Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5 ለ 1 በማሸንፍ ወደ መሪነቱ በድጋሚ ተመለስ ***************** | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 5 ለ 1 በማሸንፍ ወደ መሪነቱ በድጋሚ ተመለስ
********************************
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከሀምበርቾ ጋር ባደረገው ደማቅ ጨዋታ በ24ኛው ደቂቃ ጎል ቢቆጠርበትም ከእረፍት መልስ ባስቆጠረቸው ተከታታይ ጎሎች በብቃት አሸንፎ ሊወጣ ችሏል።
ከተከታታይ ሶስት ጨዋታ በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ 53ኛ እና 72ኛ ደቂቃ አዲስ ግደይ በፍጹም ቅጣት ምት ጎል ሲያስቆጠር በ 65ኛው ካሌብ አማንኩዋ፤ በ 74ኛው ሳይመን ፒተር እንዲሁም 87ኛው ዳዊት ዮሐንስ ባስቆጠሯቸው አምስት ድንቅ ጎሎች የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብርን በ 40 ነጥብና በ17 ንጹህ ጎል በደረጃው አናት ላይ ተመልሷል።
ዘንድሮ ያደጉትን ሁለቱን ቡድኖች ባገናኘው የምሽቱ ጨዋታ ከበድ ባለ ዝናባማ የአየር ፀባይ ውስጥ ሆኖ የተደረገ ሲሆን ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዋንጫ ጉዞው ወሳኝ በመሆኑ በጉጉት ሲጠበቅ ነበር።
ይህ ውጤት ለቀጣዩ ጨዋታዎችም ከፍተኛ መነቃቃት የፈጠረ ሲሆን ቀሪዎችነም 10 ጨዋታዎች እጅግ አጓጊ ያደርገዋል።
ለባንካችን እግር ኳስ ቡድን እንኳን ድስ አላችሁ ለቀጣዩም መልካም እድል።