Get Mystery Box with random crypto!

የጥንቃቄ መልዕክት ************** አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን | Commercial Bank of Ethiopia - Official

የጥንቃቄ መልዕክት
**************
አጭበርባሪዎች ሰሞኑን ከሲስተም ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ችግር እንደ አጋጣሚ ለመጠቀም ሙከራ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ደርሰንበታል፡፡
እነዚህ አጭበርባሪዎች በአብዛኛው ከባንክ የደወሉ በማስመሰል “የተዘጋ ሂሳብችሁን እንክፈትላችሁ” ፤ “ሂሳባችሁ እንዳይዘጋ የምንልክላቹሁን ኮድ አስገቡ” የሚል የማጭበርበሪያ ዘዴ በመጠቀም የዘረፋ ሙከራ በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
ነገር ግን ባንካችን ስልክ ደውሎ ስለ ሂሳብዎ መረጃ የሚጠይቅበት፣ ሂሳብ የሚከፍትበትም ሆነ የሚዘጋበት አሰራር እንዲሁም ደንበኞች እንዲጠቀሙበት የሚልከው ምንም አይነት ኮድ የለም፡፡
በመሆኑም ማንኛውም የባንካችን ደንበኛ መሰል ሁኔታ ሲገጥመው ምንም አይነት እርምጃ ከመውሰድ በመቆጠብ በአቅራቢያ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ አሊያም በ951 የባንኩ የደንበኞች ጥሪ ማዕከል በመደወል ስለሁኔታው መረጃ መጠየቅ እንዳለበት እናሳስባለን፡፡