Get Mystery Box with random crypto!

የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም ያለአግባብ የተወሰደን ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ እንደሚቻል ስለ | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በመጠቀም ያለአግባብ የተወሰደን ገንዘብ ተመላሽ ማድረግ እንደሚቻል ስለማሳወቅ
===========================
ባንካችን አንዳንድ ግለሰቦች ያለአግባብ የወሰዱትን የራሳቸው ያልሆነ ገንዘብ እስከ ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ ም ድረስ በአቅራቢያቸው በሚገኝ የባንካችን ቅርንጫፍ በመገኘት እንዲመልሱ ጥሪ ባደረገው መሰረት በርካታ ግለሰቦች በቅርንጫፎች እየቀረቡ ገቢ እያደረጉ ቢሆንም ተጨማሪ የመመለሻ ኣማራጭ መስጠት ጠቃሚ እንደሆነ ታምኖበታል::

ስለዚህ ከቅርንጫፎች በተጨማሪ የዲጂታል የክፍያ አማራጮችንም በመጠቀም በቀጥታ ቀድሞ ገንዘቡ አለአግባብ ወጪ ወደተደረገበት በባንካችን የሚገኝ የባንክ ሂሳባችሁ ማስተላለፍ (transfer) እና ገቢ ማድረግ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።