2023-03-05 17:26:13
ቀጣዩን የቴክኖሎጂ ዘመን በአግባቡ የሚጠቀምና የሰለጠነ ማህበረሰብ ለማፍራት በትኩረት ልንሰራ ይገባል። ማተብ ታፈረ /ዶክተር/
========================
የካቲት 26/2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከትምህርት አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ጋር በደብረ ማርቆስ ከተማ የ6 ወራት እቅድ አፈጻጸም ግምገማና የልምድ ልውውጥ አካሂዷል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ ቀጣዩን የቴክኖሎጂ ዘመን በአግባቡ የሚጠቀምና የሰለጠነ ማህበረሰብ ለማፍራት በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ለዚህም መምህራንና የትምህርት ዘርፉ አመራሮች የመማር ማስተማር ባህልን የበለጠ ለማሻሻል መስራት እንዳለባቸው ኃላፊው አሳስበዋል።
ኃላፊው የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻል ከህብረተሰቡ ጋር በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል። በመንግስት ትምህርትቤቶች ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ደረጃ አንድ ላይ የሚገኙ ሁሉንም ተቋማት ወደ ደረጃ ሁለትና ከዚያ በላይ ለማሳደግ እንዲሁም በየዞኑ ሞዴል የሆኑ ደረጃ አራት ትምህርትቤቶችን ለመፍጠር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። ደረጃቸውን ያላሟሉ የግል ትምህርትቤቶች ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ ተማሪዎችን መቀበል እንደማይችሉ ተረድተው ከወዲሁ ደረጃቸውን ለማሻሻል እንዲሰሩ ኃላፊው አመላክተዋል።
በቀጣይ ለሚፈተኑ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተለየ መንገድ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባም ተገልጿል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
1.9K views14:26