Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል አድርጓል፡፡ ******** በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ድል አድርጓል፡፡
********
በ21ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ሀዋሳ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡

በጨዋታው 39ኛ ደቂቃ ሀዋሳ ከተማ በዓሊ ሱለይማን ባገኘው ጎል ጨዋታውን እየመራ ቡድኖቹ ወደ እረፍት ያመሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከረፍት መልስ ተጭኖ በመጫወት በ50ኛው ደቂቃ በሲሞን ፒተር እና በ65ኛው ደቂቃ በኪቲካ ጅማ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች ጨዋታውን ማሸነፍ ችሏል፡፡

በሊጉ ባደረጋቸው 21 ጨዋታዎች 13 አሸንፎ በአራቱ አቻ በመለያየት በአራቱ የተሸነፈው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በ43 ነጥብ እና በ18 ንፁህ ጎል ሊጉን በመምራት ላይ ይገኛል፡፡