2023-02-27 09:45:22
በተማሪዎች ውጤታማነትና የቀጣይ የትኩረት ነጥቦች ዙሪያ ከ12ኛ ክፍል የተማሪ ወላጆች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።
*******************
የካቲት 20/2015ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የ12ኛ ክፍል ተማሪ ወላጆች እና የትምህርት ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በተማሪዎች ውጤታማነትና የቀጣይ የትኩረት ነጥቦች ዙሪያ የምክክር መድረክ ተካሂዷል።
የምክክር መድረኩ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ሀዲስ አለማየሁ አዳራሽ የተካሄደ ሲሆን የተለያዩ የመወያያ ፅሁፎች በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ ምሁራን ቀርቧል።
በመድረኩ ተጋባዥ እንግዶች በትምህርት ውጤታማነት ዙሪያ ለወላጆችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት ልምዳቸውን አካፍለዋል።
ደብረ ማርቆስ ኮሚኒኬሽን
ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት የሚከተሉትን አማራጮች ይጠቀሙ
1. በዌብ ሳይት ገጻችን http://www.anrseb.gov.et/
2. በዩቱብ ቻናላችን https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
3. በፌስ ቡክ ገጻችን https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
4. በቴሌግራም ቻናላችን t.me/anrse
ያግኙን
820 views06:45