Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጵያ የዲጂታል የክፍያ ስርአት እንዲያድግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

በኢትዮጵያ የዲጂታል የክፍያ ስርአት እንዲያድግ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎት ከፍተኛ እገዛ ማድረጉ የባንካችን ፐሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ ገለጹ።
================
በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዘጋጅነት ዛሬ በእስካይ ላይት ሆቴል በተዘጋጀው በዚህ ኮንፍረንስ ላይ በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፡ የፋይናንስ ተቋማት ፡ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች ተገኝተዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኢትዮጵያ የዲጂታል ባንክ አገልግሎት አሁን ለደረሰበት ደረጃ የተጫወተውን ሚና አስመልክተው ገለፃ አድርገዋል፡፡
አቶ አቤ እንዳሉት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዲጂታ ባንክ አገልግሎትን ለደንበኞቹ ከማስተዋወቅ እና ግንዛቤ ከመፍጠር አንስቶ ለሌሎችም አርአያ በሚሆን መልኩ ለዘርፉ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽዎ እንዳረገ ጠቁመዋል። ይህ ደግሞ በኢትዮጵያ ለዲጂታል የክፍያ ስርአት እድገት የላቀ ሚና እንዲወጣ አስችሎታል ብለዋል።
አቶ አቤ አክለውም ለዲጂታል የክፍያ ስርአት መጎልበት በሀገሪቱ የሚገኙ ባንኮች፡ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ፡ ቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና የዘርፉ ተሳታፊዎች በጋራ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በዚህ መልኩ የዘርፉን ተሳታፊዎች ያሳተፈ የውይይት መድረክ ማሰናዳቱ እርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ እንዲኖር ያስችላል ብለዋል።
በመጨረሻም እንደነዚህ አይነት የውይይት መድረኮች በሀገር አቀፍ ደረጃ በዲጂታል የክፍያ ስርአት ላይ ለሚወጡ ስትራቴጂዎች እና ፖሊሲዎች ከፍተኛ ግብአት የመሆን አቅም ኣላቸው ብለዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ባንኮች ፣የቴክኖሎጂ አቅራቢዎች እና የግሉ ዘርፍ ፋይናንስ ተቋማት ተሳታፊዎች ነበሩ፡፡