Get Mystery Box with random crypto!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahmedin99 — Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
የሰርጥ አድራሻ: @ahmedin99
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 59.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2024-03-11 09:05:41

12.7K views06:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 22:03:05
«ውሃን በመጎንጨት ቢሆን እንኳ ስሁርን ተጠቀሙ።»

ነብዩ ሙሐመድ ‎ﷺ

T.me/ahmedin99
13.9K views19:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 19:23:15
ስንቶች እየተመኙት ያላገኙትን እድል አገኘን። ወዳጆቻችን ቀብር ውስጥ ክንዳቸውን ተንተርሰዋል። እኛ ግን ይኸው አለን።ረመዳንን ደርሰን። ይህ መታደል ነውና አመስግኑ። የአላህ ችሮታ ነውና ተደሰቱ። ከዚህስ በላይ መታደል አለን? “አልሀምዱሊላህ” በሉ። በደስታ እንግዳችሁን አክብሩ። ክብሩን ጠብቃችሁ አስተናግዱት። ይሄ እንግዳ ጀነታችሁ ነው። ከእሳት መድህናችሁ ነው። ሽልማታችሁ ነው። ምሽጋችሁ ነው። ጋሻችሁ ነው። ያደረግንለትን አቀባበል ነገ አላህ ፊት የሚመሰክረው እንግዳችን ከኛ ጋር በእንግድነት የሚቆየው ጥቂት ቀናትን ነውና ሐቁን ጠብቁለት።
15.9K views16:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 18:21:49 ረመዳን ሙባረክ!

የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ነገ ሰኞ march 11 እንደሚጀምር ታውቋል።
12.7K views15:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-10 11:33:45 በአዲስ ተከታይ (ፎሎ) 30 ብር ፣ በሼር 10 ብር ልዩ የረመዳን ስጦታ በይፋ ተጀመረ።

የኢትዮ ቴሌኮም ማህበራዊ ገጽን ፎሎ ሲያደርጉ በእያንዳንዱ ፎሎ 30 ብር ፣ በተጨማሪም ሼር ሲያደርጉ 10 ብር ለእያንዳንዱ ኢትዮ ቴሌኮም ለባቡል ኸይር ክፍያ ይፈጽማል። ከእርሶ ምንም አይነት ክፍያ ሳይቀነስ።

ውድ የሀገሬ ልጆች በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮጵያዊያን ፣ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ፊታችሁ ቁሜ የምጠይቃችሁ አንድ ደቂቃ ስልካችሁን በመጠቀም ብቻ የኢትዮ ቴሌኮም ገጾችን እንድትወዳጁና ባቡል ኸይር የምገባና የአረጋዊያን መጠለያ ማዕከል ፕሮጀክትን እውን እንድናደርግ በያላችሁበት አንባሳደር በመሆን ራሳችሁን ቤተሰቦቻችሁን ፣ ጓደኞቻችሁን ፣ በስሮቻችሁ የሚገኙ ሰራተኞቻችሁን በማስተባበር የአንድ ደቂቃ ዘመቻን እንድትቀላቀሉ ከአደራ ጭምር በአረጋዊያን እና በአቅመ ደካሞች እና በወጣቶች የባቡል ኸይር ቤተሰቦች ስም እጠይቃቹሃለው።

ሊንኮቹን በመንካት ዘመቻውን ይቀላቀሉ


1. ፌስቡክ ኢትዮ ቴሌኮም : https://www.facebook.com/ethiotelecom

2. ቴሌ ብር : https://www.facebook.com/telebirr?mibextid=LQQJ4d

3. ቴሌግራም፡ https://t.me/ethio_telecom

4. ቲክቶክ፡ http://www.tiktok.com/@ethio_telecom?lang=en

5. ዩትዩብ፡ https://www.youtube.com/c/EthiotelecomETH

6. ኢንስታግራም ፡https://www.instagram.com/ethiotelecom/

7. ቲዊተር : https://twitter.com/ethiotelecom

8. ሊንክዲን፡ https://www.linkedin.com/company/ethio-telecom

ስምንቱን የኢትዮ ቴሌኮም ገጾችን ፎሎ ሲያደርጉ 240 ብር ለባቡል ኸይር ለገሱ ማለት ነው።

በተጨማሪም ሼር ሲያደርጉ በእያንዳንዱ 10 ብር በስምንቱ 80 በድጋሚ ለገሱ ማለት ነው።

በድምሩ 320 ብር በአንድ ደቂቃ ውስጥ ከ እርሶ ምንም ሳይቀነስ ለባቡል ኸይር ድጋፍ አደረጉ ማለት ነው። ይህን እድል ማለፍ አያስቆጭምን?


በተጨማሪ:- 7335 ላይ በቀጥታ ሚሴጅ Ok ብሎ በመላክ የባቡል ኸይር ቋሚ ቤተሰብ ይሁኑ!

#አታግዙንም
#አንተባበርም
#ከመጋቢት1 #እስከመጋቢት30
#MatchingFundForSustainableFuture
#Ethiotelecom #telebirr
#RealizingDigitalEthiopia
14.5K views08:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-07 18:51:44
ብርቅዬ 13 ዓመታት – ኑር ኢስላሚክ ሴንተር
.
ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በካሪኩለንም በመታገዝ በቁርዓን ፣ በሂፍዝ ፣ በሀዲስ ፣ በፊቅሂ ፣ በተጅዊድ ፣ በነህውና በሌሎች ኢስላማዊ ዘርፎች እያፈሩ 13 ዓመታትን ተሻግረዋል።

ኢስላማዊ ተቋማት እምብዛም ባልነበሩበትና ባልታወቁበት ፣ በጊዜው በነበሩ የአገዛዝ ስርዓቶች የሚደርሱ ችግሮችንና ተግዳሮቶችን በማለፍ በአላህ ችሮታ ለዛሬ በቅተዋል። ከዲናዊ እውቀት ባሻገር ለተማሪዎች የቲቶርር እገዛዎችን በማድረግ ፣ የማንበቢያ ላይበረሪዎችን በማመቻትና ሪፈረንሶችን በማቅረብ በትምህርታቸው የበቁ በጥሩ ውጤት ወደ ውጭ ሀገር ሄደው የሚማሩና በሀገራችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጀምዓ አሚርነት እያገለገሉ የሚገኙ ወጣቶችን አፍርተዋል።

ትውልዱ ካለበት የእውቀት ክፍተት ባሻገር ያሉብንን የማህበራዊ ሀላፊነቶች ለመወጣት እልፍ አይታሞችን ተንከባክበው አሳድገዋል። ብዙ ባላቸው የሞተባቸውን የቲም የሚያሳድጉ እህቶችን ቋሚ የስራ ዕድል በማመቻት ደግፈናል። የምስኪን እናቶች የፈረሱ ቤቶችን እንደአዲስ ገንብተዋል።
.
ዛሬ ላይ ኑር ኢስላሚክ ሴንተር ከ410 በላይ ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን ይዞ በዲናዊ እውቀት ለማነፅና በትምህርታቸው የበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል እየሰራ የሚገኝ ኢስላማዊ ተቋም ነው።
.
ኑር ኢስላሚክ ሴንተር በእነዚህ ብርቅዬ 13 ዓመታት በነበሩን የጉዞ ሂደቶች ያገዙን አካላትን ሊያመሰግን ፣ ከዚህ በፊት ከሚሰራው ስራዎቹ ባሻገር ሌሎች ትልሞችን ሰንቆ ወደ ላቀ ቀጣይ ምዕራፍ መሻገሩን ሊያበስር ነገ ጁምዓ የካቲት 29 በሸራተን አዲስ ሆቴል በአላህ ፍቃድ ደማቅ ፕሮግራም አሰናድቶ ቀጠሮ ይዘናል።
.
#ብርቅዬ_13_ዓመታት

#ለተሻለ_ትውልድ
15.5K viewsedited  15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-03 22:46:37 ባለፈው አመት ረመዳን ሲጠናቀቅብህ የተፀፀትክባቸው በርካታ ጉዳዮች ይኖራሉ።

ከነዚህም ውስጥ...
ቁርአን ያከተምከው ትንሽ ጊዜ መሆኑ

የሌሊት ሶላት ላይ የነበረብህ ክፍተት

የሰጠኸው ሰደቃ አናሳ መሆን

ሰዎችን አለማስፈጠርህ

ያልተፈቀዱ ነገራቶችን መመልከትህና ማድመጥህ

ከቤተሰብና ጓደኛ ጋር የነበረህ ጥሩ ያልሆነ ግንኙነት

ዚክር ላይ የነበረህ ድክመት

ሶላትን በጀመዓ ያለመስገድህ ሊሆን ይችላል።

ታዲያ አላህ አድሎህ ለዚህ ረመዳን ካደረሰህ፤ የዘንድሮውን ረመዳን ከአምናው ረመዳን በምን ልትለየው አስበሃል
ወይስ ሃሳብህ ተመሳሳይ ረመዳንን ለማሳለፍ ነው

አሁንም ተዘናግተህ ከሆነ ትቶህ እየነጎደ መሆኑን አስተውል
13.3K views19:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 22:27:22 Ergaa Muslimonni mana amala sirreessaa Ziwaay jiran dhaammatan
~
Nuti (sirreeffamatoonni) muslimoonni mana amala sirreessaa Ziwaay jirru 480 Ramadaanaa dhufe kanaaf galtee ifxaraaf ittiin qophoofnu homaa waan hin qabneef, kanaaf ammoo qarshii kuma 800 ol waan nu barbaachisuuf obboleeyyan Muslimaa ergaan kun isin qaqqabe hanga dandeessan deeggarsa akka nuuf gootan maqaa Rabbiitiin isin gaafanna.

• Bankii Daldala Itiyoophiyaa
• Lakkoofsa Herreegaa: 1000607361596
• Maqaan: Daawud Hasaniifi Abdurrahmaan Waabalaa
14.7K views19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-03-01 18:29:53
በዝዋይ ማረሚያ ቤት ከሚገኙ ሙስሊም ታራሚዮች የተላለፈ ጥሪ


እኛ በዝዋይ ማረሚያ ቤት የምንገኝ 480 ሙስሊም ታራሚዎች መጪውን ረመዳን ኢፍጣር የምንዘጋጅበት ምንም ግብዐት የሌለን በመሆኑ እና ይህንንም ለመሸፈን ከ800ሺህ ብር በላይ ስለሚያስፈልገን ይህንን መልዕክት የምትከታተሉ ሙስሊም ወንድም እህቶች የተቻላችሁን ድጋፍና ትብብር ታደርጉልን ዘንድ በአላህ ስም እንጠይቃለን።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

አካውንት ቁጥር 1000607361596

ስም፦ ዳውድ ሀሰንና አብዱራህማን ዋበላ
14.6K views15:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-02-26 21:11:28
የሰደቃ ትንሽ የለውም!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿تصدَّقوا ولو بتَمرةٍ﴾

“በቴምርም ቢሆን ሰደቃ ‘ምፅዋት’ አድርጉ።”

ሶሂህ አልጃሚ: 2951

Rasuulli akkana jedhaniiru'-

Timoraanillee taanaan sadaqaa godhaa (kennaa)

Sahih Aljaami: 2951
14.8K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ