65ኛው ካሌብ አማንኩዋ፤ በ 74ኛው ሳይመን ፒተር እንዲሁም 87ኛው ዳዊት ዮሐንስ ባስቆጠሯቸው አምስት ድንቅ ጎሎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብርን በ 40 ነጥብና በ17 ንጹህ ጎል በደረጃው አናት ላይ ተመልሷል።
ዘንድሮ ያደጉትን ሁለቱን ቡድኖች ባገናኘው የምሽቱ ጨዋታ ከበድ ባለ ዝናባማ የአየር ፀባይ ውስጥ ሆኖ የተደረገ ሲሆን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዋንጫ ጉዞው ወሳኝ በመሆኑ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር።
ይህ ውጤት ለቀጣዩ ጨዋታዎችም ከፍተኛ መነቃቃት የፈጠረ ሲሆን ቀሪዎችነም 10 ጨዋታዎች እጅግ አጓጊ ያደርገዋል።
ለባንካችን እግር ኳስ ቡድን እንኳን ድስ አላችሁ ለቀጣዩም መልካም እድል።
17.2K viewsBiniam zewdie, 19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 20:24:13
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 - 1 ሀምበሪቾ
 53' አዲስ ግደይ(ፍ)      24' አላዛር አድማሱ

የ2016 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

በድሬዳዋ ስታዲየም
15.6K viewsBiniam zewdie, 17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-04 12:56:53
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከሀምበርቾ ጨዋታ ያደርጋል፡፡
**********
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከሀምበርቾ ዛሬ፣ መጋቢት 26፣ 2016 ከምሽቱ 1፡00 በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

መቻል ፕሪሚየር ሊጉን በ39 ነጥብ እየመራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ከቅዱስ ጊዮርጊስ በእኩል 37 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ7 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ የሚገኘውን ሀምበርቾ በቀላሉ ያሸንፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መልካም እድል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን!
12.7K viewsH, 09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ