Get Mystery Box with random crypto!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahmedin99 — Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
የሰርጥ አድራሻ: @ahmedin99
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 59.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 48

2022-07-09 06:59:08 የኢድ ተክቢራ
T.me/ahmedin99
21.7K views03:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:10:02
ኢድ ሙባረክ፤ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በሰላም አደረሰን!

ተቀበለላሏሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊኸል አዕማል

Iid Mubaarak! Baga ayyaana Iid al-adha bara 1443tiin nuun gahe!

Taqabbalallaahu minnaa waminkum Saalihal a'amaal

★ T.me/ahmedin99
24.5K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 20:27:44 ኡድሒያን የሚመለከቱ ወሳኝ ነጥቦች

ኡድሒያ ማለት በዐረፋ በዓል ቀን እና ቀጥሎ ባሉ ተከታታይ ሶስት ቀናት ውስጥ ወደ አላህ ለመቃረብ ተብሎ የሚታረድ የቤት እንሥሳ ማለት ነው።
"ኡድሒያ" የተባለው የእርዱ ሰዓት የሚጀምረው የዒድ ቀን ረፋድ (ዱሓ) ላይ ስለሆነ ነው።

ኡድሒያ ማረድ የዲን አካልና ተወዳጅ ተግባር መሆኑ ላይ ሁሉም ሊቃውንት ይስማማሉ፤ ብዙሃኑ ሊቃውንት ዘንድ ሱንናህ እንጂ ስለት (ነዝር) ለሌለበት ሰው ግዴታ አይደለም። አቡ ሐኒፋን ጨምሮ በርካታ ግዴታ ነው የሚል አቋም ያላቸው ሊቃውንት ስላሉና በዒድ ቀን ማረድ ልዩና ከፍ ያለ ምንዳም ስላለው አቅም ያለው ሰው ኡድሒያ ማረድ ባይተው ይመረጣል፤

ከቤት እንስሳት (ከግመል፣ ከከብት ፣ ከበግና ፍየል) ውጪ ሌላን እንስሳ ለኡድሒያ ማረድ እንደማይቻል የፊቅህ ሊቃውንት በሙሉ (ከሐሰን ኢብኑ ሳሊሕ በስተቀር) ይስማማሉ።

ለኡድሑያ የሚታረደው እንስሳ ወንድም ይሁን ሴት ለውጥ የለውም፤ ሁለትም ጾታዎች ለኡድሒያ እንደሚሆኑ (እንደ ሚበቁ) የፊቅህ ሊቃውንት ይስማማሉ።

የዒድ ቀን ከሰላተል-ዒድ በፊትና፣ ከ 14ኛው ቀን የጸሐይ መጥለቅ በኋላ የሚታረድ እርድ ከኡድሒያ አይቆጠርም።

በመሰረቱ የኡድሑያ እንስሳ መግዣ ገንዘቡን ሰደቃ ከመስጠት ይልቅ ኡድሒያ ማረዱ በአጅር ይበልጣል። ይህም የሆነው ኡድሒያ በዕለቱ ተወዳጅና ከዒድ ሰላት ጋር የተያያዘ ዒባዳህ ስለሆነ ነው። (ኢብኑልቀይም)

ነገር ግን ገንዘቡን መስጠቱ ለተቸገረ ሰው ይበልጥ የሚጠቅምበት ሁኔታዎች ላይ በላጩ ገንዘብ መስጠቱ ይሆናል። (ኢብኑ ዑሠይሚን)

ብዙሃኑ የፊቅህ ሊቃውንት ዘንድ ለኡድሒያ እርድ በላጭና ተመራጩ እንስሳ በቅደም ተከተል ግመል፣ ከዛም ከብት፣ ከዛ በግ ወይም ፍየል ነው።
ይህ የሚባለው ግን ግመል ወይም ከብት አንድ አባወራ ለብቻው የሚያርድ ከሆነ ነው። ለጋራ ወይም በቅርጫ ከሆነ ግን የሚያርደው ከግመልና ከከብት ይልቅ በግ ወይም ፍየል ይሻላል።
ኢማሙ ማሊክ በሁሉም ሁኔታ ላይ በላጩ በግና ፍየል፣ ከዛም ከብት፣ ከዛ ግመል ነው የሚል አቋም አላቸው።
ይህ በላጩና ይበልጥ ተወዳጁን ከመግለጽ አንጻር ነው እንጂ ከ4ቱ የቤት እንስሳት ውስጥ ማንኛውንም ቢያርዱ ትክክል ይሆናል።

ለኡድሒያ የሚታረድ ማንኛውም እንስሳ ቁመናና መልኩ የሚያምረው፣ ስጋው ይበልጥ ጣፋጭና ንጹህ ይሆናል የሚባለውና በዋጋም ውድ የሆነው ከዚህ ተቃራኒ ከሁኑ እንስሳት ይልቅ ለኡድሑያ ተወዳጅ እንደሚሆን ሊቃውንት ይስማማሉ። (አን'ነወዊይ)

ይህም ኡድሒያ የሚታረደው ለአላህ ተብሎ ስለሆነና ለርሱ የሚደረግ ነገር በሙሉ ንጹሁ፣ ትልቅና የሚያምር መሆን ስለሚገባው ነው።

ለኡድሒያ የሚታረድ እንስሳ እድሜው በግ ከሆነ 6 ወርና ከዛ በላይ፣ ፍየል ከሆነ 1አመትና ከዛ በላይ፣ ከብት ከሆነ 2 አመትና ከዛ በላይ፣ ግመል ከሆነ 5አመትና ከዛ በላይ መሆን አለበት።
ዕድሜው እዚህ ከተጠቀሰው በታች የሆነ እንስሳ ለኡድሒያ በቂ አይሆንም።

በተፈጥሮ ምንም ቀንድ የሌለው ወይም ቀንዱ በጣም ትንሽ የሆነ፣ ጭራ ወይም ላት የሌለው፣ የተኮላሸ፣ ጆሮው የተሰነጠቀና ከግማሽ በታች የሚሆነው ብቻ የተቆረጠ እንስሳን ለኡድሒያ ማረድ ችግር የለውም።
በላጩ ግን ቀንድ ያለውና አካላቱ ሙሉ የሆኑትን ማረዱ ነው።

ግልጽ የሆነና እንደልቡ ተንቀሳቅሶ እንዳይበላ የሚያደርግ ሸፋፋነት ያለበት፣ አንድ ወይም ሁለቱም አይኑ የማያይ፣ በጣም ከመክሳቱ የተነሳ ቅልጥም፣ ጮማና ሞራው ያለቀ/የሌለው፣ ግልጽ የሆነ በሽታ ወይም የበሽታ ምልክት ያለበት ማንኛውም እንስሳ ለኡድሒያ አይሆንም።

ከላይ ከተጠቀሱት እንከኖች ጋር ተመሳሳይና የባሰ እንከን ያለበትንም ማረድ አይቻልም።
ነገር ግን ከእነዚህ እንከኖች መካከል ቀላልና ግልጽ ያልሆነ ያለበትን ማረድ አማራጭ ካጡ እንደሚቻል ሊቃውንት ይስማማሉ።ጤነኛና ከእንከን ንጹህ ሆኖ የገዙት እንስሳ ያለጥንቃቄ ጉድለት ከላይ የተጠቀሱ እንከኖች ቢገጥሙት ማረድ ይቻላል፤ አቅም ያለው ሰው ሌላ ቢቀይር ግን ይመረጣል።

አንድ በግ ወይም ፍየል ለአንድ አባወራ እስከ ቤተሰቦቹ፣ አንድ ከበት ወይም ግመል ለ7 እና ከዛ በታች ለሆኑ አባወራዎች ( ቤተሰቦች) ይበቃል።
አንድ ሰው ኡድሒያው ላይ ማንኛውንም (በህይወት ያለም ይሁን የሞተን) ሰው በምንዳው ማጋራትና ማካተት ይችላል።

ለአንድ አብሮ ለሚኖር ቤተ ሰብ አንድ ኡድሒያ የሚበቃ ከመሆኑም ጋር አቅም ያለው በሙሉ በስሙ ኡድሒያ ቢያርድ መልካም ይሆናል።

አንድ እንስሳ ቤት ውስጥ ተወልዶ ያደገ (የረባ)ም ይሁን፣ እራሱ ወይም ገንዘቡ በስጦታ መልኩ የተገኘም ይሁን በማንኛውም ህጋዊ በሆነ መንገድ የራስ የተደረገ ከሆነ ለኡድሒያ ነይቶ ካረዱት በቂ ይሆናል። የግድ በጊዜው ለኡድሒያ ተብሎ በራስ ገንዘብ የተገዛ ካልሆነ አይባልም።

አንድን እንስሳ ለኡድሒያ ከወሰኑት በኋላ ሀሳብ ቀይሮ ማረዱን መተው፣ መሸጥ ወይም ለሌላ ሰው ስጦታ መስጠት አይቻልም።ግዴታ ላልሆነ ኡድሒያ የተዘጋጀ እንስሳ ያለጥንቃቄ ጉድለት ቢጠፋ ሌላ መተካት ግዴታ አይሆንም።

ለኡድሑያ የታረደን እንስሳ ቆዳውንም ይሁን ምኑንም መሸጥ፣ ለአራጅ ክፍያ ይሆን ዘንድ ብሎ ምንም ነገር መስጠት አይቻልም።በምንም መልኩ ክፍያው ላይ ተጽዕኖ ሳይኖረው ለአራጅ እንደተጨማሪ ስጦታ ወይም ሰደቃ መስጠት ግን ይቻላል።

ኡስታዝ አሕመድ አደም
19.9K views17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 15:57:52 የመልክተኛው ﷺ የሀጀቱል ወዳዕ (የመሰናበቻዋ ሀጅ ) ላይ ያስተላለፉት ውብ መልዕክት

ሰዎች ሆይ ከዚህ አመት በኋላ ከመካከላቹ እንደገና መገኘቴን አላውቅምና ልብ ብሎ የሚያዳምጥ ጆሮዋቹን አውሱኝ። ዛሬ የምነግራችሁን ቁም ነገር በጥሞና አዳምጡኝ በዚህች እለት ከመካከላቹ ላልተገኙም መልክቴን አድርሱ።

ሰዎች ሆይ !! የዛሬው ቀን ፤ይህ ከተማ የተቀደሱና የተከበሩ መሆናቸውን የምታውቁትን ያህል የያንዳንዱን ሙስሊም ህይወትና ንብረትን በክብር እንድቲዙ አደራ ተጥሎባቹሀል።

በእጃችሁ የሚገኙትን የአደራ እቃዎች ለባለቤቶቻቸው መልሱ ! ማንም ሰው እንዳይበድላቹ ማንንም አትበድሉ!

ያለምንም ጥርጥር ፈጣሪያቹ ዘንድ በግንባራቹ ተደፍታችሁ እንደምትቀርቡ አትዘንጉ።

የብድር ወለድ ተግባራችሁንም መክፈል ከንግዲህ በኃላ እርም ተደርጎባቹሀል።

ዲናቹን ለመንከባከብ ከ ሸይጧን ተጠንቀቁ!
በትልልቅ ጉዳዮች እናንተን አሳስቶ በዱንያ ላይ እናንተን አዘቅት ውስጥ ለመጣል የሚያደርገው ሙከራ ተስፋ ስላስቆረጠው በጥቃቅን ጉዳዮች ተከታዩ እንዳትሆኑ እራሳችሁን ጠብቁ።

ሰዎች ሆይ! በሴቶቻቹሁ ላይ የተወሰነ መብት ያላቹ መሆኑ እርግጥ ነው... ነገር ግን እነሱም በናንተ ላይ መብት አላቸው! በናንተ ቁጥጥር እስካሉ ድረስ እነሱን መመገብ ፣ማልበስና በእዝነትና በርህራሄ የመያዝ ግዴታ ይኖርባቹሀል።

ሴቶቻቹ የኑሮ ጓደኞቻቹና የቅርብ ደጋፊያቹ ናቸው!በርህራሄና አግባብ ባለው መንገድ ተንከባከቧቸው። እናንተ ከማትፈልጉት ሰው ጋር ጓደኝነት እንዳይመሰርቱ ቤታቹ በጭራሽ እንዳይፈርስ ማድረግ ይኖርባቹሀል።

ሰዎች ሆይ !! በሚገባ አድምጡኝ አላህን ተገ፣ በቀን አምስት ጊዜ ሰላታቹን ስገዱ፣ የረመዳንንም ወር ፁሙ፣ ከንብረታቹም ዘካን ስጡለት፣ እንዲሁም ከተቻላቹ ሀጅንም አድርጉ።

እያንዳንዱ ሙስሊም ለሌላው ሙስሊም ወንድም መሆኑንን ታቃላቹ!? ሁላቹም እኩል ናችሁ።
ማንም ሰው ከሌላው ሚበልጥበት መንገድ የለም !!... አላህን መፍራትና በመልካም ተግባሩ ቢሆን እንጂ ።

አስታውሱ !! አንድ ቀን ጌታቹ ፊት ቀርባቹ ስለሰራቹት ስራ ትጠየቃላቹ! ስለዚህም ተጠንቀቁ እኔ ካለፍኩኝ ቡሃላ አላህን ከመፍራት ጎዳና እንዳታፈነግጡ ።

ሰዎች ሆይ !! ከኔ ቡሃላ አዲስ ነብይ አይመጣም!
አዲስ እምነትም አይወለድም!
በሚገባ እውቀትን ፈልጉ።

ህዝቦች ሆይ !! የማስተላልፈውን መልክት በትክክል ተረዱ። ከኋላዬ ሁለት ነገርን ቁርዓንንና ሱናን ትቼላቹ አልፋለው እሱን ከተከተላቹ ስህተት ላይ ከመውደቅ ትድናላቹ።

ያዳመጠኝ ሁሉ መልዕክቴን ላልሰሙት ያስተላልፍ። ምናልባትም የመጨረሻዎቹ አድማጮች ከኔ አንደበት ከሰሙት ይልቅ በተሻለ ሊይዙት ይችላልና።

አላህ ሆይ መልዕክትህን ለህዝቦቼ ማድረሴን ምስክሬ ሁን።

ይህንን መልክት ካስተላለፉ በኋላ ቀጣዩ አመት ሀጅ ከመድረሱ በፊት ታላቁ ተወዳጁ ነብይ እንደተመኙትም ወደ ጌታቸው እዝነት ሄዱ።
18.7K views12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 14:08:16
Warra hajjii baranaa godhuu hin danda'iniif! Ibnu Rajab Rabbiin Raahmata haagodhuufi akkana jadhaniiru:-

namni gaara arafaarra dhaabatu carraa hin argatin, daangaa Rabbii beekurratti of qabe haadhaabatu.

muzdalifaas namni buluu hin danda'iin Rabbii isaatitti dhihaachuuf ajajamaa ta'ee haa bulu.

Qalmas minaatti namni godhuu hin danda'iin Rabbiif jecha fedhi isaa haa qalu(fedhii lubbuu isaa haa dhiisu).

namni gara mana isaa(kaa'abaa) sababa fageenyaatin gahuu hin danda'iin gara Rabbii hidda dhiigaa isaa irra itti dhihaatu haa kajeelu

(Ibnu Rajab lixxaa'if Al-ma'araf 633)
16.6K views11:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 10:00:27 በአመት አንድ ቀን ብቻ የሚገኘውን እለት ምንልባትም በድጋሚ እናግኘው ወይም አናግኘው እርግጠኛ መሆን በማንችለው በዚህ እለት በሚገባ ጊዜያችንን ተጠቅመን፣ በርትተን ሳንሰላች ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን፣ ለልጆቻችን በአጠቃላይ በኛ ላይ ሀቅ ላላቸው ሁሉ ፣ ለመላው ሙስሊም ማህበረሰብ በዱንያም ይሁን በአኼራ መልካምን እንዲሰጠን ዱዓእ ልናደርግ ይገባል::
16.9K views07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 08:40:34
በዚህ አመት ሀጅ ማድረግ ያልቻላችሁ ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

አራፋ ተራራ ላይ የመቆም እድል ያላገኘ፣በሚያውቀው የአምላኩ ወሰን ላይ ታቅቦ ይቁም።

በሙዝደሊፋም ማደር ያልቻለ ሰው እሱ ዘንድ ይቃረብበት ዘንድ ለአምላኩ ታዘዥ ሆኖ ይደር።

ስጦታንም በሚና ማረድ ያልቻለው ሰው ለአምላኩ ሲል ፍላጎቱን ይረድ(ዝንባሌውን ይቃረን)።

ወደ ቤቱ (ከዕባ) ድረስ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለም ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ዘንድ ይከጅል!"

(ኢብኑ ረጀብ ሊጣኢፍ አል-ማዓረፍ ገፅ 633)
17.3K views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 23:31:26 “ልመናቸውን ለዐረፋ ቀን ተዘጋጅተው በዐረፋ እለት ያንን ጉዳያቸውን ለአላህ ለመንገር የሚዘጋጁ ህዝቦችን አግኝቻለሁ”

ኢማም አል-አውዛዒይ
19.4K views20:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 22:26:04 ዑዝር ላይ ያሉ ወንድም/እሕቶች የአረፋ ቀንን እንዴት ያሳልፉ?

የዐረፋን ቀን ፆም ከልቡ ለመፆም የወሰነ ወንድም/እሕት፣ ነገር ግን በዑዝር ሰበብ (በሽታ፣ ሰፈር፣ ሐይድ፣ የወሊድ ደም፣ ወዘተ) ቀኑን መፆም ባይችልስ? ለሚለው ሸይኽ ስዑድ ከረመዷን ዐሽሩል አዋኺር ጋር ተመሳሳይ ጥያቄ ቀርቦላቸው መልስ ስለሰጡበት: መልሱን እንዲህ አቅርበነዋል:–

ተጠያቂው ሸይኽ ኻሊድ ቢን ሱዑድ

ጥያቄ፡- አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ ያ ሸይኽ! በሐይድ ላይ ያለች ሴት ወይም የወለደች እንዴት አድርጋ የረመዷንን የመጨረሻ አስር ቀናት መጠቀም ትችላለች? ያ ሸይኽ! እኔ በጣም በመጨናነቄ ሰበብ እርሶ እንዲረዱኝና እንዲሁም ሀሳቡና ጭንቀቱ እንዲቀልልኝ እፈልጋለሁ፡፡ አላህም የለይለቱል-ቀድርን ምንዳ እንዳይከለክለኝ ዱዓእ እንዲያረጉልኝ እማጸንዎታለሁ፡፡

ምላሽ፡- ወዐለይኩሙ-ሰላሙ ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ የተከበርሽ እህቴ! ከሁሉ በፊት ቀድመሽ ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- የወር አበባና የወሊድ ደም አላህ እሱ ብቻ ለሚያውቀውና ለፈለገው ጥበብም በአንቺ ላይ የወሰነው የተፈጥሮ ህግ መሆኑን ነው፡፡ መልካም ነገር ደግሞ አላህ ላንቺ የመረጠልሽ ነገር እንጂ አንቺ ለራስሽ የመረጥሽው አይደለም፡፡ አላህ ለወሰነው (ቀዷ ወል-ቀደር) እጅ ስጪ፡፡ ደግሞም አንቺ ለነፍሲያሽ ከጓጓሽው በላይ አላህ ላንቺ አዛኝ ጌታ መሆኑን እርግጠኛ ሁኚ፡፡

በተጨማሪም ልታውቂው የሚገባ ነገር፡- አንድ ሰው በዑዝር ወቅት በሰላም ጊዜ ይፈጽመው የነበረውን ነገር መቀጠል ቢያቅተው እንኳ አጅሩ ግን እንደማይቋረጥበት ነው፡፡ ተወዳጁ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡- "አንድ የአላህ ባሪያ ከታመመ ወይም ከመኖሪያ ክልል ርቆ (ሙሳፊር የሚሰኝበትን ያህል) ከተጓዘ: ጤነኛና የአካባቢው ነዋሪ ሆኖ ይፈጽመው የነበረው (መልካም ስራ) ሳይቋረጥ ይጻፍለታል" (ቡኻሪይ 2996)፡፡

አንቺ ደግሞ በሐይድ ወቅት ያለ ጥርጥር ዑዝር ያለሽ ነሽ፡፡ ምክንያቱም፡- ያለ ምርጫሽና ፍላጎትሽ የመጣ በመሆኑ፡፡ እንዲሁም ልትከላከዪውና ልታስቀሪው የማትችዪው ነገር ስለሆነ፡፡ በድጋሚም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- አንድ የአላህ ባሪያ አንድን ነገር ለመስራት ከልብ የቆረጠ ኒያ ካለው ከዛም ያንን የነየተውን ነገር ለመስራት ድንገተኛ ሁኔታና ክስተት ቢከለክለውና ቢያግደው፤ አላህ ግን እንደሰራው በመቁጠር ሙሉ አጅሩን የሚጽፍለት መሆኑን ነው፡፡ ይህንን አስመልክቶ የአላህ ነቢይም (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) እንዲህ ብለዋል፡-

"በመዲና ውስጥ ሰዎች አሉ፡፡ እናንተ አንድንም ሸለቆ አታቋርጡም መንገድንም አትዘልቁም እነሱ በአጅር ቢጋሯችሁ እንጂ፡፡ ከናንተው ጋር አብረው እንዳይጓዙ ዑዝር ከለከላቸው" (ቡኻሪይ)፡፡

በሌላ ቅዱስ ትምህርታቸው ላይ ደግሞ እንዲህ አሉ፡- "አላህን በፍጹም ልቡ ሸሂድነትን (ለዲን ሰማእት ሆኖ መሞትን) እንዲወፍቀው የለመነ ሰው ቀኑ ደርሶ በፍራሹ ላይ እንኳ ቢሞት(በኒያው ሰበብ) የሸሂዶችን (ሰማእታት) ደረጃ ያጎናጽፈዋል" (ሙስሊም)፡፡

ታዲያ አንቺም እንደ ሌሎቹ ሙስሊም እህቶችሽና ወንድሞችሽ እነዚህን አስር ቀናት በዒባዳ ለማሳለፍ ገና ከመጀመሪያው የነየትሽና የጓጓሽለት ከነበር ጌታሽ ኒያሽን ከንቱ እንደማያረግብሽ ባለሙሉ ተስፋ ሁኚ አብሽሪ፡፡

ሌላው ደግሞ ይህ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ሶላት ከመስገድ፣ ጾም ከመጾምና መስጂድ ከመግባት ቢያግድሽም ሌሎች ያልተከለከልሻቸው ዒባዳዎች መኖራቸውንም አትዘንጊ፡፡ ከነዚም መካከል፡- (ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር…) አዝካሮችን ማለት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ በነቢያችን (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ላይ ሶላዋት ማውረድ፣ ሶደቃ ማውጣት፣ ኢስቲግፋር ማብዛት፣ በአላህ ስሞችና በሱ ስራዎች ማስተንተንን የመሳሰሉት፡፡

በመጨረሻም ማወቅ ያለብሽ ነገር፡- እነዚህ አስር ቀናት በዑዝር ሰበብ ሊያመልጠኝ ነው ብለሽ ማሰብና መጨነቅሽ በራሱ የሚያመላክተው የኢማንሽን ታላቅነት፣ ወደ አላህ ለመቃረብ ያለሽን ጉጉት ነው ኢንሻአላህ፡፡ ስለዚህም የቻልሽውን ያህል ኸይር ስራ ለመስራት ታገዪ፣ ተረጋጊ አትጨናነቂ፣ አይዞሽ፣ አላህ ላይ ያለሽን ተስፋ ከፍ አድርጊ እሱ ኒያሽንም ሆነ መልካም ስራሽን አያባክነውም ምንዳውንም አይከለክልሽም፡፡ የሱ እዝነት አንቺን ብቻ ሳይሆን ዓለሙን ሁሉ የሰፋና ያካለለ ነውና፡፡ ወሰሊላሁመ ወሰለም ዓላ ነቢዪና ሙሐመድ ወዓላ ኣሊሂ ወሰሕቢሂ ወሰለም፡፡

ስለዚህ ነገ ጁምዓ የዐረፋ ቀን ነውና ይህን ቀን እንጹመው እንዳያመልጠን፡፡ አላህ ይወፍቀን አሚን፡፡

ኡስታዝ አቡ ሃይደር
19.3K viewsedited  19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ