Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከሀምበርቾ ጨዋታ ያደርጋል፡፡ ********** በኢትዮጵያ ፕሪሚየር | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ከሀምበርቾ ጨዋታ ያደርጋል፡፡
**********
በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሃ ግብር የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን ከሀምበርቾ ዛሬ፣ መጋቢት 26፣ 2016 ከምሽቱ 1፡00 በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታውን የሚያደርግ ይሆናል፡፡

መቻል ፕሪሚየር ሊጉን በ39 ነጥብ እየመራ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በፕሪሚየር ሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ከቅዱስ ጊዮርጊስ በእኩል 37 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ በሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ7 ነጥብ የደረጃ ሰንጠረዡ ግርጌ የሚገኘውን ሀምበርቾ በቀላሉ ያሸንፋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መልካም እድል ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወንዶች እግር ኳስ ቡድን!