2023-04-07 14:38:42
አይ አር ሲ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት በ24 ሚሊዮን ብር ወጭ ያሳተማቸውን ከ87 ሽህ በላይ የአንደኛ ደረጃ የመማሪያ መጽሐፍት ለትምህርት ቢሮ አስረከበ።
===============================
ድርጅቱ በ24 ሚሊዮን ብር ወጭ ያሳተማቸውን 87 ሽህ 590 ከአንደኛ እስከ አራተኛ ክፍል በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የተዘጋጁ የተማሪዎች የመማሪያ መጽሐፍት ለትምህርት ቢሮ አስረከቧል።
መጽሐፍቱ በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው 162 ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 56 ሽህ የሚሆኑ ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን የአይ አር ሲ ድርጅት የአማራ ክልል አስተባባሪ አቶ ሀብታሙ ሞላ ገልጸዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አቢ አይ አር ሲ ትምህርትን በአደጋ ጊዜ ማስቀጠል መርሀ ግብር በክልሉ በርካታ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል። ድርጅቱ በተለየ ሁኔታ ከትምህርት ቢሮ የቀረበለትን የመጽሐፍት ህትመት ጥያቄ ተቀብሎ በማሳተሙ አመስግነዋል። ሌሎች አጋር ድርጅቶችም መጽሐፍት አቅርቦት ላይ የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ ወንድወሰን ጥሪ አቅርበዋል።
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
2.9K views11:38